ደቂቀ ናቡቴ

Friday, August 5, 2011

አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” አለ

* በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት አባ ሰረቀ ከሀገር ሊወጡ ነው፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2011)፦ ወደ ቤተ ክርስቲያን የውስጥ መዋቅር በመግባት የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን ዓላማ ለማሳካት ከሚፍጨረጨሩትና ከእነርሱም መካከል እንደ ዋነኛ ከሚታዩት የወቅቱ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ቅጥረኞች አንዱ ሆነው አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” ሲል በገዛ አንደበቱ መናገሩ ተሰማ፡፡ አሰግድ ይህን ምስክርነት ስለ ራሱ የሰጠው ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ለንባብ እንደሚበቃ በተጠቆመ አንድ መጽሔት ሰሞኑን በሰጠው ቃለ ምልልስ ነው፤ ንግግሩንም በአንድ ወቅት በ‹ተሐድሶ› ጉዳይ ላይ ለጠየቀችው አንዲት ሴት የመለሰው መሆኑ ተገልጧል፡፡

ግለሰቡ ቃለ ምልልሱን ከሰጠና መጽሔቱ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ ይህ ቃሉ ከቃለ ምልልሱ እንዲወጣለት አልያም ቃለ ምልልሱ ጨርሶ እንዲቀር “ደኅንነቶች ናቸው” በሚላቸው ግለሰቦች ዋና አዘጋጁን ማስፈራራቱ ታውቋል፡፡ አሰግድ በተለያዩ አጋጣሚዎች “ደኅንነቶች ናቸው” በሚላቸው ግለሰቦች እያስፈራራ ሕገ ወጥ ፍላጎቱን እንደሚያስፈጽም ያስታወሱት የዜና ምንጮቹ ግለሰቡ ከዚህ መንገዱ እንዲታቀብ ሊገደድ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡

አሰግድ ባለበት የሃይማኖት ችግርና ባቀረበው የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከትምህርት ገበታ ቢያገደውም ታኅሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም በኮሌጁ ላይ በመሠረተው ክስ “የኮሌጁ ውሳኔ አግባብ አይደለም” በሚል ሐምሌ ሰባት ቀን 2003 ዓ.ም ትምህርቱን እየተከታተለ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ለክሱ በሰጠው ምላሽ፣ “ጉዳዩ የሃይማኖት ክርክርን የያዘ ስለሆነ ፍ/ቤቱ አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የለውም” ሲል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡ የፍሬ ነገር ክርክሩንም በተመለከተ፣ “ከሳሽ ቤተ ክርስቲያን የማትቀበለውን ትምህርት የሚያራምዱ በመሆናቸው፣ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ ቀርቦባቸው ቤተ ክርስቲያንም ይህን ማረጋገጧ፣ ከሳሽ ያለሰበካቸው በማታለል የቀበና መድኃኔዓለም ሰበካ ጉባኤ አባል ነኝ በማለታቸው ያቀረቡት ማስረጃ በደብሩ አስተዳዳሪ የተሰረዘ በመሆኑ” የከሳሽ ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር፡፡ ደጀ ሰላም የጡመራ መድረክ በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ዘገባዎችን (http://www.dejeselam.org/2011/02/blog-post_10.html) ማቅረቧ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በየጊዜው በፈጸሙት የስም ማጥፋት ድርጊት ክስ ተመሥርቶባቸውና በማስረጃ ተመስክሮባቸው እንዲከላከሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ በአቡነ ጳውሎስ ጥያቄ ፍትሕ ሚኒስቴር ክሱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ካስደረጉ በኋላ ነገ ቅዳሜ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን - ዲሲ ለመብረር መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል፡፡ በዋና ሓላፊው ጥብቅ ቁጥጥር ሥር በሚዘጋጀው የመምሪያው ድረ ገጽ ላይ “ክሱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ በነጻ እንደተሰናበቱ” አስመስለው እንዲዘገብ ያደረጉት አባ ሰረቀ ከሕግ የበላይነት ለመሸሽ በጀመሩት መንገድ ከሀገር ለመውጣት መወሰናቸውን ነው ምንጮቹ የጠቆሙት፡፡ አባ ሰረቀ በድረ ገጹ ያወጡት የተሳሳተ ዘገባ እንዲታረም ክሱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ባዘዘው በፍትሕ ሚኒስቴር ሰዎች ቢነገራቸውም “እምቢ፣ አይሆንም፣ አልሰርዘውም” አልኳቸው እያሉ በጀብድ መልክ ሲያወሩ መሰንብታቸው ተገልጧል፡፡ የ1200 ዜጎችን ከ56 ሚልዮን ብር በላይ አላግባብ ወስዷል የተባለው የአስካሉካን ትሬዲንጉ ግርማይ ከሕግ ተጠያቂነት መሸሽ እንደማይችል ታውቆ ሰሞኑን በኢንተርፖልና በመንግሥት ጥረት በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል፡፡ የእኛው አባ ሰረቀስ? የፍትሕ ፈላጊ ኦርቶዶክሳውያን ጥያቄ ነው፡፡

3 comments:

  1. ምናለ የእግዚያብሔርን ቃል ብትነግሩን
    ስለዐሰግድ የፈጠረው አለለትና አትጨነቁ
    ደግሞ እግዚያብሔር የመረጠውን ማንም አይጥለውም አካሔዳችው በተንኮል ከሆነ አሰግድ እውነት ነፃ ታወጣዋለች፡፡
    ለሆዳችሁ አትሩጡ እግዚያብሔርን አስቡት ስልጣንና ገንዘብ ይመስለኛል እንደዚህ የሚያባላችው እንጂ እውነት ክርስትና አንገብግቧችው ነው አልልም ምክኒያቱም ግልጽ ነው መጻሐፍ ቅዱስ ሁሉነገር በፍቅር እንድናደርግ እነጂ በመነቃቀፍ እንዲሁም በየሚዲያው እራሳችንን በማዋረድ አይደለም እውነት የሚወጣው፡፡ እግዚያብሔር አለ ይፈርዳል ተጠንቀቁ እየዋሻችሁ የእግዚያብሔርን ሰዎች ከመቅደሱ አታባሩ የናንተን ውድቀት አትችሉትም ምክኒያቱም እግዚያብሄር የተመረጡትን እግዚያብሄር ዘይቱን ያፈሰሰባቸውን ማንንም ሊጥለው አይችለውም አትደከሙ በከንቱነው ልፍለፋችሁ ይልቅ አፋችሁን ዘግታችው ፀልዩ በጣም እየበዛ ስለመሰለኝነው እሄን ያህል ያለማቋረጥ ክርስትናን ባልተላበሰ አቀራረብ የማይጥም ፅሁፍ የምታቀርቡት፡፡ ለሆዳችን ሳሆን ለህሊናችን እንኑር የእግዚያብሄርን ቁጣ አትቀስቅሱብን ልጆቹ ቤተክርስቲያ ቆንጥጣ ያሳደገቻቸው ስርአቷዋን የሚያወቁ ናቸው ምከሯቸው እንዲህ በአደባባይ የክርስትና ደንብ አይደለም፡፡ አታሰድቡን የሴጣንም መደሰቻ አታድረጉን ለነሱም ፈተና ይመስለኛል እንጂ ………………….

    ReplyDelete
  2. ምናለ የእግዚያብሔርን ቃል ብትነግሩን

  3. ምናለ የእግዚያብሔርን ቃል ብትነግሩን