ደቂቀ ናቡቴ

Wednesday, August 15, 2012

ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ የሚጠራውን ቡድን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አገደ


በጠቅላይ ቤተ ክህነት አካባቢ ራሱንጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶብሎ የሰየመውን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት የእገዳ ደብዳቤ ጣለበት፡፡ የጉባኤው መስራቾች ነን ባዮች እነ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ፡ ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል ፡ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን እና ሌሎች 27 የሚሆኑ ሲሆ ጉባኤውን እያደራጁ የሚገኙ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት እያጡ የመጡ ግለሰቦች እንደሆኑ ለመረዳት ችለናል::   


የቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት የጉባኤው ዓላማና ፍላጎት ምን እንደሆነ እንደማይታወቅና እንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖደስ ካለመቋቋሙም በላይ እውቅና ሳያገኝና ሳይፈቀድለት በራሱ ተነሳሽነት የሚንቀሳቀስ በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ /ቤትም የማያውቀውና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት ዋና ጸሓፊና የከፋ ሸካ ቤንች እና ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፊርማ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ቤት በቁጥር 486/836/2004 ሐምሌ 25 ቀን 2004 .. በተጻፈው ደብዳቤ መታገዱ ተገልጿል፡፡

ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶቡድኑ በምን ምክንያት እንደተቋቋመና ለምንስ በኅቡዕ መንቀሳቀስ እንደፈለገ ምንም መረጃ ያልተገኘ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስም እነዚህ ግለሰቦች ሊፈጥሩት ካሰቡት ከፍተኛ አደጋ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊታደጋት እንደሚገባና በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ሆነው የዚህን ሕገ ወጥ ቡድን አባላት በሆኑ ግለሰቦች ላይ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ርምጃዎች ሊወስደ እንደሚችል እየተገለጸ ነው፡፡

የዚህ የእገዳ ደብዳቤ ግልባጭ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ልዩ /ቤት፣ ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሃይማኖትና ሥነ ሥርዐት ዳይሬክቶሬት ጀኔራል፣ ለብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት፣ እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ግልባጭ የተደረገ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡መረጃዎቹን ያገኘነው ምንጭ፡-ማህበረ ቅዱሳን
 ቸር አምላክ ከቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ ጠላቶች የሰውረን አሜን

4 comments:

  1. Also it makes no difference which type you make use of the only thing which needs to be
    taken good care of over here is the fact that, you must make certain
    you are going for a proper good care of your body at the
    same time. A baby's immune system is just not as developed as a possible adult's immune
    system and cannot as effectively eliminate toxic pesticides.



    my page - best baby swing reviews (http://sanluisjilotepeque.xp3.biz/)

    ReplyDelete
  2. Another advantage of Bowen therapy is you will find virtually
    no contra-indications. I have to tell you that I sympathize with how
    my patients are feeling and congratulate them
    for seeing a physician.

    Feel free to visit my web site :: Quick Plans In inversion table For 2012

    ReplyDelete
  3. A: First of, it's completely normal being jealous of the wife's
    relationship using your new baby-in particular when she's breastfeeding. Bratt Decor is one from the thousand distributors of comfortable and convenient cribs.

    Take a look at my web-site - best rated baby swing

    ReplyDelete
  4. Generally I don't read article on blogs, but I would like to say
    that this write-up very compelled me to try and do so! Your writing style has been surprised me.
    Thanks, very great post.

    Feel free to surf to my page; Beats By Dre Headphones

    ReplyDelete