ደቂቀ ናቡቴ

Monday, June 25, 2012

ለምን አልሰለምሁም? ክፍል አንድ ምስጢረ ሥላሴ


ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ሥላሴን አላስተማረም፣ የአምላክ ልጅም አይደለም፣ አምላክ ልጅ ነኝም አላለም እያሉ ዓለምን ለሚያወናብዱት ለነአሕመድ ዲዳት ማብራሪያ  

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በአካል አንድ ብቻ አልነበረም፡፡ በአካል በስም፣ በግብር ሦስት፣ በመለኮት፣ በባሕርይ በህልውና አንድ ሁኖ አንድ አምላክ እየተባለ ዘለዓለም ሲቀደስ ኑሯል፤ይኖራል፡፡
ሥላሴ በስም:- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡ በግብር አብ ይወልዳል፤ ያሠርጻል፤ ወልድ፤  ይወለዳል፤ መንፈስ ቅዱስ ይሠርጻል፡፡ በአካል አብም፤ ፍጹም አካል (ህልውና፤ ገጽ) አለው፤ እንደዚሁም ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ የተለየ ፍፁም አካላት አሏቸው። አካልና ሰውነትን  ያልተማሩ ሰዎች ያደባልቋቸዋል፤ አካል ሦስቱም፣አብ ወልድ ፡ መንፈስ ቅዱስ ለእየራሳቸው አሏቸው ሰውነት ግን የሚጨበጥ የሚዳሰስ ያለው ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይኽውም ሥጋ በመልበሱ፡፡ በምስጢረ ሥላሴ አካል ለቀዋሚ ነገር ለመንፈስ ነው የሚነገረው፤ አይታይም አይዳሰስም፤ መንፈስ ነው፡፡ አካል በምናውቃቸው በሌሎቹ ቋንቋዎች (ፕሮሶፓን ግሪክ፤ ፔርሶና ላቲን፤ ፔርሶን እንግሊዝ፣ ጣልያን ፈረንሳይ ነው፡፡ ሰውነት (በአልካ በሚዳሰስ ትርጉሙ)ሶማ ግሪክ፣ ቦዲእንገሊዘ፡ ኮርም ጣልያን፡ በፈረንሳይ በንባብ ኮር በአፃፃፍ ኮርጥስ፡ ላቲን ኮርፑስ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ ረቂቅ አካሉ ሥጋ ስለለበሰ። ሰውነት(የሚዳሰስ አካል) አለው የሚባለው፡፡ ባሕሪያቸው መለኮታቸው፣ መንግሥታቸው፣ ሥልጣናቸው ግን አንድ ነው፡፡ በአካል ሦስት ስለሆኑና በመለኮት፣ በባሕርይ አንድ ስለሆኑ፣ እኔ እያለ በነቢያት በክርስቶስ፣ በሐዋርያት፣ እግዚአብሔር ሲያናግር ኑሯል፡፡  
  1.  (ዮሐ. 1፡1-3) በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ይህ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ሁሉም በእሱ ሆነ፡፡ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም። ከዚህ ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ ጋራ ሌላ እግዚአብሔር ወልድ እንዳለ እና ያለእሱም ምንም  እንዳልሆነ ይናገራል፤ በአካል የተለያዩ በመለኮት ግን አንድ የሆኑ፤ ሁለት አካላት፤ አንድ እግዚአብሔር እንድ እግዚአብሔር እንዳለ  ወንጌላዊው ቁልጭ አድርጎ ገልጧል፤ ከዚህ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ አካላት አብና ወልድ ናቸው፣ ዝቅ ስንል ደግሞ ሦስት አካላት መሆናቸውን እናያለን፡፡ 
  2.    (ማቴ.3፡16-17) ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኋ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ወርዶ ከእሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም ድምፅ ከሰማይት ወጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡ በዚህም በአምሰላ ርግብ  የወረደው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፤ የምወደው ልጄ ያለ እግዚአብሔር አብ ፤ ተጠማቂው ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በትስብእቱ ዐማኑኤል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው፣በኋላ የቤተክርስቲያ ሊቃውንት ሥላሴ ብለው የሰየሟቸው አካላት፣ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡(ማር.1፡911፤ ሉቃ.3፡21-22) 
  3.   ይኽው ታሪክ በድብረ ታቦርም ተደግሟል፣ ያውም ከትእዛዝ ጋራ፣ (ማቴ.17፡1-6፤ማር.9፡2-13 ሉቃ.9.28-36)"እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት፡፡"፥ 
  4.  (ዮሐ.11፡4) ኢየሱስም ሰምቶ፣ ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ፡፡ 
  5.    (ዮሐ.11፡-፡27) አዎ!ጌታ ሆይ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ቁርአንና እስላሞች እንደሚሉት አምላክ ባይሆን ኑሮ፣ አይደለሁም  ተሳስተሸል፣ እኔ አምላክ አይደለሁም ይላት ነበር፡፡ 
  6.    (ዮሐ12፡45)  " እኔን ያየ የላከኝን አየ፡፡" ከዚህም ላኪና ተላኪ ሁለት አካል መኖራቸውን ይናገራል፡፡
  7.   (ዮሐ13፡3) ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደመጣ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ዐውቆ ከእራት ተነሥቶ ልብሱን አኖረ፡፡ 
  8.    (ዮሐ14፡1) ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔርም እመኑ፣ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ---፡፡ 
  9.   ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት፣ ሕይወትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡ እኔንስ ብታወቁኝ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፡፡ 
  10. (ዮሐ14፡15-17) ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ፡፡ እኔም አብን እለምነውዋለሁ፣ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላውን አጽናኝ እንዲሰጣቸሁ። እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ሰላሆነ ሊቀበለው የማይችል የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ከእናንተ ዘንድ በውስጣችሁም ስለሚኖርታውቁታላችሁ፡፡ በዚህም ሦስት መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አብን እለምነዋለሁ፤ መንፈስ ቅዱስ ይልክላችኋል ብሎ ፣ሦስቱንም፤ ተለማኝ ፣ ለማኝ ፣ተላኪ አድርጎ ሦስቱን አካላት ዘርዝሯል፡፡ 
  11.  (ዮሐ14፡23-24) ኢየሱስም መልሶ አለው፣ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፣ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን፡፡ የማይወደኝም ቃሌን አይጠብቅም (እንደአይሁድና እንደ አሕመድ ዲዳት ያለው)፡፡ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እጂ የኔ አይደለም፡፡
  12. (ዮሐ14፡25) ከእናንተ ጋራ ስኖር ይህን ነገርኋችሁ፣ አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፣እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያስተውሳችኋል፡፡ 
  13. (ዮሐ14፡31) ነገር ግን እኔ አብን እንደምወደው ዓለም ያውቅ ዘንድ አብ ያዘዘኝን ሁሉ እፈጽማለሁ፡፡ 
  14.   (ዮሐ.15፡9) አብ እኔን እንደ ወደደኝ እኔም እናነተን ወደድኋችሁ፡፡ (15) አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፡፡ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለነገርኋችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፡፡
  15.   (ዮሐ.15:21) የላከኝን ስለማያውቁ በእኔ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል፡፡ 
  16.  (ዮሐ.15:23) እኔን የጠላ አባቴንም ይጠላል፡፡ (ዮሐ.15:26) ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ የምልከላችሁ የእውነት መንፈስ፣ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ፣ ስለኔ የመሰክራል፡፡ እናተም ከመጀመሪያ ጀምሮ ከኔ ጋራ አብራችሁ ስነበራችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡
  17. (ዮሐ.16፡1-3) ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይህንም የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ሰለማያውቁ ነው፡፡
  18.  (ዮሐ.16:7-8) እኔ ግን እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፣ ምክንያቱም እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ (ጰራቅሊጦስ፣ መንፈስ ቅዱስ) ወደእናንተ አይመጣም፣ እኔ ከሄድሁ ግን ወደ እናንተ እልከዋለሁ፡፡ እርሱ በመጣ ጊዜ ስለ ኅጢአት፣ ስለፍርድና ስለጽድቅም ሰዎችን ያስረዳል፡፡ 
  19.   (ዮሐ.16:12-15) ገና የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ይከብዳችኋል፡፡ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ የመራችኋል፤ምክንያቱም እሱ የሚናገረወ የሰማውን እንጂ የራሱን አይደለምና ነው፡፡ እርሱ ወደ ፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግችኋል፤ የኔ ከሆነው ወስዶ ስለሚነግራችሁ ፣ እኔን ያከብረኛል፡፡---፡፡ 
  20.   (ዮሐ.16:28) ከአብ ዘንድ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፣ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳሁ፡፡----፡፡ (ዮሐ.16:30) አንተ ሁሉን እንደ ምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማትፈልግ አሁን ዐወቅን፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፡፡ 
  21.  (ዮሐ.16:32፡-፤) ነገር ግን አብ ከኔ ጋራ ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም፡፡ 
  22.   በጠቅላላ አባትና ልጅ መሆናቸውን ለማወቅ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ዐሥራ ሰባትን ያነቧል፡፡ 
  23.  (ዮሐ.19፡7) አይሁድም እኛ ሕግ አለን፣ ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ስላደረገ በሕጋችን መሠረት ሞት ይገባዋል አሉ፡፡  
  24.  (ዮሐ.10፡30) እኔና አብ አንድ ነን፡፡

እነ አሕመድ ዲዳት ኢየሱስ አምላክ ነኝ፣ የአምላክ ልጅ ነኝ  አላለም፣ እነ ጳውሎስ ለከኩበት ስላሉ፣ ለመልስ ያህል የዚህ በላዩን ጠቅሰን እንጂ መላ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር ስለአባትና ልጁ ነው፡፡ዓለምም የሚድነው በእየቦታው እንደገለጥነው ኦሪትና ነቢያት ፍርጥርጥ አድርገው ተንቢተዋል፣ እየሱስም አስተምሮአል፣ ሐዋርያትም ሰብከዋል፡፡ ገርብተዋል፣ ቀልብሰዋል፤ርግጥ ነው፣  ሥጋ በመልበሱ፣ ሥጋ ለብሶ ዓለምን ለማዳን ከኃጢአት በቀረ ሰው የሠራውን ሁሉ ሠርቷል፣ እህል በልቷል፣ውሃ ጠጥቷል፣ ጥቂት በጥቂት አድርጓል፤ ተርቧል፣ ተጠምቷል፣ በሥጋው ሰው የሆነ አምላክ የማርያም ልጅነውና፡፡ አሁንም በሥጋው ሰው ስለሆነ፣ ተገፏል፣ ተስቅሏል፣ ሙቷል በመለከቱ ሥጋውን ይዞ ያላንዳች ረዳት መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ተነሥቷል፣ ተነሥቶም ወደ ሰማይ በክብር ዐርጎ በአባቱ ቀኝ በሥልጣን በክብር ተቀምጧል፡፡
እርግጥ ከመለኮቱ ከመዋሐዱ በፊት ሥጋውን የፈጠረ በመንፈስ ቅዱስ ወልድ እንዲዋሐደው ያደረገ፣ ያመቻቸ እግዚአብሔር አብ በሦስትነቱ ነው፤ ስለዚህም አባቴም (በመለኮቱ) አምላኪየም በትስብእቱ ይለዋል፡፡ አባቱም ልጄ ይለዋል፣ መለኮቱን ሲያይ፡፡ ሐዋርያትም የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ  እግዚአብሔር አብ እያሉ ያስተማሩ ስለዚህ ነው፡፡(ዮሐ.20፡17፤2ቆሮ.1፡3፤ኤፌ.1፡3፤ጴጥ.1፡3፤17) እሱም ራሱ እንደ መለኮት ሲያሰብ አባቴ እንደ ሰውነቱ ሲያሰብ አምላኪየ  ሲል ኑሯል፡፡ አስተምሯል፡፡
ይህ ሁሉ ምስክር እያለ ነው እንዲዳት ፣ ኢየሱስ አምላክ ወይም የአምላክ ልጅ አይደለም የሚሉት፡፡
እስከዚህ የአብን አባትነትና የወልድን ልጅነት፣ የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነት በሐዲስና በብሉይ ከገለጥን በቁርአን ደግሞ እንዴት እንደሆኑ እንይ፡፡

ሥላሴ በቁርአን
(ሱራህ 4፡171) እናንተ የመጽሐፍ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰነን አትለፉ፣ በአላህም ላይ ከእውነት ሌላ አትናገሩ የማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መልእክተኛና ቃሉም ነው፤ ከእሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡
እኛስ ምን እንላለን? ቃለ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር  ቃል ከማለት በቀር፡፡ ለእነ ዲዳት የእግዚአብሔር ልጅ ስንል በወሲብ የወለደው ነው የምንል ይመስላችዋል፡፡ ከዚህ ላይ በቁርአኑ እንደተገለጠው በአንድበቱ የሚወጣ ቃሉ እንጂ ከማርያም በወሲብ የወለደው የሚል ጤነኛ ክርስቲያን የለም፡፡ ለምን? ቢሉ እግዚአብሔር አብ መለኮት መንፈስ እንጂ ሥጋዊ አይደለም፡፡ ሥጋ የለውምና፣ ትስብእትን የተጎናጸፈ ሰው አይደለም፣ ቀጥሎም እሱም ወደ ማርያም አንድ መንፈስ አምጥቷል አለ፤ ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ ፤ ትስብእትን የተጎናጸፈ ሰው አይደለምና፣ ቀጥሎም እሱም ወደ ማርያም አንድ መንፈስ አምጥቷል አለ፤ ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ፤በዚህም መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ በከርሠ ድንግል ማደሩን ይናገራል፡፡ (ሱራህ፡19፡34) የማርያም ልጅ ኢየሱስ በእሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃሉ ነው፡፡ ማስተዋል የለ፣ የነአሕመድ ነገር፣ እኛስ እውነተኛ ቃል እግዚአብሔር ነው እንላላን እንጂ ምን እንላለን? ከዚህ አስቀድሞም በሉቃስ ወንጌል (4፡18-20) የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኆች እንዳበስር ሹሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታተን፣ ለታወሩት ማየትን እንዳውጅና የተጨቁኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ምዕራፍ ፡19፡30፡ ሕፃኑም አለ፤ እኔ የእግዚአብሔር ባርያ ነኝ(በሥጋው) መጽሐፍን ሰጥቶኛል፣ ነቢይም አድርጎኛል፡፡ በየትም ስፍራ ቢሆን ቡሩክ አድርጎኛል፡፡ ለእናቴም ታዛዥ አድረጎኛል፤ ትዕቢተኛና  እምቢተኛም አላደረገኝም፡፡---፡፡በመንፈስ እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች በምን ይለያያሉ? ዓለምን ለማዳን በትሕትና የመጣው የወልደ እግዚአብሔር ቃላት ናቸው፡፡ ምስጢረ ሥላሴን ወስኖ አሰተምሮት የዐረገ ክርስቶስ ነው፡፡ እነ ዲዳት ግን በአራተኛው መቶ ዘመን በ325 በኒቅያ ነው የተወሰነው ይላሉ፤ ተሳስተዋል፣ ለምን ቢሉ? ከጰራቅሊጦስ አንሥቶ እስከ ዘመነ ቆስጠንጢኖስ ያለው ዘመን ለክርሲቲያን ዘመነ ሰማዕት፣ ዘመነ ስደት ይባላል፤ በዚህ ዘመን ክርስቲያኖች እንደልባቸው ለመገናኘትና ተገናኝተውም እንደልባቸው ለመናገር ስላልቻሉ፣ በቀላሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ሁሉ ክርስቲያን ይባል ነበር፤ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ግን መጻሕፍት ተጠንተው፣ምስጢራት በቅዱሳት መጽሐፍት ተመርምረው ተወስስኑ፤ መናፍቃንም ተወገዙ፣ ኢምሁራንም ተማሩ፡፡
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
ይቆየን የቀጥላል
በተከታታይ በክፍል በክፍል የምናቀርብላችሁ ይኖራል ተከታተሉን
ምንጭ ለምን አልሰለምሁም ገፅ 11-15

3 comments:

  1. i tried to read ur document its better to give answers for such things from our churches point of view. from what i tried to read let me give ma comment i failed to read above the two lines bcus this is a preaching on divinity so in such case we need to take care for each word not to made a mistake but i can say it is posted without any editing so this needs greater care. and the picture of Holy trinity in ma opinion is wrong which is in contradiction with what u r talking about so pls give greater care before posting any spritual things.

    ReplyDelete
  2. አኔ ያልገባኝ ምስሉ ኦርቶዶክሳዊ ነዉ አንዴ ? አስቡበት

    ReplyDelete
  3. bewunetu kale hiwot yasemaln ketaun entebikalen

    ReplyDelete