ደቂቀ ናቡቴ

Monday, August 13, 2012

ፅንሰታ ለማርያም

ቅዱስ ያሬድማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ:- ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች"      አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ:- ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ"
 በኢየሩሳሌም አገር የሚኖሩ ኢያቄምና ሃና የተባሉ በጣም ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ኢያቄምና ሃና እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተውለነዚኽ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?” ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡ በተኙ ግዜም ለሁለቱም እግዚአብሔር መልካም ፈቃዱን በህልም ገለጠላቸው፡፡ ኢያቄም በህልሙ ሃና በእቅፍ ውስጥ ከፍሬዎች ሁሉ የምትበልጥ መልካም ጣፋጭ ፍሬ ይዛ ተመለከተ፡፡ ሃና የኢያቄም በትር ለምልማ፣ አብባና አፍርታ ተመለከተች፡፡ ከእንቅልፋቸውም ነቅተው ስለ ህልማቸው ተነጋገሩ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሆንላቸው በጸሎት ጠየቁ፡፡ እግዚአብሔር ወንድም ሆነ ሴት ልጅ ቢሰጣቸው አድጎ እኛን ያገልግለን ይታዘዘን ሳይሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆን እንደሚሰጡት ቃል ገቡ፡፡

ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡:   ሃና በእርጅናዋ ጊዜ መፅነሷ የተመለከቱ ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርመው እየመጡ ይጠይቋት ነበር፡፡ 

እመቤታችን ማርያም በፅንስ እያለች ያደረገቻቸው ተአምራት ዐይነ ስውር የነበረችው  የአርሳባን ልጅ ወደ ሃና መጥታ እውነትም ሃና መጽነሷን ለማረጋገጥ ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡ በአድናቆትም ሳታስበው ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ በሌላ ግዜም የአጎቷ ልጅ በህመም ምክንያት ይሞትና ሃና ትወደው ስለነበር ልታለቅስ ወደአረፈበት ቤት ትሔዳለች፡፡ እንደደረሰችም አስክሬኑ በተቀመጠበት መካከል አልጋ ዙሪያ ስታለቅስ ሳለ ድንገት ጥላዋ ቢያርፍበት የሞተው ሰው ተነስቶ ሃና የአምላክ እናት የምትሆን እመቤታችንን እንደምልድና በዚህም ሃና እጅግ የከበረችና ምስጋና የሚገባት መሆኗን መሰከረ፡፡
ኃጥያታችንን ከሚያስተሰርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አሜን !!!!!

1 comment:

  1. I am sure this paragraph has touched all the internet people, its really
    really fastidious piece of writing on building up new website.



    my blog post; Beats By Dre Studio

    ReplyDelete