«የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም» ነህ.
10፡39
እየተሰራ ያለው ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን |
"ኑ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ" መ.ነህ 2:20:: ቦታው ከአ.አ 210 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘዋ ላፍቶ ሌንቃ የምትባል የገጠር ከተማ ሲደርሱ ወደ ቀኝ የሚገነጠለውን እና ወደ ስልጤ ዞን እና ቄልጦ ከተማ የሚወስደውን ኮረኮንቻማ የገጠር መንገድ ይዘው ሲጓዙ በግምት ከ4-5 ኪ.ሜ በኋላ ያገኙታል፡፡ ታሪክ ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተበትን ዘመን በእርግጠኝነት ለማወቅ እና እና ለመናገር የሚያስችል በቂ መረጃ የሌለ ቢሆንም በጣም ብዙ የሆኑ ዘመናትን እንዳስቆጠረ የሀገር ሽማግሌዎች የተናገሩ እና በአካባቢው ላይ ያሉ የጥንት አባቶች ሲጠቀሙበት የነበሩ ዋሻዎች በውስጣቸውም የተገኘው የመስቀል ምልክት እና ፅሁፍ ምስክር ሲሆኑ በይበልጥ ግን ጥናት እና ምርምር ሊደረግበት የሚገባው ነገር ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ
ይህ ቤተክርስቲያን አሁን ያለበት ሁኔታ እስከ ዛሬ ካየነው ከሠማነው ሁሉ የሚለይ እና እጅግ የሚያሳዝን ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች ቦታዎች ቢያንስ የሚያፈሱ ያረጁ በመቃብር ቤት ያሉ…. ብቻ የሆነ ትንሽ ነገር ያላቸው ናቸው፡፡ እዚህ ግን ምንም የለም እንደ ቤተክርስቲያን የሚያገለግለው ዋርካ/ዛፍ/ ሲሆን ከስሩ ስዕለ መድኃኔዓለምን በማስቀመጥ ይጠቀሙበታል፡፡