ደቂቀ ናቡቴ

Friday, September 21, 2012

በክርስቶስ ደም የተመሠረተች ቤተክርስቲያን ልዕልናዋ ተጠብቆ እንዲቀጥል ከምዕመናን ምን ይጠበቃል ?? ተግዳሮቶቿስ ምንድናቸው???

(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 11/2005) የምህላው ጊዜ ተፈፅመዋል ዛሬ ላይ በአንድ ልብ ሆነን ስላ ቤተ ክርስቲያናችን የልዕልና አና ብሩህ ጊዜን እናልማለን፡፡  
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሕዳሴ ዘመን:: ኢትዮጵያ ታላላቅ ቅዱሳንን ያፈራችበትን ወርቃማ ዘመንን ለመድገም ከአሁን የተሻለ ታላቅ አጋጣሚ ይመጣል ተብሎ መቼም የሚጠብቅ አይሆንም፡፡ ፈር ያጡት ሰርዓቶቻችን መስመር የሚይዙበት ፣ ምንም ስርዓት ያልተሰራላቸው ጉዳዮች አዲስ ስርዓት ተዘርግቶላቸው የወደፊት መጭውን እድል የምትወስንበት ፣ እንደ ግመል ያበጡትን ከፍተኛ ችግሮቻችንን የሚወገዱበት ፣ የምንፈታበት ጊዜ ከዚህ የተለየ አጋጣሚ ምቹ ሊመጣ? የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ወርቃማዎቹ ጊዜያት ዛሬ ላለነው ትውልድ ሲናፈቁን የሚኖሩ ቢሆንም እንዲህ ያሉ ትውልድን የምንፈጥረው እጅ ለእጅ ተያይዘን ተከባብረን በአንዲት ቤተክርስቲያን ያለሰለሰ ጥረት ስናደርግ ፣  ስርዓቶቿን ስናስጠብቅና ስንጠብቅ ፣ ማንም እንዳሻው ሲፈነጭ አይቶ ዝም እየተባለ የሚታይበትን ጊዜ ሲከስም መሆነ ግልጽ ነው፡፡  
በዚህ አጋጣሚ ይህ ጊዜ ካለፈን እና መሠረታዊ ችግሮቻችንን ሳናስተካክል የነበረው ስርዓት አለብኝነት ይቀጥል ብለን ዝም ካልን ግን ምን አልባትም ለቤተክርክስቲያናችን ጥቁር አሻራ አስቀምጠን እንዳልፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በተለይ ደግሞ የዘረኝነትና የፍቅረ ነዋይ ችግሮች መጥራት ካልቻሉ አደጋው የከፋ ይሆናል፡፡
የውስጥ ችግሮቻችን ምንም ብዙ ቢሆኑም ትኩረት ወስድን እያንዳንዱ ስርዓት እንዲስተካከል ካደረግን በአንድ ሀሳብና በአንድ ልብ ሆነን ከውጪ ጠላቶቻችን የሚመጣብንን የሰማዕትነት ጊዜያት እየናፈቅን ብሩህ ዘመንን እያየን በቃለ እግዚአብሔር የታነጸ ታላቅ ዜጋ ፣ ትውልድ የምንፈጥርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡: በዚህ ረገድም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አርአያነት ለእኛም ይህ ተስፋ ይሆናል፡፡
እንደሚታወቀው በአስተዳዳራዊ ጉዳዮች ይህች ቤተክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉባት እነኝህ ችግሮች ከሌሎች አኀት አቢያተ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች አንፃር እንኳን ስናየው የትየለሌ ናቸው::  ሁል ጊዜ መርሳት የሌለበት ጉዳይ ቢኖር ይህ ምዕመን እስከ አሁን ችግሮቻችንን ዝም ብሎ ይመለከታል ለወደፊትስ ይህ ይቀጥላል? ዛሬ ላይ ከሞባይል ስልክ አቅም እንኳን መቅደስ ገብቶ ቅዳሴ ላይ የሚያነጋግር ትውልድ፣ ሽጉጥ ታጥቆ መቅደስ የሚገባ ትውልድ፣ በአለባበሱ አቅም እንኳን ሳይቀር ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትውልድ ነው ያፈራነው፡፡ ይህን መሰሉን ችግሮቻችንን እየተመለከትን ዛሬም ዝም የምንል ይሆን?   ጥቃቅን ችግሮቻችንን ባለመፍታታችን ምክንያት እንኳን የማያስቀድስ ሰንበት ተማሪ፣ ወንጌል የማይወድ ምእመን፣ ንስሀ አባተ የሌለው ትውልድ፣ በዘፈቀደ የሚመላለስ አገልጋይ ነው የፈጠርነው፡፡ በተለይ አገልጋይ የሆንን እስኪ ወደ እራሳችን እንመለስ፣ ራሳችንን እንይ፣ ከራሳችን እንጀምር እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው መጀመሪያ ሕይወታችንን ነው፡፡ እራሳችንን ሳናስተካክል ሌላውን ለማረም ስንጥር እንታያለን:: ሕይወት የሌለው አገልጋይ እንዴት ሕዝቡን ወደ እግዚአብሔር ማምጣት ይችላል? እግዚአብሔር ካደረግነው አገልግሎት ይልቅ እኛን ያየል "ወደ አቤል እና ወደ መስዋእቱ ተመለከተ" መጀመሪያ አቤል ነው የተመለከተው አቤል ማነው? አገልግሎቱ ተግባሩ ቀጥሎ የሚመጣ ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡ በአገልግሎቱ ያለን መጀመሪያ ከሁሉም ነገር ይልቅ ልንለወጥ፣ እራሳችንን ልናርም ፣ ከመዳፈር ልንቆጠብ ይገባል፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘብ ልናደርግ ይገባል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ካሉባት የውስጥ ችግሮች ለማላቀቅ በአንድ ሀሳብ ሆነን ልናግዛት ይገባል፡፡ የምናያቸው ችግሮች ፣ ስርዓት አልበኝነቶች ሁሉ በግልፅ እየተነጋገርን ለማረም ዝግጁ እንሁን::  ነገ ላይ የእኔም ችግር ይጋለጣል እያልን መደባበቁ ዋጋ አያሰጠንም ፡፡ ዛሬ ላይ በውስጥ ችግሮቻችንና በእኛ የተነሳ ቤተ ክረስቲያን የወንበዴዎች ዋሻ፣ የስርዓት አልበኞች መከማቺያ እየተባለች እስከመቼ? ሁላችንም ከተጠያቂነት አናመልጥም ትልቁም ትንሹም፡፡        
ታዲያ ለዚህ ሁሉ ችግር እልባት መስጫ ጊዜ ከዚህ የተለየ ቀን ከየት የምጣ ወገኔ? ለመፍትሄም ነገ ዛሬ ሳንል መወያየት ፣ መመካከር ፣ ምን ቢሰራ ይሻላል? ማለት ተገቢ ነው፡፡ ነገር ሳናበዛ እስኪ ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ከፓትሪያርክ ምርጫ በፊትም ይሆን ብኋላ ግን በአስቸኳይ ቢያያቸው የሚገቡና ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጥቂት ስርዓቶችን እንመልከት፡-
  • ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ምዕመናን ለመንግስተ ሰማይ ከማብቃት ባሻገር ለወደፊት ቤተ ክርስቲያን በአለም ደረጃ የቱ ጋር ለማድረስ ነው የምሰራው? በአፍረካ ደረጃ ምን ርዕይ ቤተ ክርስቲያኗ ይኖራታል? የሚለውን መወሰን፡፡
  • ገዳማት ሲቃጠሉ እና በሕዛብ ሲፈርሱ ዝም ብሎ ከመመልከት ውጪ የሚታይ መፍትሄ የሚሰጥበትን መንገድ ማየትና መወሰን፡፡
  •   በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ለማስከፈት ምን መፍትሄ መሰጠት አለበት?  የሚለውን መወሰን፡፡
  •   የቤተክርስቲያን የውስጥ ጉዳዮች ካህናት እርስ በእርስ መካሰስ አገልጋይ ከአገልጋይ መካሰስ በአህዝብ ፍርድ ቤት መዳኘቱ እስከመቼ ነው? የሚለውን መወሰን አቅጣጫ ማመላከት፡፡
  •   የሊቃውንት ጉባኤ ሚና ምንድነው? ሥራውስ? ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ መጻህፍት ካልፃፋ፣ የተጣመመውን ካላስተካከለ ፣ ህዝቡን ካላረጋጉ፣ ለመናፍቃን ተገቢ መልስ ካልሰጡ፣ ተሃድህሶውያን በቤተ ክርስቲያናችን እንዳሻቸው ሲፈነጩ አጠጋቢ መልስ ካልሰጡ ጥቅሙ ምንድነው? በስም የሊቃውንት ጉባኤ ይባል እንጂ የሚታይ የሚጠቀስ ስራ የቱጋ ተሰርቷል? ጳጳሳት ሲያጠፉ ዝም ብለው የሚመለከቱ ከሆነ? ምን ላይ ነው የሊቃውንት ጉባኤ የሚያስብለው “ኃጢአተኛውን ኃጢአቱን ተመልክተህ ባተመከረው ባትመልሰው ከእነኃጢአቱ ቢሞት እኔ ደሙን ከአንተ እፈልጋለሁ” የተባለው እውቀቱ ላላቸው አይደለምን ይህን ባለመድረጋቸው እንደሚያስጠይቃቸው እና መሰሎቹን ጉዳዮች ዛሬ ላይ መወሰን፡፡
  •   በሃይማኖት ጉዳይ ችግር ያለባቸውን አገልጋዮች ቦታ እና ኃላፊነት ከመቀያየር ወጪ ቁርጥ ያለ ውሳኔ መስጠት እና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መምጫ መንገድ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
  • አገልጋይ ካህናትና መሪጌቶች ከካቶሊኩ ቤተ ፀሎት በመሄድ ለገንዘብ ብለው ሁለት ቦታ የመረገጣቸውን አካሄድ እንዲቀር የሚደረግበት መንገድ መቅረት ያለበትና ድርጊቱን በሚፈፅሙት ላይ የማያዳግም ውሳኔ መወሰን፡፡
  • መነኮሳት፣ ባሕታውያን እና ካህናት የተመለከቱ ጉዳዮችን ለምሳሌ፡- መነኮሳት የት ይመነኩሳሉ? የት ይቀመጣሉ? የስረ ድርሻቸው ምንድነው? ከአጢቢያ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በአገልግሎት ደረጃ ድርሻቸው ምንድነው? ካህናትም ባህታውያንም ጋር አሁን የሚታዩት ተመሳሳይ ችግሮችን መርምሮ ውሳኔ መስጠት፡፡
  • መምህራን ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ተመርቀው ከወጡ በኋላ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ፣ በጠረፋማው ሁሉ ተንቀሳቅሰው የማያስተምሩበት ሁኔታ እስከመቼ ነው? እንዲሁም አሰቀድሱ እያሉ የማያስቀድሱ፣ ጹሙ እያሉ የማይጾሙ፣ ንስሀ ግቡ እያሉ ንስሃ የማይገቡ መምህራንን ይዛ እስከመቼ ነው? በአዲስ አበባ ብቻ ታጉረው መምህራን ነን ቢሉ ጥቅሙ ምን ይሆን? ይህም ውሳኔ ይጠይቃል፡፡
  • ሌሎችም …….
ታዲያ እነኝህና መሰል ችግሮቻችንን ለመቅረፍ ከዚህ የተለየ፣ የተሸለ አጋጣሚ ከየት ይምጣ ? ወይስ ችግሮቹ የለም? በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያናችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ የሚመለከታቸው ሁሉ እነኝህና ተያያዥ ችግሮች መፍታት ያላሰለሰ ጥረት ቢደረግ ነገ ለምንፈልጋት አንዲት እና ቀጥተኛ ሃይማኖት መለምለም ታላቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ 
የተፈጠረው አጋጣሚ አያምልጠን ነው በአጭሩ፡፡
+++እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን+++

4 comments:

  1. amen, amen, amen!! commitment! commitment!! commitment!!!

    ReplyDelete
  2. ጥሩ እይታ ነው በበኩሌ ያለኝ ሲኖዶሱ ምርጫ ከማድረጉ በፊት ተግዳሮቶቿን ቢያጠራ ለመጪው ፓትርያሪክ መልካም ይመስለኛል በበኩሌ ቃለ ወንጌል በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስፋፋ የሚያደርግ አሰራር ቢኖረን ጡሩ ነው በክርስትናው ቀደምት እንደመሆናችን አይደለም ዛሬ ላይ ያለው ይልቁንም ምዕመኗ እየቀነሰ የሌላው እየጨመረ እና ለሌላው እምነት መጋቢ ነው የሆንው ስለዚህ በአለም አቀፍ ደረጃ መስራት ይጠበቅብናል የያዝነው ሃይማኖት ታላቅ አና ቀደምት እንደመሆኗ ሁላችንም ለአፍሪካውያን የራሳችን የሚሉትን ሃይማኖት እናስረክባችሁ አመስግናለሁ፡፤

    ReplyDelete
  3. ጥሩ እይታ ነው

    ReplyDelete