(በሁሉባንተ አበበ)
ጽሁፎችን በተለያየ መልኩ ስንጽፋው ለመነበብ አሰልችነቱን እንቀንሳለን ዛሬ እንዲህ አስቤአለሁ አስኪ . . . .
ከተመቻችሁ ተከተሉኝ አስተያየት እቀበላለሁ ካልሆነም ደግሞ
በፍጥነት ብሎጉን ዘጋ ማድረግ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም እድሜ ለነ ጎግል ዛሬ የኢሜል ያክል ብሎጎች እንደ አሸን ፈልተዋል እያንዳንዱን በእያይነቱ ማግኘት ቀላል ነው ። ይኸው እኛም ይህንን ተከትለን
ያላቅማችን ዳንኤል ክብረት እይታወች ብሎ አሳየን እይታ ዕያልን እንከተላለን አይቀርበት ይኸው እንጽፋለን እድሜ ለኮፒይ ፔስት ቴክኖሎጅይ መጻፍ ባንችል እንገለብጣለን ።
ስሙ ሰሞኑን እንዴት እንዳለፈ እኔ ነው የማቀው . .
. ቀድመን ስንጠረጥራት የነበረች ድራማ ይኸው እውን እየሆነች እንደሆነ ተመለከትናት /እንዴት ነው ሰውለሰው እንበላት ወይስ ፓትርያርክ
ለመንግስት/ ። አባት የተባሉትም ምን እንደነካቸው አላቅም ይመስለኛል
ቤተክህነቱም እንደ ቤተመንግስቱ የ ቀድሞ መሪውን /የአቡነ ጳውሎስን/ ራዕይ ለማሳካት እየጣረ ይመስላል። እንዴት ነው ይህ ነገር የራሷ ራዕይ የሌላት ሀገር፤ የራሷ ራዕይ የሌለት ቤተ መንግስት፤ አሁን ደግሞ የራሷ
ራእይ የሌላት ቤተ ክህነት ልንፈጥር ይመስላል እንዴት ነው ራዕይ የሌለው ትውልድ መረን ይሆናል እያላችሁን ? ለሁሉም መጠርጠር
መልካም ነው ብየ ነው እንጂ የፓትርያርካችንን ራእይ ለማሳካት ብላችሁ
በግልጽ አልነገራችሁንም ነገሩ ሰውን እኮ ተግባሩ ነው የሚገልጠው አይደል እንዴ ? ግራ ገባን ኮ ምን እንበል ብላችሁ ነው ? ግን
በእውነት ድራማዋ አፈጣጠኗም ሂደቷም ትመቻለች
ምርጫውም ደግሞ በካርድ ነው አሉ እንዴት ነው ታዛቢስ
ከውጭ አይመጣም እንዴ ? የምረጡኝ ቅስቀሳም እኮ ሳያስፈልገው አይቀርም በዚህ ዐይነት ? ይቅርታ ይቅርታ ነገሩ ተመራጩ በታወቀበት ምርጫ ላይ ለካ ይህ አያስፈልግም
።ነገሩ መዘዙ ነው የሚብሰን ደግሞምኮ ይሁን ቢባል ባበው ጨነቀኝ
እንተወው . . . / መቸም ይህችን ምርጫ ግብጻውያኑ የ አቡነ ሺኖዳ
ልጆች ቢሰሙ ፍርፍር ብለው ነበር የሚስቁብን/። እውነት እውነት የዚህች
እቅድ አቃጅ ግን እውነተኛ ቃሉን ጠባቂ ነው የመሪውን ራዕይ የሚከተል የሚያሳካ። ከ ቤመንግስቱ ባለራዕዮች ከሆነ ያው መቸስ የአገሪቱን አብዛኘውን ቁጥር የያዘ እምነት መሪን በቁጥጥር ስር ማድረግ የትራንስፎርሜሽኑን
እቅድ ለማካት ዋናና ዋና ተግባር መሆኑ የማይጠረጠር ነው ስለዚህ የመሪውን ራእይ ለማሳካት ይህንን ማከናወን የግድ ነው ። ከቤተክህነቱም
ከሆነ ደግሞ ያው በጥቂት አመታት ውስጥ ቤተክርስትያኗን የተሃድሶወች መሮጫ ለማድረግ ለታቀደው የተሃድሷውያን የትራንስፎርሜሽን እቅድ
መፈጸም ዋናውን መቆጣጠር የማይጠረጠር አስፈላጊ ነው ። ለሁሉም ከሁለቱም ቢሆን የሚደነቅ ቃል ጠባቂነት ነው ? አንዳንዴ ትክክል
የሆነ ብቻን ሳይሆን ሁሉንም ማድነቅ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም …. ነገር ግን ይህ ሃይማኖት ነው ቀልድ አይደለም ይመስላል እንጂ መጨረሻው
እንደ አቃጆቹ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው ። መቸም ለመልካም ነገር ለመንፈስ ቅዱስ ስራ የምርጫ ካርድ መፍትሔ እንዳልሆነ መነገር የሚያስፈልገው አይደለም ።
ደግሞ መቸነው ከእንቅልፌ ብድግ ስል ስለ ግብጹ የሙስሊም ብራዘር ሁድና ማህበረ ቅዱሳን የተጻፈ ጽሁፍ ፌስ ቡክ አካውንቴ
ላይ ተለቆ አገኘሁት ። ይህ ነገር እንዴ ነው ? ጹሁፉ ከ ሰማይ ቤት ነው ? ብየ አሰብኩ ያለፈው የፓርላማ አስቂኝ ንግግር ትዝ ቢለኝ /ድንገት ዳግም ትዝብሏቸው
በመንፈሳቸው በኩል ተናግረውት ከሆነ ብየ ነው/ ምን አልባት ደግሞ
ራእያቸውን ለማሳካት የሚታገሉት ትጉ አገልጋዮች ለክ እንደ ገደል
ማሚቶ አስተጋብተውት ከሆነስ ??? እኔ እንጃ ብቻ እያሰብኩ ማፈንጠርያውን /link/ ከፈትኩት ከፍቸ ሳየው ለካ እነእንቶኔ ናቸው እነርሱ እንኳ ግራ የገባቸው በኦርቶዶከስ ማሊያ ለነ ማርቲን ሉተር የሚጫወቱት
እሰይ አወቃችኋቸው ? ከዚያውላችሁ እኔም ተረጋጋሁ ። “እሰይ ኤፍሬም
እሸቴ አረፈ” አልኩ ደግሞ ዳግም እርሱ የጠቅላይ ሚንስትሩ መንፈስ
ባለው አልስማማም ብሎ ከመጻፍ ስንት ነገር የሚሰራበትን ሰዓቱን ከማባከን ተረፈ። / ለነዚህ የጥቃቅን ጥቃቅኖች እኛ ጥቃቅኖች እንበቃለን ብየ ነው / ።