ደቂቀ ናቡቴ

Friday, September 14, 2012

ፍሬዋን ለመብላት




መውተርተር መግተርተር ይኑርህ መታታት
መማረክ እጅ መስጠት ትሁን ለጠላት
ለማሸነፍ ይሁን ሁሌም ፆም ፀሎት



ርዕይ የሌለህ እንዳትሆን ከንቱ
ንደፍ ተልዕኮህን አሳውቅ በብርቱ
ይታይሃልን በጭላንጭል ክፍቱ

መጓዝህን አታቁም ለመድረስ ካሰብከው
ወደ ኋላ አትይ ተስፋቢስ ዝርው ሰው
ነገ ትደርሳለህ በአምላክህ ካሰብከው



ወላዋይ ሰው ሆነህ አትጓዝ በሕይወትህ
አምላክ ያለው አይቀር ይገባል ከእጅህ
ተፍጨርጨር ሁል ጊዜም እስክታልፍ በሞትህ


አንኳኳ አትሰልች እስኪከፈትልህ
እስኪሰማ ድረስ በር መቺ መሆንህ
የበሰለን ፍሬ አፍርቶ ታያለህ

ያሰብከው ያቀድከው ውጥን ባይሳካ
እንዳልነበር ቢሆን ሊጥህ ባየቦካ
አንደቀን ይሆናል እያልክ ተመካ

ደግሞም ካንተ አስወግድ መቀያየር አቋም
ቸር አንደሆነ አስብ ሁሌም መዳሃኔአለም
የሚጎዳህን አየቶ ከለክሎህ ቢሆንም
ይሰጥህ ይሆንል ለአንተ ነገ የሚጠቅም


ታዲያ መታገስህ ፍሬ ያፈራ ለት
ጾም ጸሎት ስግደትህ ሲደርስ ከፀባዖት
ጊዜ ያለው አምላክ ይሰጥሃል ወተት
አንተ ብቻ ታገስ ፍሬዋን ለመብላት

2 comments:

  1. It is perfect time to make some plans for the long run and it is time to be happy.

    I've learn this submit and if I may I wish to suggest you some interesting things or tips. Maybe you can write subsequent articles relating to this article. I want to read more issues approximately it!
    my web page :: ballard massage center

    ReplyDelete