ደቂቀ ናቡቴ

Tuesday, February 14, 2012

ትውፊት


ትውፊት   የሚለው ቃል አወፈየ /ሰጠ/ ከሚለው የግእዝ ቃል /ግስ/ የተገኘ ቃል ሲሆን የተሰጠ /የተቀበሉት/ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያዊ ትውፊት ማለት ከሐዋርያት ጀምሮ በቃል፣ በጽሑፍና በተግባር ሲፈጸም በመመልከት ሲወርድ ሲዋረድ ከእኛ ዘንድ የደረሰ የቤተ ክርሰቲያን ትምህርት እና ሥርዓት ማለት ነው፡፡  ሐዋርያትና ሌሎቹ የጌታችን ደቀመዛሙርት ወንጌልን መጀመሪያ ያስተምሩ የነበሩት በቃል ነበር፡፡ በኋላ ግን ትምህርቱ እንዳይጠፋ በማለት በጽሑፍ ጽፈውታል፡፡ ከጻፏቸውም ነገሮች አብዛኞቹ ባለን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ያልተጻፉ ብዙ ነገር እንዳሉና፣ ከጽሑፋቸውም ውጪ በቃልና በተግባር ያስተማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ራሳቸው ጽፈዋል፡፡  «ጌታችን ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸው ነበር» /ዮሐ. 21.25/  «በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ» /2 ተሰ 2.15/ 
እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተተቱ የቃል፣ የጽሑፍና የተግባር ትምህርቶች ሲወርዱ ሲዋረዱ ከእኛ ዘንድ ደርሰዋል፡፡ እኛም ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከእውነተኛ ምንጭ ከጌታና ከሐዋርያት ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ አማኝነት የመጡ የተቀደሱ ውርሶች ስለሆኑ እንቀበላለን፤ እንመራባቸዋለን፡፡   


የቤተ ክርስቲያንን ስርአት እና ትውፊት አውቀን እንተገብረው ዘንድ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን ፡፡

1 comment: