ደቂቀ ናቡቴ

Friday, January 4, 2013

የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም

«የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም» ነህ. 1039 

እየተሰራ ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
 ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሁኔታ በአጭሩ(ሜሮን) 
" የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ" .ነህ 2:20::  ቦታው ከአ. 210 . ርቀት ላይ ከምትገኘዋ ላፍቶ ሌንቃ የምትባል የገጠር ከተማ ሲደርሱ ወደ ቀኝ የሚገነጠለውን እና ወደ ስልጤ ዞን እና ቄልጦ ከተማ የሚወስደውን ኮረኮንቻማ የገጠር መንገድ ይዘው ሲጓዙ በግምት 4-5 . በኋላ ያገኙታል፡፡ ታሪክ ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተበትን ዘመን በእርግጠኝነት ለማወቅ እና እና ለመናገር የሚያስችል በቂ መረጃ የሌለ ቢሆንም በጣም ብዙ የሆኑ ዘመናትን እንዳስቆጠረ የሀገር ሽማግሌዎች የተናገሩ እና በአካባቢው ላይ ያሉ የጥንት አባቶች ሲጠቀሙበት የነበሩ ዋሻዎች በውስጣቸውም የተገኘው የመስቀል ምልክት እና ፅሁፍ ምስክር ሲሆኑ በይበልጥ ግን ጥናት እና ምርምር ሊደረግበት የሚገባው ነገር ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ይህ ቤተክርስቲያን አሁን ያለበት ሁኔታ እስከ ዛሬ ካየነው ከሠማነው ሁሉ የሚለይ እና እጅግ የሚያሳዝን ሁኔታ ነው፡፡ ሌሎች ቦታዎች ቢያንስ የሚያፈሱ ያረጁ በመቃብር ቤት ያሉ. ብቻ የሆነ ትንሽ ነገር ያላቸው ናቸው፡፡ እዚህ ግን ምንም የለም እንደ ቤተክርስቲያን የሚያገለግለው ዋርካ/ዛፍ/ ሲሆን ከስሩ ስዕለ መድኃኔዓለምን በማስቀመጥ ይጠቀሙበታል፡፡
በፊት የነበረው ቤተክርስቲያን በተለያየ ጊዜ የተነሱ አፅራረ ቤተክርስቲያን 3 ጊዜ ያፈረሱት ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ 1971 . ከዛሬ 32 ዓመታት በፊት በአህዛብ የተቃጠለ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ለዚህን ያህል ዓመታት ሙሉ በአካባቢው ያሉት 7 ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን አግኝተው/አይተው/አያውቁም ነገር ግን ሃይማኖታችንን አንክድም ማተባችንን አንበጥስም በማለት ያለ መምህር በመፅናት ለብዙዎች አርአያ ለመሆን የሚችሉ ዕንቊ የቤተክርስቲያን ልጆች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ እነዚህ ምእመናን 32 ዓመታት ያሳለፉትን ጭንቅ /መከራ/ ተናግሮ መጨረስ የማይቻል በሰው አእምሮ የማይገመት አሰቃቂ ለመግለፅም የሚከብድ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ አንሰጥም በማለታቸው ምክንያት 4 ጊዜ በላይ ታስረዋል ተገርፈዋል መከራም ደርሶባቸዋል፡፡ ልጅ ወልደው ክርስትና ማስነሳት ንስሀ መግባት ማስቀደስ. የማይታሰቡ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰው ሲሞት እንኳ ጸሎተ ፍትሀት ሳይደረግለት ዝም ብለው ቤተክርስቲያኑ የተቃጠለበት ቦታ አምጥተው ይቀብሩታል፡፡ አስከ አሁንም ድረስ የልጅነት ጥምቀት ያልተጠመቁ ህፃናት እና ወጣቶች ያሉ ሲሆን አንገታቸው ላይ ማህተብ በማሰር እኔ ክርስቲያን ነኝ በማለት በአህዛብ መካከል ይመሰክራሉ፡፡ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በእለተ ሰንበት ተኝቶ አያረፍድም ወንዱም ሴቱም ህፃናቱም ትልልቆቹም ነጠላቸውን አጣፍተው ጋቢያቸውን አደግድገው ቤተክርስቲያኑ የተቃጠለበት ቦታ የምትገኝ አንድ ዛፍ ስር የመድኃኔዓለምን ስዕል በማኖር/በማስቀመጥ/ ይሰግዳሉ ይማፀናሉ፣ይለምናሉ ሥርዓተ አምልኮታቸውንም ይፈፅማሉ፡፡ ወር በገባ 27 የመድኃኔዓለም ዕለት ተራ ይዘው ዳቦ በመጋገር ጠላ በመጥመቅ / ጠበል ፀዲቅ በማዘጋጀት/ መድኃኔዓለምን ይዘክራሉ፡፡ በአጠቃላይ በአህዛብ ተከበው ሃይማኖትን በማፅናት አስደናቂ ተጋድሎ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡ 

ተአምራት፡- በቦታው ላይ የተገለጡት ብዙ ተአምራት ቢሆኑም ለጊዜው ጥቂቶቹ
 1. ቤተክርስቲያኑን ያቃጠሉት 2 ወንድ እና 1 ሴት አህዛብ ሲሆኑ፡- ሴቲቱ እሳት በእንስራ ደብቃ ይዛ በመምጣት ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ይጠብg ለነበሩ 2 ወንዶች በመስጠት ተባብረው ካቃጠሉት በኋላ በተለያየ ወር የመድኃኔዓለም እለት 2ቱም ወንዶች በመብረቅ የተቀጡ /የሞቱ/ መሆናቸው፡፡ሴቲቱም ከብቶችዋ በሙሉ በመብረቅ ማለቃቸው፤
2. ቤተክርስቲያኑ ሲቃጠል የነበሩ አገልጋይ መልሶ ለማሰራት የተሰበሰበውን ብዙ ገንዘብ በእጃቸው አድርገው ከአገልጋያቸው ጭምር ወደ እስልምና በገቡ በእለቱ አይነስውር መሆናቸው አገልጋዩም ሽባ መሆኑ እና እስከዛሬ በህይወት መኖራቸው፤
3. ቤተክርስቲያኑ በተቃጠለበት ቦታ እና አፀዶች መካከል ዝማሬ ቃጭልና እና ከበሮ የሚሰማ ዕጣን /ማዕጠንት/ የሚሸት መሆኑ
4. ጥንታውያን ዋሻዎች /ሰው የሚገባባቸው እና የማይገባባቸው/ሲኖሩ በድፍረት የገቡት አንደበተ-ዲዳ፤ዓይነ-ስውር መሆን እና በእሳት እየተቃጠሉ መውጣት በተጨማሪም ዝማሬ ቅዳሴ ወዘተ በዋሻዎቹ ውስጥ መሰማት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በተጨማሪም በተለያዩ ቅዱሳት/ቅዱሳን/ ስም የተሰየሙ ፍል/ሙቅ/ጠበሎች ያሉ ሲሆን ህዝብም አህዛብም እየተጠቀሙባቸው በመፈወስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀጣይ ተግባር፡- በሀዲያ እና ስልጢ ሀገረ ስብከት ውስጥ ያሉትን ችግሮች እና በምእመናኑም ላይ የሚደርሰውን መከራ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለማስወገድ በማሰብ የቤተክርስቲያን ልጆች በመሰባሰብ እና በመምከር ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመነጋገር አብሮ በመስራት እና እውቅና በመውሰድ በመጀመሪያ ደረጃ የላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን በተገቢው ሁኔታ እና በአጭር ጊዜ ለማቋቋም፤ በቀጣይነት ደግሞ ሀገረ ስብከቱን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ያሉትን ችግሮች ለዘለቄታው ለመቅረፍ እና ለማስወገድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር ማኅበር ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የቤተክርስቲያን ነገር የሚያሳስበው አካል ማኅበራትም ሆኑ ምእመናን ከዚህ የባሰ ሁኔታ ስለሌለ በኅብረት ሆነን አስቸኳይ እና ዘለቄታዊ መፍትሄ እንድንሰጥ ሁላችንም የምንችለውን ሁሉ እና የሚጠበቅብንን እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡  50 ሎሚ 1 ሰው ሸክሙ ነው 50 ሰዎች ግን ጌጥ ነው እንርዳዳ ይህችን ቤተክርስትያን እንጨርስ ከእግዚያአብሔር ጋራ
ህንፃ ቤተክርስቲያኑ እየተሰራ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ በተቸላችሁ መርዳት ይቻላል..ኑ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ .ነህ 2:20ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር  Commercial Bank of Ethiopia, Bomb Tera Branch. Account no. 1000017080249 mobile +251911143653, +251911780816, +251910016008 ክብር ምስጋና ለመድሓኔአለም ይሁን፡፡ለፍፃሜው አድርሶ የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን ያብቃን፡፡በርቱ እመቤቴ ከነልጅዋ ትርዳችሁ ትርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!
 

7 comments:

  1. Your way of explaining all in this article is genuinely fastidious, all
    can easily know it, Thanks a lot.
    Also see my webpage > How to win at roulette

    ReplyDelete
  2. WΟW just what I was searching for. Came herе
    by searching fοr shaгing
    My weblog ... drop leaf dining table

    ReplyDelete
  3. Can уou tell us more about this? I'd like to find out some additional information.
    My site > http://vitiligorescue.com

    ReplyDelete
  4. Stunning stoгy there. Whаt ocсurreԁ
    after? Gooԁ luck!
    Here is my webpage ... fort max diet

    ReplyDelete
  5. Hey there, I think your sitе might be hаνing browѕer cοmpatibility issues.
    When Ι loоk at your blog sіtе іn Ie, it loоks
    fine but ωhen openіng in Inteгnet Exploreг, it hаs some oνеrlaρріng.
    I just wanted to give you a quicκ heads up! Οther
    then that, wonderful blog!
    Visit my web blog : part time income

    ReplyDelete
  6. Can I just say what a relief to uncover an individual
    who genuinely knows what they are discussing on the web.

    You definitely know how to bring a problem to light and make it important.
    A lot more people have to read this and understand this side
    of your story. I was surprised you are not more popular since you definitely have
    the gift.
    Have a look at my homepage :: how to increase Breast size

    ReplyDelete
  7. The reactionѕ hereafter deѕcribed ceаse as soon as уou get your skin glowing and the
    bodу. Nirvіkаlpа Samadhі
    ensues now and the New York City, UЅA - On May 21 & 22, аround 250
    leadeгs of the Τаntгa pгices?
    Wi tantra is located in Grindavik, Iсelаnԁ, and
    while thіs particular tгeatmеnt may sеem fairly nouveau, it has a ԁeciԁedly high-еnd feel.
    Τhеrе are no ѕpeciаl trіcks.
    An excitement that is sharеd by the camera is unrelеnting.


    Visit my homepagе: lomi lomi

    ReplyDelete