ደቂቀ ናቡቴ

Saturday, August 11, 2012

በገዳማት ላይ እየተከሰተ ባለው ጥቃት በተመለከተ ስብሰባ ተጠራ


 እንደሚታወቃው በኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳማትና አድባራት ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ነው የማይባል በደልና ግፍ እየደረሰ መሆኑን ይታወቃል፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ ማሕበራዊና ስነጥበባዊ እድገት ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው አለም የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡ Read in PDF

ቤተክርስቲያናችን ባላት ታሪክና መንፈሳዊ ሐብት ለበርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ትልቁን ድርሻ የምትይዝ ሲሆን ለዚህም መንግስትና የተላያዩ ተቋማትን በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ እያደረገች ስትገኝ፣ ወደኦትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶችም በዋነኛነት የቤተክርስትያን ጥንታዊያን ገዳማት አድባራት እና እንደጥምቀት ፤ መስቀል(ደማራ)እና ልደት የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላትን መንፈሳዊ አከባበርን ለመመልከት እንደመጡ ዘወትር የሚመሰክሩነው፡፡
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያው እና ስነጥበባዊ የአበረከተችውን አስተዋጽኦ በየትኛውም ዘመን የነበረና ወደፊትም የሚኖር እንደሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚመሰክረው እውነታ ነው፡፡ 

 ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በበርካታ ችግሮች ከውስጥና ከውጭ እየተፈተነች ትገኛለች ፡፡ በችግሮቹ ዙሪያ መወያየትና ዘላቂ መፍትሔ ሀሳብ ማግኘትና ችግሮቿን መፍታት አስፈላጊና ዋነኛ ጉዳይ ነው፡፡
ይህንኑ በተመለከተ በችግሮቿ ዙሪያ ለመወያየትና ዘላቂ የመፍትሔ ሀሳብ የመፈለግ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ለሚኖሩ  ኦርቶዶክሳውያን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል ነሐሴ 6, 2004 በዋሽንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከ4፡00pm  ተዘጋጅቷል በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ  ኦርቶዶክሳውያንም በጉባኤው እንዲገኙ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪ ቀርቧል፡፡
የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ችግር ተወያይቶ መፍትሔ መሻት የሁላችንን ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡በጉባኤው ላይ ሊቃውንት ቤተክርስቲያን መምህራን ዘማሪያን እንዲሁም ሙሁራን ተጋብዘዋል፡፡ ኑና የበኩሎን አስተዋጽኦ ያድርጉ ይላሉ የጉባኤው አስተባባሪዎች ቀንና ሰዓት ነሐሴ 6, 2004 4፡00(EST)
እግዚአብሔር ገዳማቱን አድባራቱን ከጠላት ይጠብቅልን ፡፡
ለበለጠ መረጃ  savewaldba@gmail.com

No comments:

Post a Comment