ደቂቀ ናቡቴ

Thursday, August 30, 2012

ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀ ጋብቻ

ሁሌም ቢሆን ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ እያየን ዝም የሚል ልብ የለንም፡፡ በተለይ በመድረክ አገልግሎት ላይ በመናያቸው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ ማየተ ደግሞ በጣሙን የቆስላል፡፡ መቼም ሳይገባው የቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ለመውጣት የሚደፍር አለ ብለን አናስብም ትንሽም ቢሆን ምስጢራትን የተማረ እና የስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያወቀ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትማ ካየንው አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት በፈሪሐ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይገባዋል::“በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።” ዘዳ.12:28፤ እንደተባልንው ስንመላለስ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚያዘንን በመፈጸም መሆን ይኖርብናል:: 
እግዚአብሔርን የሚፈራ ትውልድ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል ይገዛል በእግዚአብሔርም የባረካል፡፡ በንስሃ ህይወቱም ሁል ጊዜ ተጠብቆ መኖርም ይገባል “እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ” ራእ.3:3 ንስሃ የሚገባ ሰው ደግሞ ህይወቱ በጸሎት የመሰረታል ሁል ጊዜም ይሰግዳል ይጾማልም ለአገልግሎቱም መቃናተ ፈቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ ይኖራልም፡፡ እነኝህ ያነሳናቸው በጣም ጥቂቱን ግዴታዎች ነው ይህቺን ትንሻን ህይወት የሌለው ክርስቲያን አገልጋይ አይደለም ክርስቲያን ለመሆኑም ጥርጣሬ ውስጥ ይገባል፡፡
ይሁንና ይህቺን በጥቂቱ ያልነው የዘማሪት ዘርፌ አይን ያወጣ ጋብቻ ነው፡፡ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ማናት? በዘፋኝነት ህይወት እያለች ምን አይነት ህይወት ነበራት? የሚሉትን ሁሉ እንተወውና በቤተ ክርስቲያናችን ወደ አገልግሎት ከመጣች ብኋላ በኢትዮጵያ እያለች ከፕሮትስታንት ተሃድሶ አራማጆች ጎን ብዙ ጊዜ ስሟ ሲነሳ የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካም ከሄደች ወዲህ ከ"አባ" ወልደ ትንሳኤ ጋር በአንድ ጉባኤ ለአገልግሎት እንደምትሳተፍ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
ዘማሪት ዘርፌ በኢትዮጵያም እያለች ከጋምቤላ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ረዳት የሆነውን ዲ/ን አይናለምን ከጋምቤላ ከተማው ውጪ በለ አድባር በቅዱስ ቁርባን ማግባቷ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ከዚየም ወደ አዲስ አበባም ሲመጣ አብረው እንደነበሩም የሚታወቅ ነው::

Tuesday, August 28, 2012

ቅዱስ ነአኩቶለአብ



ቅዱስ ነአኩቶለአብ ከአባቱ ከቅዱስ ገ/ማርም ከእናቱ ከንግሥት መርኬዛ ለ1164 ዓ.ም ታህሣሥ 29 ቀን ተወለደ ነአኩቶለአብ ማለት የሰማይ አባታችን እናመሰግነው ማለት ነው፡፡ ልደቱም ቅዱስ  ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እንዳበሰረው  እሱም የተወለደው በብስራተ ገብርኤል ነው፡፡ ከ11 ነገስታት አንዱ ከ4ቱ ነገስታት(ቅዱስ የምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ ገብረማርያም ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነዓኩቶለአብ) ቅዱስ የሚባል ስም የተሰጠው ካህን ወንጉስ ቅዱስ ነአኩቶለአብ እስካሁን ድረስ በህይወት ያለ ለወደፊት በሀይማኖቱ እንደኤልያስና እንደሄኖክ ስለቅዱሳን አማላጅነት መስክሮ የሚሞት እስከ አሁን በብሄረ ህያዋን ያለ በንግስና 40 ዓመት የቆየ ስውር ጻድቅ ነው፡፡ እናትና አባቱ በህፃንነቱ ነበር የሞቱበት፡፡ ነገር ግን የቃልኪዳን አባት ቅዱስ ላሊበላ ከቤተ መንግስቱ ወስዶት በጥሩ ሁኔታ ስርዓተ መንግስቱን እየተመለከተ አደገ፡፡

Friday, August 24, 2012

ኑዛዜ

በዲ/ን ሕብረት የሽጥላ
  • ስን ለካህን ማሳየት ይገባል::
  • ኃጢአትን ለካህን መናገር አይገባም ለሚሉ::
 ይህንን ልናስደምጣችሁ የፈለግንው መናፍቃን እና ፕሮቴስታንት ተሓድሶዎች ኃጢአትን  ለካህን መናገር አያስፍልግም መጸሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም ለሚሉ መልስ ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ከተወገዙት ተሐድሶዎች ውስጥ አሸናፊ መኮንን አሁንም ይህንኑ እያለ እያሳተበት ስለሆነ እና ለሁላችንም ኃጢአትን ለካህን መናገር እንደሚገባን እንድንረዳ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡

 

ዲ/ን ሕብረት የሽጥላ ቃለህይወትን ያሰማልን አሜን::


የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው


የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሪ ሊቀ ብርሃናት ተ/ማርያም መንገሻ ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ  የፍልሰታን ሰአታት ለመቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን  በሚሄዱበት ሰአት እዚያው በቤተ ክረስስቲያኑ ቅጥር ግቢ  ሁለት የደብሩ አገልጋዮች  እንደደበደባቸውና በመሀልም የተመለከቱ ሰዎች በመጮሃቸው ምክነያት የደብሩ ጠበቃዎች መሳሪያቸውን በመተኮሳቸው የተነሳ ፓሊስ ደርሶ ሊተርፉ እንደቻሉ እና ከደብሩ አስተዳዳሪ ጋር ጠብ ይኖራቸዋል ተባለው የተገመቱ የታሰሩ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የታየ ሲሆን ከግድያ ሙከራው የሉበትም ተብለው የታሰሩ የነበሩትን የደብሩ አገልጋዮችን በዋስ የፈታ ሲሆን በወንጀሉ እጃቸው አለበት ብሎ ያመነባቸውን በእስር እንዲቆዩ ሆኗል፡፡
ደብዳቢዎቹ ጳጳሱ ከሚገቡበት ጉድጓድ አንተም ተገባለህ እያሉ እንደደበደቧቸው እና ሊገድሏቸው እንዳሰቡ ያገኘንው መረጃ ያስረዳል ፡፡

Thursday, August 23, 2012

የብጹዕ አባታችን አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአታቸው ተፈፅሟል አጠር ያለ የህይወት ታሪካቸውንም ያድምጡት

የታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ እና ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት ሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን አንድ መሆኑ እንድምታው ምንድነው?

የአለቃ አያሌው ታምሩ የሥርአተ ቀብር የተፈፀመበት ቀን 17/12/1999 ዓ.ም ሐሙስ

ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት 17/12/2004 ሐሙስ

Wednesday, August 22, 2012

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደች

"†♥†ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥"ኢሳ.60፡12
ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መቼም የማይነጣጠሉ ነበር ዛሬ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ተሰሚነቷ እየቀነስ አመራሩ አካል ጫና እያሳደረባት እና ቤተ ክርስቲያኗ እንኳን ሲቃጠሉ ሀይ ባይ እያጣች መጥቶ ዛሬ ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክስ ተፋተው የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ መሪ ለማስተናገድ በቃች፡፡
መቼም ሁላችሁም እንደምትገምቱት ሐይለማርያም ብሎ ፓሮቴስታንት አይኖርም አይደረግም ብላችሁ ተገምቱ ይሆናል ነገር ግን በደቡቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንሰራፍ ያለው የፕሮቴስታንት እምነት ወደድንም ጠላንም አሁን መሪ የተባሉትን ጠቅላይ ሚንስቴር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ሳይቀር  ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ ወላይታና አካባቢውም ቢሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተኩረት ባለመስጠቷ ብዙዎቹ ካደጉባት ቤተ ክርስቲያን   አስተምህሮዋን ባለመረዳት ኮብልለዋል፡፡ እግዚአብሔር ወደ እናት ቤታቸው እስኪመልስልን ልንፀልይ ይገባል እኛ የምንሰራቸው የቤተ ክርስቲያናችን ስራዎች ግን በዝተዋል ፡፡
ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ  እንዲሉ

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም.ከ4.00 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት የቀብር ስነ ስርዓት ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም.ከ4.00 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል ስርአቱ እስከ ነገ ከሰዓት ድረስ የሚቀጥል ይሆናል ከ4.00 ጀምሮም ከሆስፒታል ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመደረስ በዚያም ጸሎት ሲደረግለት ቆይቷል፡፡

በምንኩስና ከዓለም መለየት እና የምነኩስና ቆብ፡፡

ምንኩስና በምንኩስና ከዓለም መለየት
ምንኩስና ማለት አንድ ልብ አንድ ሐሳብ ሆኖ እግዚአብሔርን በማገልገልና እሱን ብቻ በማሰብ ተወስኖ መላእክትን በመምሰል ከዓለማዊው ተድላ ደስታ መለየት ማለት ነው እንጂ ሰው መሆንን ለመርሳት ወይም ለመተው አይደለም፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ሐዋርያ ጳውሎስ " ወበኅቤየስ ምውት ዓለም ወአነሂ ምውት በኅበ ዓለም በኔ ዘንድ የሞተ ነው፡ እኔም በዓለም ዘንድ የሞትኩ ነኝ ብሏል፡፡ ገላ 6፡ ፡14
ሞት ማለትም መለየት ማለት ነው እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡ "አኮኑ ወዳዕነ ሞትነ እምኃጢአት እፎ እንከንክል ሐይወ ባቲ" ከኃጢአት ፈጽመን ተለይተናል እንግዲህ በኃጢአት መኖር እንዴት እንችላለን እንዳለ:: ሮሜ 6፡2
በምንኩስና ከዓለማዊ ግብር መለየትም ፍጹም ለመሆን ነው እንጂ በዓለማዊ ግብር ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገል አይቻልም ማለት አይደለም በዓለማዊ ግብር ሆነው የታዘዘውን ሕግ ፈጽመው ከጸደቁ ዓለማውያን እነ ኖኅ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ሄኖክ ኢዮብን የመሳሰሉ አሉ ማቴ 22 ፡ 32፡፡ ያዕ፡5:11:ዕብ፡11፡ 5፡6፡፡

Monday, August 20, 2012

የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ሆኗል መግለጫውንም እንዲህ ሰማን

" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"ዮሐ.1:3
PM Meles Zenawi has died. The long lasting discussion of his whereabouts are rested now. Ethiopia lost two of its powerful leaders: the premier and the patriarch. It is amazing time. May God rest their souls. Amen
ዛሬ ማለዳ ነሐሴ 15,2004ዓ/ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ አድርጓል::

ይህንንም ተከትሎ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ Haile Mariam Desalegne named acting Prime Minister

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ መረጠ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ  ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ  ሰየመ፡፡ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ  ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቃቤ መንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርክ እስኪመርጥ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት የሚመሩ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ይሆናል::
ቡነ ህዝቅኤል ዛሬ ነሐሴ 14/04 በ9.00 ሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ ውሳኔው ግን የተወሰነው ዛሬ ጠዋት መሆኑ ታውቋል::

Sunday, August 19, 2012

የፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች

ቅዱስ ሲኖዶስ 1991 . ባወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  ስለ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምዕራፍ አራት ላይ ያሉትን አንቀፆች እንመ 
አንቀጽ 13
ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ
  1. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ቀኖና በሚፈቅደው መሠረት ተመርጦ ይሾማል፡፡
  2. ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ፓትርያርክ ምርጫ በሚወስነው ቁጥር መሠረት አስመራጭ ኮሚቴ ይቋቋማል::
  3.   ለፓትርያርክነት የሚመረጡት ዕጩዎች ከሊቃነ ጳጳሳት ከጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳት መካከል ሲሆን ብዛታቸው ከሦስት ያላነሡ ከአምስት ያልበለጡ ይሆናል፡፡