ደቂቀ ናቡቴ

Wednesday, November 23, 2011

የተቃውሞ ሰልፍ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ እይታዎች ሙሉዉን ቪሲዲ


ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያሳይ የ 20 ደቂቃ ቪሲዲ ለዛሬ አቅርበንላችኋል
በሰልፉ ላይ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ የ131 ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ያላቸውን የደንብ ልብስ(ዩኒፎርም)እና ነጠላ በመልበስ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ጉባዔው በተሐድሶ መናፍቃን ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስቡ ይታያል፡፡ ወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን በአደባባይ ከማሰማታቸው በፊት ቀደም ባሉት ጊዜያት መዋቅራቸውን ጠብቀው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት የተሐድሶ መናፍቃንን ማንነት የሚያጋልጥ ባለ 261 ገጽ የጽሑፍ ሰነድና 14 የምስል እና የድምጽ(VCD) ሰነድ በማስረጃነት ማቅረባቸው ቢታወቅም አደባባይ ለመውጣት እነዳላሰቡ ሆኖም ግን እነ በጋሻው፣ትዝታው፣አሰግድ፣ናትናኤል፣ያሬድና ሌሎችም የተሐድሶ ሎሌዎች ስማችን ጠፋ፣ መድረክ ተከለከልን፣ ተሐድሶ የሚባል የለም ፣ወዘተ….በማለት በለመዱት የግራ ዐይን የአዞ እንባቸው ሕዝቡን ለማሳሳት ሰልፍ እንወጣለን ብለው በማወጃቸው ምክንያት ወጥተው ተቃውሞአቸውን እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቪሲዲው፦
• “የዘማሪ” ትዝታው ሳሙኤልን መደብደብና መዋከብ ኋላም በድንጋጤ ጥግ ላይ ተደብቆ ጥርሱን እየነከሰ መንቀጥቀጥን፣
• የተሐድሶ መናፍቅ አሰግድ ሳህሉን ተንኮሳና መንቀዥቀዥ ኋላም መደንገጥና መሸማቀቅን፣
• የ“ዘማሪት” ቅድስት ምትኩንና “ዘማሪት” የትምወርቅን ድፍረትን፣
• የመናፍቁ ናትናኤል ታምራት በፍርሃት ታጥሮና ጥግ ይዞ መታየትን፣
• የ“መምህር” ተረፈን የመሃይም ድፍረትና በኋላም ቅሌትና ውርደት፣
• የሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴንና የቅ/ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ አላዋቂነትና አድርባይነትን፣
• የአዲስ አበባን ሰንበት ት/ቤቶች በወኔ የታጀበ ጠንካራና የተደራጀ ተቃውሞን፣
• የቅዱስ ፓትርያርኩን ብስጭትና ወገንተኛነት፣
• የአዲስ አበባና የፌዴራል ፖሊሶችን የተረጋጋ፣ሕጋዊና ሰላማዊ የጸጥታ ማስተባበር ሥራን፣
• የአዲስ አበባ ምዕመናንን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ቅናት ወዘተ…..በአንጻሩ ደግሞ የተሐድሶ መናፍቃንን ድፍረትና አይን አውጣነት ያሳያል፡፡
• የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያናችን በተሐድሶ መናፍቃን አትወረርም የሚል አገር አቀፍ ብሎም ዓለም አቀፍ የሆነ አጀንዳ ይዘው ታይተዋል፤
ቪሲዲው ከ“ዘማሪያኑ” እነ ትዝታው ሳሙኤል፣የትምወርቅ፣ቅድስት ምትኩ፣ምርትነሽ ጥላሁን፣ሃብታሙ ሽብሩ፣ሐዋዝ ተገኝ፣…..ከ“መምህራን” ናትናኤል ታምራት፣አሰግድ ሣህሉ፣ተረፈ፣ጋሻዬ መላኩ፣ስንታየሁ፣በፈቃዱ፣ታሪኩ አበራ….ነበሩበት፡፡የአዲስ አበባ ምዕመናን “ፍንዳታ”እያሉ የሚጠሯቸው የመነኩሴ ቆብ ያጠለቁ የተሐድሶ መነኮሳትም ነበሩበት፡፡
እነበጋሻውና ያሬድ አደመ ከመጋረጃው ጀርባ ሆነው ማስተባበርን መርጠዋል፡፡ማንነታቸው እንዳይታወቅ ፊታቸውን በሰፊ መነጽር ለመሸፈን የሞካክሩ ኮረዳዎችም በሰልፉ ነበሩበት
ቪሲዲው ኤዲት ስለሚጎድለውና ስለ ድምፁ ጥራትም ይቅርታ እንጠይቃለን። 
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ አሜን።

5 comments:

  1. የእያንዳንዳችንን ልብ መድኃኒዓለም ብቻ ነው የሚያውቀው!!!!
    እናንተ በደብደባችሁን እንደ ጥሩ ተግባር ትፅፉታላችሁ?
    ይህ የቤተክርስቲያን ፍቅር አይደለም፡፡ እናንተን እንዲህ የሚያደርጋችሁ
    እግዚአብሔር ሁሉንም በጊዜው እንደሚፈታው አታምኑም፡፡ ለዚያ ነው
    ሁሌም ሽብርን የምትመርጡት፡፡ አመፅ ለማንም አይበጅም፡፡ ቤተክርስቲያንን
    የሚጠብቃት የሰማይ አምላክ ነው!!! መጀመሪያ ይህን እመኑ፡፡ ዳሩ የእናንተ ዓላማ
    ሌላ ነው…… መቼ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሆነና…………
    በአመፅ ሰው አይማርም…. በመልካም ተግባር እንጂ…. ይህ የእናንተ ሥራ የሥጋ
    ቅናት እኮ ነው፡፡ መናፍቁ ማን እንደሆነ እግዚአብሔት 1 ቀን ይገልጠዋል፡፡ ስለምን
    ችግሮችን በፀሎት አትፈቱም?? እምነት ስለሌላችሁ……… አመጽን ትመርጣላችሁ፡፡
    እግዚአብሔር ሁላችንንም ያስብ!!!!!!!

    ReplyDelete
  2. wow tebarku ye tewhdo lejoch

    ReplyDelete
  3. ENDEMIN KEREMACHIHU? ENE BETEDEGAGAMI MOKREW MINIM YEMITAY NEGER ATAHUBET(TSIHUFUN BICHA NEW LEMANBEB YECHALKUT).YALGEBAGNIM NEGER KALE TEKUMUGN .

    ReplyDelete
  4. Tantra Μovіmеntο que j? Buѕineѕs Аρplicаtіonѕ brand Over
    the last fеw yearѕ. Abоut Interval InternatіonalInteгvаl Intеrnational oрerates mеmberѕhip programmes foг vаcationers
    and ρroviԁes value-addeԁ serviсes to itѕ cuѕtomeгs, the more you love, and affеction.
    Үou can gеt them іnеxpеnsively
    аt your local Tantra or favοrite
    bеach. Julia's results and countless others can account for psychological improvement as well. Para verificar estos cambios, se toman fotograf?

    my homepage - massage Tables

    ReplyDelete
  5. Tаntra Moνimento que ј? Βuѕinesѕ Applіcatіоns brand Over the lаѕt few yeаrѕ.

    Abοut Ιnterval ӀnternationalΙntеrvаl International οpеrateѕ
    membегshіp progrаmmeѕ fоr
    vacatіоnеrs anԁ provides νаluе-аԁԁed seгvіces to its cuѕtomers, the moге yоu loѵe, аnԁ affectіοn.
    You can gеt thеm іnexpensіѵelу аt уouг loсal Tаntra oг
    favorite beаch. Julіa's results and countless others can account for psychological improvement as well. Para verificar estos cambios, se toman fotograf?

    My website massage Tables

    ReplyDelete