ደቂቀ ናቡቴ

Friday, October 5, 2012

“ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡”



እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋ፡፡ መዝ.96፡10
እንኳን ለቅዱስ ዮሴፍ (የእመቤታችን ጠባቂ)፣ እና ለታላቁ ጸድቅ ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም ወርሃዊ ክብረ በዓል  በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ አሜን፡፡
ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር አብ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር  ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ስለ አባቴ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም እንድጽፍ ስላነሳሳኸኝ  ክብርና ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባሃል አሜን፡፡
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተ ማርያም ከተከበሩና ህገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በትሩፋት ከሚተጉ በንጽህናና በቅድስና ይኖሩ ከነበሩ አባታቸው ፍሬ ብሩክና እናታቸው ዮስቴና ከተባሉ በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ተወለዱ፡፡ እናታቸው የምናኔ ሀሳብ ለመፈጸም በአንድ ገዳም በሄዱበት ወቅት አንድ መነኩሴ መንኩስና ላንቺ አልተፈቀደም ወደ ቤቴሽ ሂጂ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ፣ ቱሩፋቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም በአጸደ ሥጋ በአጸደ ነፍስ የሚያማልድ ምድርም ሆነ መንበረ ጸባዖትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ባሏቸው መሠረት የተወለዱና በእናታቸው ጀርባ ታዝለው ካህኑ በቤክርስቲያን “እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ” ሲሉ በሕፃንነት አንደበታቸው “እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ” ይሉ ነበር፡፡ ካደጉ በዃላ ትምህርታቸውን ከጥሩ ስነምግባርና ሕግን ከመጠበቅ ጠንቅቀው ከመማር ባሻገር በአባ ሳሙኤል እጅ ምንኩስናን ተቀበሉ፡፡ አቡነ መልክአ ጼዴቅ ገዳም ተነስቶ ሲሄዱ መንገድ ላይ በአንድ ዋሻ ውስጥ ለሦስት ወራት ቆይተዋል፡፡ እግዚአብሔር… “መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርገዋለሁ” ብሎ ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡ ይህም ዋሻ የይሰበይ  አባ ሀብተ ማርያም ገዳም በመባል በሰሜን ሸዋ ሰላሌ አህጉረ ስብከት ከደብረሊባኖስ ወደ ቆላው ዝቅ ብሎ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙንም በስማቸው መሠረቱ፡፡ አባታችን ጽንሰታቸው ነሀሴ 26 ልደታቸው ግንቦት 26፣በዓለ ዕረፍታቸው ደግሞ ህዳር 26 ቀን ነው፡፡  “ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡” መዝሙር 111/112፡6  (“የጸድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል፡፡” መዝሙር 111/112፡6)
ሰላም ለጽንሰትከ፡-
+++++ምግባሩ የተወደደ የሆነ የጸድቁ ባህታዊ ብስራት የተጸነስክበት የእናት የዮስቴና ማህጸን በእውነት ሰላምታ ይገባል፡፡ ጻድቁ አባቴ ሆይ ሀብተማርያም እንደዮና ልጅ እንደ ጴጥሮስ የእውነት ሥራን አስተምረኝ አይነ ልቦናዬንም አብራልኝ ፍጽምት ከሆነች ትህትና ጋር ባልንጀራኤን እንደራሴ እወድ ዘንድ፡፡
ሰላም ለዝክረ ስምክ፡- በዃለኛው ዘመን የዚህን ዓለም ረሃብና ጥም የሚያስረሳና ከወይን ዘለላ ይልቅ ለሚወደድ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡+++++
ታላቁ  ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ ቢህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡ ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታች እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ  ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአባታቸው ጎን እንደ ተኙ በድንገት እግዚአብሔር በድምጽ “ሀብተማርያም ሆይ! አንተን የተመረጠ ዕቃ አድርጌሃለሁና ቃሌን ለተመረጡ ሰዎች ተናገር” አላቸው፡፡ ይህን ግን የተበሰረላቸው የቤተሰቦቻቸውን ከብቶች በሚጠብቁበት ጊዜ ነበር፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ አባታቸው ትምህርት ቤት አስገቡአቸው፡፡ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡
“ልጄ ሆይ እራስህን  ለእግዚአብሔር ታስገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህ ለመከራ አዘጋጅ፡፡” መጽሐፈ ሲራክ 2፡1   
በዚያን አባ ሳሙኤል ለሚባሉ በረዳትነት ሲያገለግሉብዙ ገቢረ ተዓምራት ተደርጎላቸዋል፡፡ ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው  ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሳባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡ በ 490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው፡፡ ምንጭ ነገረ ቅዱሳን፣መልክአ አቡነ ሀብተማርያም እና ሐመር መጽሔት 4ኛ ዓመት ቁጥር 3 የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡፡
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር  በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡
በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡
በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡
በሰማዕትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን  ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡
 “ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፤ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥  በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ፤ ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ፤ የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።”  መዝ. ፻፵፰/፻፵፱:-
o   “ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡”
(አባ እንጦስ)
 ·         “ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል” (ቅዱስ አትናቴዎስ)
           
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

6 comments:

  1. “ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡”
    (አባ እንጦስ)

    ReplyDelete
  2. “ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል” (ቅዱስ አትናቴዎስ)

    ReplyDelete
  3. ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡

    ReplyDelete
  4. ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡

    ReplyDelete
  5. een webwinkel beginnen webshops

    Here is my homepage ... Nuwebwinkelbeginnen.Nl

    ReplyDelete
  6. When I initially commented I appear to have clicked the -Notify me when new comments are added- checkbox and from now on each time a comment is added I receive four emails with the exact same comment.
    Perhaps there is a means you are able to remove me from that service?
    Appreciate it!

    Feel free to surf to my web-site; digital clock gadget windows 7

    ReplyDelete