ደቂቀ ናቡቴ

Thursday, August 30, 2012

ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀ ጋብቻ

ሁሌም ቢሆን ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ እያየን ዝም የሚል ልብ የለንም፡፡ በተለይ በመድረክ አገልግሎት ላይ በመናያቸው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ ማየተ ደግሞ በጣሙን የቆስላል፡፡ መቼም ሳይገባው የቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ለመውጣት የሚደፍር አለ ብለን አናስብም ትንሽም ቢሆን ምስጢራትን የተማረ እና የስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያወቀ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትማ ካየንው አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት በፈሪሐ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይገባዋል::“በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።” ዘዳ.12:28፤ እንደተባልንው ስንመላለስ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚያዘንን በመፈጸም መሆን ይኖርብናል:: 
እግዚአብሔርን የሚፈራ ትውልድ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል ይገዛል በእግዚአብሔርም የባረካል፡፡ በንስሃ ህይወቱም ሁል ጊዜ ተጠብቆ መኖርም ይገባል “እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ” ራእ.3:3 ንስሃ የሚገባ ሰው ደግሞ ህይወቱ በጸሎት የመሰረታል ሁል ጊዜም ይሰግዳል ይጾማልም ለአገልግሎቱም መቃናተ ፈቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ ይኖራልም፡፡ እነኝህ ያነሳናቸው በጣም ጥቂቱን ግዴታዎች ነው ይህቺን ትንሻን ህይወት የሌለው ክርስቲያን አገልጋይ አይደለም ክርስቲያን ለመሆኑም ጥርጣሬ ውስጥ ይገባል፡፡
ይሁንና ይህቺን በጥቂቱ ያልነው የዘማሪት ዘርፌ አይን ያወጣ ጋብቻ ነው፡፡ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ማናት? በዘፋኝነት ህይወት እያለች ምን አይነት ህይወት ነበራት? የሚሉትን ሁሉ እንተወውና በቤተ ክርስቲያናችን ወደ አገልግሎት ከመጣች ብኋላ በኢትዮጵያ እያለች ከፕሮትስታንት ተሃድሶ አራማጆች ጎን ብዙ ጊዜ ስሟ ሲነሳ የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካም ከሄደች ወዲህ ከ"አባ" ወልደ ትንሳኤ ጋር በአንድ ጉባኤ ለአገልግሎት እንደምትሳተፍ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
ዘማሪት ዘርፌ በኢትዮጵያም እያለች ከጋምቤላ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ረዳት የሆነውን ዲ/ን አይናለምን ከጋምቤላ ከተማው ውጪ በለ አድባር በቅዱስ ቁርባን ማግባቷ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ ከዚየም ወደ አዲስ አበባም ሲመጣ አብረው እንደነበሩም የሚታወቅ ነው::

  ከኢትዮጵያ ከወጣች ብኋላ ደግሞ በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሐምሌ ወር ቅዱስ እሰጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረውን ዲ/ን ዘገብርኤል ጋራ በስርዓተ ተክሊል ሁለተኛዋን ጋብቻ ፈፅማለች፡፡

መጀመሪያ በቅዱስ ቁርባን ሁለተኛውን ደግሞ በስርዓተ ተክሊል ልብ በሉ በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት ጋብቻ ሲፈፀም ከቤተ ክርስቲያን ከወጣ ብኋላ ምን አይነት አለባበስ የኖረዋል የሚለውን ለእናንተ ትተን ስርዓተ ተክሊል በቤተ ክርስቲያን ስርዓት መስረት እንዴት ይፈፀማል የሚለውን ጥቂት እንመልከት፡፡
በሚታየው አገልግሎት የማይታየውን ፀጋ ከምናገኝባቸው ውስጥ ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ የማይደገም ምስጢር ምስጢረ ተክሊል ነው ፡፡ ምስጢረ ተክሊል የሚፈፀመው በፍትሃ ነገስት አንቀፅ 24፡ 906 ላይ እንደተገለፀው የመጀመሪያው ሥጋው ድንግልና ነው ፡፡ ከሁለት ተጋቢዎች አንዱ ድንግልናውን ያጣ እንደሆን በድንግልና ላለው ስርአተ ተክሊሉ ተፈፅሞለት ተክሊል የሚያደርግ ሲሆን ድንግል ላልሆነው ግን ፀሎተ ንስሃ ተነቦለት ቅዱስ ቁርባኑን ተቀብለው ጋብቻቸው ይፈፀማል ፡፡
ልላው ድንግልናቸውን በተለያዩ ምክነያቶች ላጡ ለምሳሌ በሕክምና የተነሳ፤ በተፈጥሮ ሲወለዱ የድንግልና ምልክት የሌላቸው፤ ለአቅመ ሔዋን ሳይደርሱ ተገደው የተደፈሩ፤ ከአቅም በላይ የሆነ ስራ በመስራት ድንግላናቸውን ያጡ ስርዓተ ተክሊል ሊፈፀምላቸው ይችላል፡፡ ይህ በዚሁ እንዳለ ስርአተ ተክሊል የሚፈፀመው የሃየማኖት አንድነት ላላቸው 2ኛ ቆሮ. 6፡ 14-18፤ ፍቃደኝነታቸውን ለገለፁ ተጋቢዎች እና ከ 20 አመት እድሜ በላይ ለወንዱ ፡ከ15 እድሜ ኣመት በላይ ለሴት ከሆኑ እንድሆነ ሰረዓተ ተክሊል ይፈፀምላቸዋል፡፡ ይህንንማ ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 24 ፤883-884፤894 እና 906 ላይ በስፋት ተዘርዝሯል፡፡
በድንግልና ለመኖር ወስኖ ቃልኪዳኑን ትቶ አፍርሶ ያለ አንድ ሰው ፀሎተ ተክሊል ሳይፈፀምለት በቁርባን ብቻ ማግባት የተፈቀደ ነው፡፡ ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 24፤ 834 “ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱ በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።”ዘኊ.30:2::
በስዓርተ ተክሊል ተጋብተው ባል ወይም ሚስት አንዱ የሞተ እንድሆን እና በሕይወት ያለው ለማግባት ቢፈልግ ግን ሚስቱ የሞተችበት ከአንድ ዓመት ብኋላ፤ ባሏ የሞተባት ከ10 ወር ብኋላ ከሐዘናቸው ተፅናንታ ማግባት ይችላሉ ይህም በፍትሐ ነገስት አንቀፅ24 ፤ 916 ተገልጧል፡፡
በጥቂቱ ስለ ስርዓተ ተክሊል ካየን ዘማሪት ዘርፌን ከላይ ከጠቀስንው የሚገልፃት የቱ ነው፡፡
1. በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈፀሟ?
2. ከበፊቱ ባሏ ወደ ልላ ካህን ባል ማግባቷ?
3. የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት በአደባባይ መጣሷ እና ማስጣሷ?
4. አርአያ በመሆን ፋንታ ብጣሽ ጨርቅ ለብሶ ገላን እያሳዩ ከበሮ መምታቷ?
5. ማህተብ ሳታስር መታየቷ?
ሌላም ሌላም ሌላም ብቻ ሁሉም ስርአተ ቤተ ክርስቲያን ለምን አልተከበረም?  በውጪ ያሉ አብያተ ክርስቲያናተም በስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተብለው ለስርአቷ መከበር ከመድከም ይልቅ ስርዓቷን ለማጥፋት ለመቀየር ጥረቶችስ ለምንድን ነው? ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች ናቸው::
ለአንድ አገልጋይ ነኝ ባይ ደግሞ ይህቺን ጥቂቷን የቤተ ክርስቲያን ግዴታ መወጣት ግዴታው ነው ባዮች ነን፡፡ የእኛ ድርሻመሆን ያለበት እንዲህ መሰሉን ኢሰርአተ ቤተ ክርስቲያን ሲፈፀም ተመልክተን ማለፍ ሳይሆን እንዳይደግም የየራሳችንን ጥረት ማድረግ የጠበቅብናል፡፡

ለቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መከበር ያለሰለሰ ጥረት እናድርግ ፡፡

ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

67 comments:

  1. ሰላም ለደቂቀ ናቡቴ ጸሐፊዎች። በእውነት የጻፋቹት ጽሑፍ ተገቢ እና አስተማሪ ነው። እኔ በመጀመሪያ የአንድን ግለሰብ ስም (የዘማሪት ዘርፌ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀ ጋብቻ) የሚለውን አርዕስት ሳነበው፣ አንድ ግለሰብ እንዲ አደረገች ብላቹ መጻፋቹ አሳዝኖኝ ነበር። ግን እናንተ እንዲህ ብላቹ እውነቱን ካልተናገራቹ ማን ይናገር ታዲያ? የሚል ሃሳብ መጣልኝ። በእዉነት እግዚአብሔር ይባርካቹ። ግን አንድ አስተያየት አለኝ። ለእራሷ ለዘርፌ ለምን ይህን ነገር ማድረግሽ መልካም አይደለም በላቹ አትነግሯትም? ምናአልባት እሱኣም በለማወቅ ይሆናልና ይህን ያደረገችው እና በትመክሯት መልካም ይመስለኛል።

    የማቴዎስ ወንጌል 18፥15
    "ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምዕመናን ከዘማሪዋ ህይወት እንዲማርበት ብለን እንጂ ገና ጋብቻውን እንደፈፀመች ለምን ብለን ይህን ልናስነብባችሁ ነበረ ነገር ግን ይህ በግለሰብ ሰም ይሆናል ብለን ዝም ብለን ቆየን፡፡ ብኋላም በተለያየ አጋጣም ሊሎች ጋብቻዋ ትክክል እንደሆነ አድርገው ሲያወሩ ሰማን በዚህ ጊዜ ግን ግን በተለይ አድርገን ያየንው ተክሊሉን የፈፀመው ደብርም ትክክል ነኝ ብሎ ያምናል ወደ ሚል ድምዳም ላይ ደረስን ስለዚህ
      1. ጋብቻውን ለፈፀመው ደብር ለታዋቂ ሰዎች ከሆነ እያለ እንዳይቀጥልበት
      2. አገልጋዮች ለምዕመናኑ አስተማሪ በሆነ መልክ ብቻ ጋብቻቸውን እንዲፈፅሙ
      3. ምእመናንም ጋብቻቸውን እንዴት መፈፀም እንደሚገባቸው እንዲረዱ
      4. የቤተ ክርስቲያ ስርአት ምን ያህል እንደሚገደን
      ተረድተው በዚህች ዘማሪ ህይወት እራሳቸውን እንዲያዩ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡
      ለምክሩ በጣም እናመሰግናለን እግዚአብሔር ይስጥልን

      Delete
    2. Fitsume menfesawi yehone eyeta naw yaleh. Egziabhare yebarkeh. Gen degmo yehe leloche yemarubet zend esuam endehulum anbeba temaribet zend yemeslegnal. Zem malet tegebe ayedelemina. Negeru esuan becha ayedelem eko yefekeduten kahinat , yajebutin meemen hulu yememeleket yemeslegnal. Este legnam , lersuam , lehulachinem. entsume,enetseleye!

      Delete
  2. amen yirdan
    betam asafarina newir new mastewalun yisten

    ReplyDelete
  3. አምላክ ይቅር ይበላት የሚያሳዝነው ግን በአሜሪካ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ዝም ብለው ተክሊሉን ማድረጋቸው????

    ReplyDelete
  4. ሁለተኛ ጋብቻ እስከሆነ ድረስ ድንግልናዋን በመጀመሪያው ባሏ አጥታዋለች ከዚያ ብኋላ ይኖራል ለማለት አልደፍርም በመሰረቱ ይህ ታሪክ የተነገረን ወደ አገልግሎት ከገባች ብኃላ ያለውን ብቻ ነው አሁን እውነቱን እንነጋገርና በዘፋኝነት እያለች ጭፈራ ቤት እንደምትሰራ ይታወቃል ታዲያ በዚያን ጊዜ ድንግልናዋን ለታጣው ትችላለች ለዚያም መሰለኝ ከመጀመሪያው ባሏ በቁርባን ያገባችው የሚገረመው ደግሞ በቁረባን ከገቡ ብኋላ ወደ ስርአተ ተክሊል ይህ እድገት ነው ዝቅጠት ብቻ ሁሉም ያዛዝናል ለቤተ ክርስቲያን ስርአት መከበር ሁላችንም ቢገደን ባይ ነኝ፡፡

    ReplyDelete
  5. እግዚአብሔር ይቅር ይበላት ።
    እኛ ከመንፈሳዊ ግልጋሎትን ከሚሰጡ ሰዎች ይህን
    መጠብቅ በጣም ዪከብዳል ግን አኔ አንደማስበው
    ጠልቅ ያለ እውቀት ያላትም ስላልመሰለኝ ሌላው እንዳይሰናከል በሰጣቹት አስተያየት ሆነ ትምህርት ተደስቻለውይህን እንድናደርግ ሉኡል እግዚአብሔር ይርዳን

    ReplyDelete
  6. selam lehulachew wegenoche
    selezeche ehete yetetsafewen anbebe betame tegeremku lemen betelu yehen negere keze befetem yemedereg beswa yetejemere endalehone be Youtube laye Ethiopia wedding belachew betegebu bezuwochu bekurbane yetegabu sewoche yeze ayenete chegere yetayebachewale lemesale http://www.youtube.com/watch?v=ynNfEGM5BsQ&feature=related ena http://www.youtube.com/watch?v=f0BbpWSQNjk&feature=related ena lelawochem alu betame buzu yaweme bekurebane ketegabu buhala bezefen yemegabu sente ayetenale ewenet orthodox tewahido yehen alekebelem kalachew christanun zefen hateyate endehone eyenegerachew lehezebu betasetemeru teru new hezebu bekalu endenore metsehafe kedusune betasetenu teru new elalew Egezeyabehere hulachenenem yeredane beretu bezew ketelu elalew

    ReplyDelete
  7. ke agelglot befit ye bete kirstianin amlko ena sireat mawekina mamen yasfelgal::
    1. በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈፀሟ
    2. ከበፊቱ ባሏ ወደ ልላ ካህን ባል ማግባቷ?
    3. የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት በአደባባይ መጣሷ እና ማስጣሷ?
    4. አርአያ በመሆን ፋንታ ብጣሽ ጨርቅ ለብሶ ገላን እያሳዩ ከበሮ መምታቷ?
    5. ማህተብ ሳታስር መታየቷ?
    ለቤተ ክርስቲያን ስርአት መከበር ሁላችንም ቢገደን.

    ReplyDelete
  8. ገና ተዋኒ ስትሆን ነበር ነቀፌታዬን ያቀረብኩት ማየት ማመን ነው ልቦና ለሌላቸው ምስጋናዬ ለደቂቀ ናቡቴ

    ReplyDelete
  9. ደቂቀ ናቡቴዎች በጣም አሳዛኝ እና የምትገርሙ ናችሁ!
    ምነው የ እናንተ ጳጳሳትን ጉድ በጉያችሁ ሸሽጋችሁ የአንዲትን ዘማሪ ታሪክ መዘርዘራችሁ!

    የእናንተንም ጉድ እኮ እናውቀዋለን!

    ReplyDelete
    Replies
    1. yihen Asteyayet Yesetehew Yeenant papasat maleth Orthodox Alemehonhn Yasayal Silezih Ezih Page lay Asteyayet mestet Yelebhim biye Amnalehu Dekike Nabutem Endih Yalutin Asteyayet Sechiwoch batawtut Elalehu

      Delete
    2. የ እናንተ የሚለው የማቅን ጳጳሳት ለማለት ነው እና እንዲታረምልኝ እጠይቃለው::
      ማቅን ቅዱስ ቅዱስ የሚሉት "ጳጳሳት" ይህን ጉድ አንዳያወጡባቸው አይደለም እንዴ?
      ለምን ይዋሻል????

      Delete
  10. Hizbu Endiredaw madregachihu Tiru new God Bless You

    ReplyDelete
    Replies
    1. danel keberet endhu new yaderegew men yegeremal

      Delete
  11. Dekike nabutiewoch mistrun endeh lememenan mastawokachuh tiru new enie zerfe kebefetu zefagn koyeta wode egzeabhare bet memelesa tru neber negr gen yeahunu yebas.....betam kebade new slezeh benante bekule tbke ketetle yedereg yebetekrstiana srat yetebk....
    .....

    ReplyDelete
  12. Sirate betekirstean malet hulum sile EGZIABHEAR kibr ena feqad yetesera neaw, yehininm eyastebeqech yalechum Orthodox Tewahido betachin nat... be betu wust kalen yeFikir ena yeLijnet gideta alebin.. Qidus Pawlos sile alebabesachin yenegerenin Lemetebeq elet elet benuroachin feqadegna kalhonin betekirstean qitir wust sihon gin yefeqadachin guday mehonu yeqeral.. Ezih lay dirdir yelewm...degomo yeterekebnewn yemeklit metenim mastewal tegebi yemeslegnal.. KE AMETAT BEFIT SILE AND TAWAQI YEHAGERACHIN ORTHODOKSAWI ZEFAGN ENDE D.NABUTE LE EGZIABHEAR QAL ENA SIRAT YEMIQOREQORU YETEWAHIDO LIJOCH YESETUTIN YETEQAWMO ASTEYAYET KE WEDAJE GAR ANBIBEN SINWEYAY ENE BALEMASTEWAL 'MALETU MINCHGIR ALEW ENEM..ANTEM YEHININ ENADERGEWALEN SILEW "..ante bitisenakel weym bititefa erasihn weym tiqitochìn tasenakilaleh neger gin esu ena endersu yalut milionochin yasenakilalu..lemadanum endeziaw.." yalegn bizu astemrognal, Libona yesten..bertu!

    ReplyDelete
  13. Sirate betekirstean malet hulum sile EGZIABHEAR kibr ena feqad yetesera neaw, yehininm eyastebeqech yalechum Orthodox Tewahido betachin nat... be betu wust kalen yeFikir ena yeLijnet gideta alebin.. Qidus Pawlos sile alebabesachin yenegerenin Lemetebeq elet elet benuroachin feqadegna kalhonin betekirstean qitir wust sihon gin yefeqadachin guday mehonu yeqeral.. Ezih lay dirdir yelewm...degomo yeterekebnewn yemeklit metenim mastewal tegebi yemeslegnal.. KE AMETAT BEFIT SILE AND TAWAQI YEHAGERACHIN ORTHODOKSAWI ZEFAGN ENDE D.NABUTE LE EGZIABHEAR QAL ENA SIRAT YEMIQOREQORU YETEWAHIDO LIJOCH YESETUTIN YETEQAWMO ASTEYAYET KE WEDAJE GAR ANBIBEN SINWEYAY ENE BALEMASTEWAL 'MALETU MINCHGIR ALEW ENEM..ANTEM YEHININ ENADERGEWALEN SILEW "..ante bitisenakel weym bititefa erasihn weym tiqitochìn tasenakilaleh neger gin esu ena endersu yalut milionochin yasenakilalu..lemadanum endeziaw.." yalegn bizu astemrognal, Libona yesten..bertu!

    ReplyDelete
  14. Sirate betekirstean malet hulum sile EGZIABHEAR kibr ena feqad yetesera neaw, yehininm eyastebeqech yalechum Orthodox Tewahido betachin nat... be betu wust kalen yeFikir ena yeLijnet gideta alebin.. Qidus Pawlos sile alebabesachin yenegerenin Lemetebeq elet elet benuroachin feqadegna kalhonin betekirstean qitir wust sihon gin yefeqadachin guday mehonu yeqeral.. Ezih lay dirdir yelewm...degomo yeterekebnewn yemeklit metenim mastewal tegebi yemeslegnal.. KE AMETAT BEFIT SILE AND TAWAQI YEHAGERACHIN ORTHODOKSAWI ZEFAGN ENDE D.NABUTE LE EGZIABHEAR QAL ENA SIRAT YEMIQOREQORU YETEWAHIDO LIJOCH YESETUTIN YETEQAWMO ASTEYAYET KE WEDAJE GAR ANBIBEN SINWEYAY ENE BALEMASTEWAL 'MALETU MINCHGIR ALEW ENEM..ANTEM YEHININ ENADERGEWALEN SILEW "..ante bitisenakel weym bititefa erasihn weym tiqitochìn tasenakilaleh neger gin esu ena endersu yalut milionochin yasenakilalu..lemadanum endeziaw.." yalegn bizu astemrognal, Libona yesten..bertu!

    ReplyDelete
  15. Sirate betekirstean malet hulum sile EGZIABHEAR kibr ena feqad yetesera neaw, yehininm eyastebeqech yalechum Orthodox Tewahido betachin nat... be betu wust kalen yeFikir ena yeLijnet gideta alebin.. Qidus Pawlos sile alebabesachin yenegerenin Lemetebeq elet elet benuroachin feqadegna kalhonin betekirstean qitir wust sihon gin yefeqadachin guday mehonu yeqeral.. Ezih lay dirdir yelewm...degomo yeterekebnewn yemeklit metenim mastewal tegebi yemeslegnal.. KE AMETAT BEFIT SILE AND TAWAQI YEHAGERACHIN ORTHODOKSAWI ZEFAGN ENDE D.NABUTE LE EGZIABHEAR QAL ENA SIRAT YEMIQOREQORU YETEWAHIDO LIJOCH YESETUTIN YETEQAWMO ASTEYAYET KE WEDAJE GAR ANBIBEN SINWEYAY ENE BALEMASTEWAL 'MALETU MINCHGIR ALEW ENEM..ANTEM YEHININ ENADERGEWALEN SILEW "..ante bitisenakel weym bititefa erasihn weym tiqitochìn tasenakilaleh neger gin esu ena endersu yalut milionochin yasenakilalu..lemadanum endeziaw.." yalegn bizu astemrognal, Libona yesten..bertu!

    ReplyDelete
  16. ወደድንም ጠላንም ስር ዓተ ቤተ ክርስቲያን በተለይ በቅዱስ ጋብቻ በኩል በቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ችግሮች ይታያሉ::

    እንኳን ዘማሪዋ ጳጳሱም አላከበሩት! ቤተ ክህነት ይመስክር! ስለዚህ ጉድ ባታወጡ መልካም ነው እላለው::

    ReplyDelete
    Replies
    1. ewnet new::

      Tekedino bikemet yishalal yeLelochu endetekedenew hulu::

      Delete
  17. endet new kenezi abiyate kirstiyanat gar weyim kenezi abatoch gar erik minamin yemibalew? esti silesu enawira?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Mikias tew tew bezih zuria bananesa yishalal::

      degimo yelelochun EThiopia yalutin Zemarian, diakonat, kahinat, papasat tarik anisiten lela gud endanafela::

      tekedino yibsel!!

      Delete
  18. wey fetari ahuns melkam yemibal zena tefa eko.....esti amlak yitareken!!!!!

    ReplyDelete
  19. danel keberet endehu new yaderegew lejun baher dar telo aydel entoto mareyam lela betekelil yagebaw.zerefe setehon lemen addes hone .demo sew neseha kegeba behuala fetsum dengel new yehe yenseha abatoch guday new.kum negeru kezh behuala letedarewa tamagn hona menorewa enge yehen seladeregech siol ategebam.batekalay werre alebachu.yehene yenante gude bezerezer ayalkem /bezu diyakonate dengelenachewen katu behuala new betekelele yemiyagebute lemen bibal yebetekerestyan gebena lemeshefen sebal.lelaw demo tekelele tederego demo yemitseleyew tselot ye serehate kureban lihon yechelale.gen yemetaderegute hulu enzehen lejoch sew endetelachew behonem enesu gen alwedekum mekenyatum manenem yemaytela egzabheren yezewalna .leb yesetachu

    ReplyDelete
  20. I think if there is a problem, try to talk to her instead of criticizing her in public. As a human being we are not perfect, so we cannot judge others. Lets be fair and if things go wrong, u can teach by mentioning the wrong doing not the doer!! that is what i think!!! We all make mistakes, we just have to pray so that God would give us the wisdom to see the right way!!! If she is the one who committed the sin, let God be the judge not us!!! Lehulachinim libona yisten!!!

    ReplyDelete
  21. ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
    የያዕቆብ መልእክት 2:17 "ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።"

    ReplyDelete
  22. አሁን እውነት ይህን ማለታችሁ የዘማሪን ዘርፌን ስህተት አይተን እኛ እንድንማር ነው ወይስ ሌላ አላማ አለው ??
    ማቅ እኮ የራሱን አባል ስም እንደ እንቁላል እየተንከባከበ የነ ዘርፌ ሲሆን ሌላው እንዲማርበት ይሉናል::
    የዘርፌ ነገር ትክክል መሆኑን እና አለመሆኑን ባላውቅም ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ከዚህ የባሱ ነገሮች አሉ::

    1000% የምናገረው ደግሞ እናንተም ይህን እንደምታውቁ ነው::

    ReplyDelete
  23. እረ የማቅ ጳጳሳት ይህን ነገር በሰሙ እና እነሱም በተማሩ!
    ብዙ ሳይወላልዱ እና ልጆቹ ሳይጣሉ!

    ReplyDelete
  24. Question? how about if she is still virgin, don't have sex with the first husband, can't she get Teklil?

    ReplyDelete
  25. why would you mention her name. you can just give your info about ' ye tekelel gabecha' well you lost me when you start to attack her on your faceboook page. may God forgive us all. we all are sinners.

    ReplyDelete
  26. በእውነቱ ዘርፌ ድሮም ከነ ፖስተር በጋሻው ጋር ሆና በቤተክርስቲያን ላይ ስታላግጥ የነበረች ወሮበላ ወንበዴ እንደሆነች እናውቃለን ነገር ግን እዚያ ያሉት እነ አባ ተብየው ጋብቻውን ፈጻሚዎቹ ናቸው የመጀመሪያዎቹ ተጠያቂዎቹ በዘፈኗ ስለምታዝናናቸው እነሱም ዝም ለነገሩ እነሱስ አፍራሾች አይደሉም እንዴ አቡነ ልበላቸው ወይማን አላውቅም እንጂ ሃብተማሪያም (መልከፄዲቅ) የወጣላቸው ለሥርዓት የማይገዙ ጸረ ቤተክርስቲያን የሆኑ በኢትዮጵያውና በአሜሪካው ሲኖዶስ መካከል እርቁ እንዳይፈጸም ከሚፈልጉት መካከል ዋነኛው መሆናቸው ግልጽ ነው። እነዚህ ሰዎች ናቸው በዚህች ወፍ ዘራሽ ጋብቻን በቅድስት ቤተክርስቲያን እየባረኩ ታሪኳን እያወቁ ሥርዓት ሲጠፋ ትውልድ ሲበላሽ ግድ የሌላቸው ታሪክ ባህል፣ ትውፊት፣ ሥርዓት የሚባል ነገር የማይገባቸው ናቸው አጠገባቸውም ፖስተር መላኩ አለ ምንም ችግር የለም አንድ ላይ ሆነው የዋሁን ኦርቶዶክሳዊ ይሄም የማርያም ቤተክርስቲያን ነው እያሉ ይኽው ሰውን ሲያውኩ አሉ 20 ዓመታት ተቆጠረ ዛሬም እንዳሉ አሉ። ዛሬ እንኳን እነ አቡነ ጳውሎስን እግዚአብሔር በማይመረመር ጥበቡ ሲያነሳ ቤተክርስቲያን አንድ እንዳትሆን ጥረታቸውን ቀጥለው ኢህአዴግ እያለ እርቅ የለም በማለት እንደ ፖለቲከኛ ሌላ ነገር ውስጥ መግባት ጀምረዋል። ወገኔ ንቃ ዛሬ በአሜሪካ እየተደራጁ ነው እነዚህ ሰዎች ቤተክርስቲያንን ወደ መናፍቃን ጎሬ ለማስገባት መንገዱን እያመቻቹ እንደሆነ ጠቋሚ ነገሮች ልንገርና ላብቃ፡
    ፩/ እነ አቡነ ፋኑኤል እነ ትዝታውን አምጥተው ሥራቸውን በዘፈን ጀምረዋል የሳቸውም ጋሻ ጃግሬ ኃይለጊዮርጊስ የዚቅ ቀንደኛ ተባባሪ ነው ስልት ቀይሰው ቤተክርስቲያናቱን ካህናቱን እና ምዕመኑን ለያይተው በተለያየ መሰሪ ወጥመዳቸው ውስጥ ለማስገባት እየሞከሩ ነው።
    ፪/ አንዳንድ ሰባኪ ነን ብለው እራሳቸውን በየቤተክርስቲያኑ የሚሹለከለኩ ለምሳሌ እራሱን ዲያቆን ነኝ የሚለው መኩሪያ ጉግሳ የተባለው የመናፍቃን cell ስውር አድርባይ የሆነ ምናልባት ዋሽንግተን ዲሲ ያለ ሰው ሊመለከትና ሊያርመኝ ይችላል ሥራውን እየሰራ ይገኛል ሥራዎቹ
    ፩ኛ/ ቅዳሴ አስቀድሶ የማያውቅ፣ በአንድ ሰንበት ሦስት ወይም አራት ቦታ ሄዶ ሰብኮ አበል ተቀብሎ የሚሄድ
    ፪ኛ/ በስብከቱ ላይ አንድም ቀን ተሳስቶ እንኳን የቅዱሳን፣ የሰማዕታት፣ የእመቤታችንን ስም የማያነሳ ለማስረሳት የሚጣጣር አድር ባይ የመናፍቃን ተወካይ፥
    ፫ኛ/ በጊዮርጊስ፣ በሚካኤል፣ በልደታ ማርያም ሲያስተምር በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ቀን ጌታችን መድኅኒታችን በመላዕክቱ አድሮ ባሕራንን እንደታደገ በሚነገርበት ቀን አንድ እንኳ የቅዱስ ሚካኤልን ስም ሳያነሳ "ጌታ በሚያቃጥል ፍቅሩ አሙቆን" "ለእኔና ለእናንተ ጌታ ያደረገልን" "ጌታ የሳሮን ጽጌረዳ" ሲል ውሎ የሚጨርስ አድርባይ
    ፬ኛ/ የጸሎት መጽሐፍ አትጠቀሙ እያለ በየቤቱ እየዞረ የሚያስተምር
    ፭ኛ/ ቅዱሳን በዙብን ያሉን ይበቁን ነበረ በየጊዜው ቄሱ አዳዲስ ቅዱሳን ለምን ያመጡብናል የሚል
    ፮ኛ/ በእኛ ቤተክርስቲያን ጾም በዝቶብናል እያለ በየጊዜው የሚደሰኩር
    ፰ኛ/ የአባ ወልደ ተንሳኤ ደቀ መዝሙር እና የነ ፖስተር በጋሻው ጥብቅ ጓደኛ እና አፈቀላጤ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል
    ስለዚህ እላይ እንዳልነው እነ አባ ወልደ ተንሳኤ፣ አባ ሓብተማሪያም (መልከፄዲቅ) አባ ፋኑኤል ጋሻ ጃግሬዎች ደግሞ ኃይለጊዮርጊስ፣ ትዝታው፣ዘርፌ፣ መኩሪያ እነዚህ ሰዎች በተለየያ ጊዜ በውስጥ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃዎች ያሳያሉ በአላማ አንድ ስለሆኑ ሥራቸውን በትልቁ ዘርግተው ቤተክርስቲያኗን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ ሁሉም የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው ስለዚህ ነቃ ብለን ዓይናችንን ከፈት አድርገን ብንመለከት እና እነዚህን የናት ጡት ነካሾች ቢቻል ንሰሃ ገብተው እንዲመለሱ ያለበለዚያ ግን ወደዛው ወደ መናፍቃኑ አዳራሻቸው እንዲሄዱ የይለፍ ወረቀታቸው እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን
    ተቆርቋሪዎች

    ReplyDelete
    Replies
    1. GOD BLESS YOU!!!

      Delete
    2. egzeabehere yestehe!!!! wondeme abezeto yedenegel lije yebarekeh!!!!!!

      Delete
    3. be ewnet yekidusan Amlak Egziabher esu yifreden!
      GOD bless you friend!

      Delete
  27. berigit yakerebachihut neger melikam new.Neger gin andande endezihi ayinet negerochin sitakerbu ergitegia mehon alebachihu. yihi sirat yetekahedebet betekirstian kahinatin meteyeki endihum leraswa menigure neberbachihu.yihenin blog yemiywit sewochi limarubetim lisitubetim yichilalu please ersi bershachin linwaded yigebanal yelelochin sihitetoch menager melikam bihonim tinkake ,maregagecha yasifeligal.

    ReplyDelete
  28. እውነቱን ለመናገር ዘርፌ መጀመሪያ በቁርባን እንዳላገባች ገልጣ ተናግራለች ፤ ከመጀመሪያዋ ጓደኛ ጋር አንድ አባት ቃል አጋቧቸው እንጂ ህጋዊ ጋብቻ እንዳልፈጸመች ተናራለች ፤ አሁን እኛ መጠየቅ ያለብን መጀመሪያ ካገባች ማስረጃችሁን አምጡ ፤ አገባች ተብሎ ተጽፎ ነበር ነገር ግን አላገባችም ፤ ቃል ኪዳን ነው የፈጸመችው ፤ ሁለተኛ ደግሞ ቤተክርስትያን ቃል የማገባባት ስርዓት ያላት አይመስለንም ፤ በአውደ ምህረት ላይ ሁለት ጓኛሞች ቃል የምታገባባበት ስርዓት የላትም ፤ ለምን በአውደ ምህረት ላይ ቃል አገባቧት ብለን መጠየቅ እንችላለን ፤ ይህ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ፤ ከቁርባን በኋላ ተክሊል ነው ብለን አናስብም ፤ ተሀድሶ ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ሆና በመስራቷ ሌላ ጥያቄ መጠየቅ ይቻላል ፤ ይህ ግን ተገቢ አይመስለንም ፤ አንገቷ ላይ ክር አለማሰሯ አግባብ አይደለም … አስኪ በደንብ አረጋግጡ.. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ እሰጣችኋለሁ ፤ ቃለመጠይቁም አለኝ ፤ እናንተ እንዳቀረባችሁት አይደለም ፤

    ReplyDelete
  29. betam yemiasazn yebetekrstianachin siraate gabcha ayen ,seman.enante nabutiewoch gen egziabher yabertachihu.
    bezih ley, be2tum wogen asteyayetochin mestet efelgalehu
    1.yezerfie difret, yemejemeriawun gabcha debka teklil endiderglat mefeleg
    2.bedebiru yalut kahinat abatoch bewunu ye EOTC abal nachew? behonu noro, matum saytaser, raqutun bemitay gela bekebero yahunu mezmure new woys yaqedmow chifera yemilewun lemeleyet eskiadagt dires bezmita memelketu asazagn new.
    lemangnawum ke endezih aynet difret yesewren.

    ReplyDelete
  30. ስለ ዘማሪት ዘርፌ የጻፋችሁት እውነት ይሁን ውሸት የማይቀው የለም:: ግን ግን ግን

    ከዚህ የበለጥ ስንት ጉድ ሞልቷል እኮ ክርስቲያኖች! አንዱ አስተያየት ሰጭ ተከድኖ ይብሰል እንዳለው እኔም እንደሱ ክድን እንዳለ ይብሰል እንጂ ጉድ እናፈላለን::

    ደቂቀ ናቡቴዎች ስለ ምስጢር ተክሊል እና ቅዱስ ጋብቻ በደፈናው ብትጽፉ ይበጃል እላለው::
    ይህች ዘማሪ ከዘፋኝነት ወደ ዚህ መምጣቷ ሊያስደስተን ይገባል:: እኛም እየመከርናት፣ የ እህት የወንድምነት ምክር እየለገስናት የድንግልን ልጅ መኃኔዓለምን እንድታመሰግን ብነረዳት መልካም ነው እላለው:: እግዚአብሔር የድምጽ ጸጋ ሰጥቷታልና::

    ReplyDelete
  31. I think now God is in action so people who disrespect our mother orthodox Church watch your back I am not kidding I am praying every day for mu church. And I know that God listens no matter who you are.

    ReplyDelete
  32. part 1
    በእውነቱ እጅግ የሚያሳዝን እና የሃይማኖታችንን ሥርአት ያልተከተለ የቤተክርስቲያናችን ስም የሚያጎድፍ ተግባር ዛሬ በእህታችን ብናየውም ትላንት በብዙ እህቶች እና ወንድሞች የተፈጸመ ተግባር ነው፡፡ …. ትላንት እህታችን የቤተክርስትያናችንን እምነት አቆሸሹ አበላሹ ካልናቸው ወገኖች ውስጥ ነች ብለን አብጠልጥለናታል ብዙ አዝነንባታል ዛሬ ደግም በዚህ አሳፋሪ ተግባር አይተናት ልባችን ቆሰለ…. መቼም የእኔው እድፍ ከሷ የከፋ ቢሆንም የዚህን ተግባር እኩይነት ከመናገር ግን አያግደኝም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የእርሱን ምህረት እና የጽድቅን መንገድ ጠቋሚ፣ ስትጠፋ ተመለሺ ብሎ የሚያግዳት እረኛ የናፈቀች ነፍስ እንደእርሷ ለጠፉ ወገኖች ልትቆረቆር ግድ ነው፡፡ ……… እውነት እኛን መቆርቆር ያለበት እርሷ ስለሰራችው ሀጥያት ነው ወይንስ ስለእርሷ መጥፋት?,,,, ስለምን ድርጊት ብቻ ወደ መኮነን እንሮጣለን….. እኛስ ማነን ? እኩይ ተግባራችን ጎልቶ አልወጣ እንደሆነ እንጂ ሁላችንም በተለያየ ጊዜና ሰዓት በአልተገቢ የሀጥያት መንገድ እራሳችንን ያገኘን ሰዎች ነን……. ትላንት በእርሷ መዝሙር እና በወንድሞቻችን ቃለ ስብከት ስንቱ ተመልሷል ስንቱንስ አንቅቷል?….. ያኔ ስንቶች አባቶች ናቸው ተሳስታችውሃል እንዲህ ነው ብለው የመለሷቸው? ስንቶቹስ ናቸው ተባረኩ ብለው መርቀው፣ መስከቀል አሳልመው የሸኙ?...... ጣራችን ስታንጠባጥብ ዝም ብለን አይተን ለምን አብዝታ ስታፈስ እናማርራለን፣ እንወቅሳለን፣ እንኮንናለን? ስለምንስ መጠገን ሲቻል ትላንት ያጠለለችንን ጣራችንን አውጥተን እንጥላለን? ሊያውም ክቡር የእግዝሄር ፍጡርን? ለዘርፌ መጥፋት እኮ ዘርፌ ብቻ አይደለችም የምትጠየቅበት፡፡……………………………

    ReplyDelete
  33. part 2
    እኩይ ተግባርን እየነቀሱ ለሌላ ማስተማርያ መመከርያ ከማድረግ ባሻገር ስለምህረት፣ ስለአንድነት፣ ስለሚያሸንፍ የእግዚያብሔር ፍቅርም በበለጠ እንስራ …. በዙዎች ጠፍተናል ሀይ ባይ መላሽ እንፈልጋለን….የጠፋነውን ይበልጡኑ እንድንጠፋ ሳይሆን እንድንመለስ መንገድ በማሳየት እና በመምራት አባቶች ሆነ ቃሉን አዋቂዎች ትልቅ ሀላፊነት ያለባችሁ ይመስለኛል፡፡…… ……………….. እና እባካችሁን አሁንም ቢሆን ጊዜው አለመሸምና እና እህቶቻችንን ወንደሞቻችንን በምክር እና በተግሰፆት እንዲሁም በጸሎት ወንድም እህቶቻችንን መልሱልን፡፡ እነሱን በትላንት ተግባራቸው ዘላለም ከመውቀስ እና ከመኮነን ይልቅ መክሮና ገስጾ ትላንት የጀመሩትን አገልግሎት በክርስቲያናዊ መንፈስ እና ሥረዓት ዛሬም እንዲቀጥሉ ማበረታታት ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ነው ያለኝ…….
    አመሰግናለሁ…….

    ReplyDelete
    Replies
    1. በጣም ልዩ የሆነ ምርጥ አስተያየት!
      ኃጥያት የሌለባት ይውገራት እንዳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጥያት የሌለበት ከፈለገ ስሟን ያጥፋ!
      ከሁሉ በፊት ግን ምክር እና ተግሳጽ ይቀድማል:: ሁሉ ነገር በፍቅር ቢሆን እዚህ ደረጃ አይደረስም ነበር::

      Delete
  34. እነ አቡነ ሚካኤል አቡነ ሳሙኤል እንዲሁም ሌሎች ታላላቅ አባቶች ስለሚያደርሱት የቤተ ክርስትያን ስርዓት መጣስ ብሎም በድንግልና ልጅን መውለድ ምነው እንደጥፋት አይታይም ? ከዘፋኝነት ወደዘማሪነት የመለሳትን አምልላክ እያመሰገንን አቅማችን በፈቀደ ማበርታት ሲገባን ስለምን የሰውን በደል ርዕስ እናደርጋለን ? በቅዱስ ቁርባን ስማግባትቱ ምን ማረጋገጫ አላችሁ ? ቸር ይግጠመን!

    ReplyDelete
    Replies
    1. do you have any proof if she is virgin???

      Delete
  35. የ ኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ስርዓት እየጣሱና ስርዓትንም ለመጣስ ቀዳሚ በመሆን ሕዝባችንን ተንኮል፤ አሕዛብን ደግሞ አሉታዊ የሆነ እይታን እያስተማራጩ ያላችሁ እናንተ ዘማሪ፣ሰባኪ፣መምህር፣ ወዘተ ነን ባዮች
    እስቲ ቆም ብላችሑ ሞት እንዳለ አስቡ።
    እግዚአብሔር ለበቱ ቀናዒ እንደሆነ እያወቃችሑ አይቅስፈንም ብላችሑ ነውን????!
    የድንግል ልጅ እርሱ ልቡናን ይስጠን።አሜን።

    ReplyDelete
  36. Hulum neger ejig betam yasazinegnal. Egziabher mefthe yisten.

    ReplyDelete
  37. wogenoche, ahun ko gudayu ye'bekeristianachinina ye'haimanotachin enji ye'andi Zerfe hiwot bicha ayidelem. 'tekedino yibisel...' esikemeche? Ye'Zerfe serg malet ko ye'tehadiso sera mehonun atizenigut.

    Tehadisowoch wanawu alamachewu ye'betekirsitianin sireat be'mabelashet ena dogmawan bemenkef silehone yihem betegibar endezihu bilishuna newur negeroching bebetekirsitian bemesirat newu. silezih ahunim ahunim ye'zih siraet guday menekef alebet be'adebabayim mewutat alebet.

    ke'tewahido

    ReplyDelete
  38. ቀድሞውኑ የመጣችው ከተሃድሶ ወገን እንደሆነ እየታወቀ አሁን ይህ ሁሉ ግርግር ምን ያደርጋል፡፡ ይልቅ የሚጠቅመው ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ከዓመታት በፊት እንዲህ ዓይነት ስርዓት የሚያፋልስ ጥፋት አቅደው የገቡ መናፍቃንን በጥንቃቄ መከታተልና በስርዓተ ቀኖና ከተመለሡ መምከር አለዚያም ወደመጡበት ሃይማኖት መመለስ ነው፡፡
    እመቤታችን ለዘርፌ የንስሀ እንባንና መመለስን ፡ ለቤተክርስቲያናችንም ፍቅርንና አንድነትን ታድድልልን፡ አሜን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. እባካቸሁ ጊዜው በሀገራችን በቤተክርስቲያናችንና የደረሰባት ከባድ ፈተና ነው መጸለይ ነው የሚግባን እንጂ ለጸብ ለክርክር አላስፈላጊ ነገሮችን ማራገብ አይግባም ማስረጃም የለም እያወቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ጥላቻን ለመንዛት አትሞክሩ ህዝቡንም ግራ አታጋቡት የተለያዩ የተክሊል ስርአት አሉ በቤተክርስቲያናችን ስለዚህ ለሁሉም እነደየ አመጣጡ የሚሰተናገድበት ስለዚህ የቤተክርስተቲያን አባቶችን መጠየቅና መረዳት ያስፈልጋል እንጂ የሰው ስም እየጠሩ አሉባልታ ማራግበና ለቤተክርስቲያኑዋ ፈተና መሆን አይግባም አንድዋ ጣት ወደ ለሌላው ስጠቁም ሶስቱ ወደኛ መሆኑን አትርሳ ለሐግራችንና ለሀይማኖታችን በመጸለይና ምህረቱን እንዲሰጠን በእግዚያብሄር ፊት መውደቅ ይገባናል

      Delete
  39. ደቂቀ ናቡቴ፣ በእርግጥ በሲኖዶስ የጸደቀ ማኅበር መሆናችሁን ባላውቅም፣ ስማሁ እንጅ ግብራችሁ ማቅን ትመስላላችሁ፣ ዲ/ነር አይነአለምና ዘርፌ አልተጋቡም፣በዘርፌ ስም ዲያቆኑን ስም አታጥፉ፡፡ ጥሩ ጓደኛዬ ነው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡

    ReplyDelete
  40. ደቂቀ ናቡቴ፣ በእርግጥ በሲኖዶስ የጸደቀ ማኅበር መሆናችሁን ባላውቅም፣ ስማሁ እንጅ ግብራችሁ ማቅን ትመስላላችሁ፣ ዲ/ነር አይነአለምና ዘርፌ አልተጋቡም፣በዘርፌ ስም ዲያቆኑን ስም አታጥፉ፡፡ ጥሩ ጓደኛዬ ነው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ለመሆኑ ስንት ማቅ ነው ከአውራቸው ከዳንኤል ክብረት ጀምሮ በሥርዓተ ተክሊል ያገባው፣ እናንተን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ደንጋጊ ያደረጋችሁ ማነው፡፡ ማቆች በራሳው ስም የሚፈጥሩት ሁከት አንሷው በቂቀ ናቡቴ፣ እያሉ ምናምንቴ ነገር ለምን ትጨምላችሁ፣

    ReplyDelete
  41. የምን መሸፋፈፈን ነው፤እውነተኛ የቤ/ክን ልጅ ከሆናችሁ እውነቱን አፍርጡት፤ ሳይደፍርስ አይጠራም፤አለዚያ ከአሉባልታ አያልፍም፡፡ አባሰላማዎች እኮ የጰጳሳትን ሚስቶችና ልጆች መዘርዘር ጀምረዋል፤አውነቱ ማ ጋር እንዳለ እንድዬ መድሐኔዓለም ማጥራቱ አይቀርም፤ ተሐድሶ መናፍቃን ግንቦት ወር ላይ ማጣፊያው ሲያጥራቸው ጳጳሳትን ሚስቶች አላቸው እያሉ ጀምረው ነበር ፤ስለዚህ እውነት እንዳይፃፍ ማስፈራራቱ ይቅርና አለ የተባለውን ጉዳይ አፍርጡት፤
    ቤ/ክን እግዚአብሔር ያጥናት፤ መለየት የሚወድ ምኞቱን ይከተላል እንዲል ሁሉም በገዛ ፈቃዱ ነጎደ ከልካይ ፣መካሪ ተቆጪ ጠፋ ዋ ቤ/ክን ተዋህዶ፤

    ReplyDelete
  42. እናንተ የምታውቁትን ያህል ሌላ ሰው የማያውቅ ይመስላችኋል?

    ReplyDelete
  43. ለቤተክርስቲያን ስርአት መቆርቆራችሁስ ባልከፋ !
    ከባቴ አበሳ መድሀኔ አለም ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሐጢአት ሲሸፍን ፣ወይ ደሞ ለራሱ ሐጢአቱን ለሰራው ሰውዬ ብቻ ሲያሳውቅ እንጂ በገሀድ ለሰው ሲያውጅ አልሰማንም ፡፡እናንተ ከማን ተማራችሁት ?

    ReplyDelete
  44. እመቤታችን ለዘርፌ የንስሀ እንባንና መመለስን ፡ ለቤተክርስቲያናችንም ፍቅርንና አንድነትን ታድድልልን፡ አሜን፡፡

    ReplyDelete
  45. ke-einanite nisuh / fisum sew binor yihichin set yiwigerat. yeyanidanidachu hiywet bifetesh sinit gud teshekimachihal, De-kik nabute why u r so jealous of those gifted Orthodox?

    ReplyDelete
  46. እግዚአብሔር ይቅር ይበላት ።

    ReplyDelete
  47. kalefe behuala, sihtetin magalet bE/r fird megbat new, better to comment befoer to spesfic to her. this written pices is to personal. i hate i didnt, learn rather..

    ReplyDelete
  48. ewunetu meneger alebet hulachinim enakalen eyetedebeke kemiwera begilts siwera new mastekakel yemichalew. mikniyatum zim ketebale lelawum tikikil neew blo new yemiketlew.

    ReplyDelete
  49. እኔ ግን በዘማሪዋ ላይ ጥፋት አለ አልልም፡፡ ገና ካለማወቅ ወደ ማወቅ የመጣች ናትና ሁሉንም ነገር በሞቅታ ስታደርገው አያለሁ፡፡ ጥፋቱ ያለው አባት ተብየዎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የማውቀውን ስለመጀመሪያው ጋብቻ ልግለጽላችሁ፡፡ ይህን ጋብቻ የፈጸመችው ከእነበጋሻው ጋር ለ‹‹ታላቅ›› ጉባኤ ጋምቤላ በመጣችበት ወቅት የሀ/ስብከቱ ስራ አስኪያጂ በሆነው በአምሳሉ‹‹አባ ተክልሃይማኖት›› ግፊት ነው፡፡ የእርሱ የጥቅም ተጋሪ ከሆነው ‹‹ዲ/ን›› ዓይናለም ጋር እንድትጣበቅ አደረጋት፡፡ ያጣበቃቸው ሃይማኖት ሳይሆን የስጋ ጥቅም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም ጉደኛው አምሳሉ በ2001 ኣ.ም በጋምቤላ ሀ/ስብከት ጎደሬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ያውም በጾም ወቅት ሥርኣት ፈፀመላቸውና ጋምቤላ ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ዐውደ ምህት ላይ ህዝብ በተሰበሰበበት ዲ/ን ዓናለም እና ዘማሪ ዘርፌ ከበደ ጋብቻቸውን ፈጽመዋለ፤ እልል በሉላቸው አስባለ፡፡ የዋህዋ ዘርፌም ማግባቷን በጋቻ ቀለበቷ ከማሳየት አልፋ ለሚዲያ ግልጽ አደረገች፡፡
    ይህንንም የ2001 ዓ.ም የመጋቢት ወይም የሚያዚያ ወር የዕንቁ መጽሔት እትም ፈልጎ ማረጋገጥ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ ከሞቅታ ነጻ የሆኑ የጋምቤላ ምዕመናን እንዴት በጾም ወቅት ጋብቻ ይፈፀማል ሲሉ ውስጥ ለውስጥ መነጋገር ሲጀምሩ ቆፍጣናውና መልስ በኪሱ አምሳሉ የጋብቻ ስርዓት ፈጽሜላቸው ተመልሰዋል ባለበት አንደበቱ የቃል ኪዳን ቀለበት ነው ያሰሩት እንጂ ጋብቻ ከጾም በኋላ ነው ብለው ለዚያው ህዝብ እንደገና ዋሹት፡፡ እንግዲህ በአምሳሉ የሃይማኖት ትምህትና ዕውቀት መሰረት በፆም ጊዜ ቃል ኪዳን ማሰር ይቻላል ማለት፡፡
    የዘርፌን ሁለተኛ ጋብቻ ስሰማ አሁንም ለአገልግሎት በሄደችበት አሜሪካ አምሳሉን(አባ ተ/ሃይማኖትን-አንዳንዶች አያልቅበት ይሏቸዋል) የመሰለ ‹‹አባት››አጋጥሟት ይሆን አልኩ እንጂ በእርሷስ ፍርድ የለም፡፡ የእርሷ ጥፋት ሰው አለመምጧ ነው፡፡ ስለዚህ የዘርፌ ጋብቻ ስርዓት ብልሽት ጋምቤላ በአባ ተ/ሃይማት አማካይነት ተጀመረ እነሆ ‹‹ቅድስት›› አገር አሜሪካ በአባ . . . አማካይነት ተጠናቀቀ፡፡

    ReplyDelete


  50. It is good to teach people from mistakes of others so that the mistake is not repeated again. However going in to others personal life in detail is not expected from religious person. God teach us love and forgiveness. And we have to preach this living the life itself not by accusing others. Who are we to judge others, we can only advise positively and pray if we have the willingness to do so.
    Belief is not something which some one imposes on other person, we can only learn from each other. Whenever we are accusing we are pushing people to the wrong direction. It is only love that can attract and strengthen our relationship and keep our church safe from different challenge.
    Orthodox Church is a church which can be a member of it by choice not by force. Anyone with deep inside knowledge and God’s given wisdom will look for another option other than Orthodox Church.
    It is so confusing for me why people particularly religious leaders are antagonized while they are in exile. Religion and politics are totally a different world. I do not understand why people mix these two different ideologies.
    I am just a layman believer with very little knowledge but huge believe. I am trying just to beg you people in exile to bring peace and work together as unified people.

    ReplyDelete
  51. How come you do not post all the comments people write? Maybe because you want people to read only your lies! Saying you are defending the church, you love God and so on but living in lie. Accusing people on false evidence. You know God sees you! You can trick people, but you can not trick God!

    ReplyDelete
  52. አመጣጣቸው ለህይወት ሳይሆን ካህን ባል ፍለጋ ነበርእንዴ? ነው ወይስ በዓላማ የሚደረግ ተልእኮ ይሆን? ምክንያቱም በሳቸው ምክንያት ቢያንስ ሁለት ካህናት ተሰናክለዋል፡፡

    ReplyDelete
  53. this is because, orthodox did not teach the rules since ethiopians are kid!!! if you see the jewish people, they study the Thorah since they are age 3 !! At 12,(for boys) and 13 (for girls) they do their Bar Mitsvah, which is their anknowledgment of God publicaly and for that purpose, they have to write a short essay based on a bible story that relate to them...why is it we orthodox, we do not have a serious teaching of the Bible followed by confirmation at 12, 18 and consistant follow up? this lady is doing because she knows nothing of God's fear! the more problematic thing, is the church or the kess who approved this marriage, he is more to be blamed, the Lord said that the teachers will be judged more severly...

    I seriously invite the church to start a bible study, for boys and girls "my people perish because of the lack of knowledge" said Jesus...such teachings should be also put on youtube so parents can minister their kids at home too...I am 44 years old, all i know of orthodox is from repeating the traditions and I was lost at some point...I ordered a bible from home and studied it on my own...what I know today, could have helped me during my youth...I could have avoided many mistakes...but God is good, He protected me...orthodox does not teach well so everybody is jumping into pente...I don't blame people they want God...so they go everywhere hoping to find...

    ReplyDelete