ደቂቀ ናቡቴ

Wednesday, October 3, 2012

ሶስቱ ምክሮች

(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 23,2005 ዓ.ም) ይህን ፅሁፍ የት እንዳነበብኩት በውል ትዝ አይለኝም እናንተ ግን ትማሩበት ዘንድ እንድታነቡት አቀረብኩላችሁ ታሪኩ እንዲህ ነው፡-  

ከወንድሞች አንደበት ከሰማሁት ብሎ ይጀምራል ፀሀፊው ቀጥሎም  ባንድ ወቅት አንድ ባል እና ሚስት በትዳር ሁለት ልጆችም ነበራቸው፡፡  አብረውሲኖሩ በመሃላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው፡፡ በቤታቸው ግን የሚላስ የሚቀመስ በመጥፋቱ ምክንያት  ይህንን ችግር ለዘለቄታው ለመፍታት ባል ራቅ ብሎ ሄዶ  ሊሰራ ተስማምተው  ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ መስራት ጀመረ፡፡ በተከታታይ 13 ዓመታት ሰራ ከዚያም ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ተነሳ፡፡ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ መጣ ምን? ደሞዝ፡ ደሞዙ ምን ሆነ? በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነውን 3000 (ሶስት ) ብር  ተሰጠው፡፡ ምን ያድርግው? ተመልሶ እዛው ስራውን ይቀጥል? ወደ ናፈቁት ቤተሰቦቹ ይሂድ? ይቻላል ግን ተመልሶ ቢሰራ ደሞዙ መቆራረጡ አይቀሬ ነው፣ ወደ ቤተሰቦቹ እንዳይሄድ 13 ዓመት ይህን ብቻ ሰራሁ ቢል ማን ያምነዋል? አወጣ አወረደ በመጨረሻም  ሌላ ቦታ ተቀጥሮ ለመስራት ወሰነ፡፡  ሌላ ጉዞ..፡፡ ብዙ ከተጓዘ ብኋላም አንድ አባት አገኘ፡፡
እኛም አባት ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ምንስ ትፈልጋለህ? አሉት፣ አሱም ሁሉንም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው፡፡
አኛም አባት አንዲህ አሉት እንግዲያውስ የምትፈልገውን ማግኘት ቀላል ነው፡፡
እሱም "እንዴት አባቴ?" ሲል ጠየቃቸው
እሳቸውም "በል አንድ ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ" አሉት የቸገረው ነውና ነገሩ አሱም አንስቶ አንድ ብሩን ሰጣቸው፡፡
እኝህ አባትም "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይሉታል፡፡

"ሁለተኛውን አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ" ይሉታል አሱም በየዋህነት ሁለተኛውን ይሰጣል
እኝህ አባትም "በማያገባህ አትግባ" ይሉታል፡፡ "ይህው ነው አባቴ" ቢላቸው "አዎን ልጄ ይልቁኑም 3ኛውን አምጣና በጣም አስፈላጊውንና የመጨረሻውን ስጦታዬን ልሰጥህ" አሉት፡፡ የመጣው ይምጣ መጨረሻም የመጣው ይምጣ ብሎ ሺ  ሰጠ፡፡
እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለው "በል ልጄ በቀጥታ ወደ ቤትህ ሂድ" ብለው በባዶ ኪስ ግን ከሱሰት ምክሮች ጋር አሰናበቱት፡፡  እሱም ምክሩን ተቀብሎ ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ፡፡

በመንገድም ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጎዝ መሸባቸው  ነጋዴዎቹ ለምን ባቆራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ አሱም አብሯቸው ጉዞ እንደጀመረ የኛ አባት ምክር ትዝ አለው "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው ስለዚህ ተመልሶ በሚያውቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ አንድ ከተማ ደረሰ፡፡ "የመሸበት አንግዳ ንኝ አሳድሩኝ" ማለት ጀመረ፡፡
አንድ ሰው ተጠግቶት "የውልህ ወንድሜ እዛ ሰው ቤት ሂድ ያሳድርሀል ነገር ግን ሰውዬው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም አድልህን ሞክር" አለው፡፡ አሱም የተባለበት ቤት አንኮክቶ "ቤት የእንግዳ" ነው ተብሎ ገባ፡፡ ታዲያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረውም ባለቤቱ ተገርሞ "አንዴት ሆነህ ተረፍክ በል?" ቢለው ባለ ፀጋው፡፡ እንግዳው "ከምኑ?" ብሎ ደነገጠ፡፡ ባለ ፀጋውም  ምነው ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴዎች ተዘርፈው ግማሾቹም ተገለው ዛሬ ከተማው ለቀሶ ብቻኮ ነው፡፡ አለው ፡፡ እንግዳዉም አንድ ነገር ትዝ  አለው ያቺ በአንድ ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛው ሕይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ"
ስለ መሽ የቤቱ አመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጎዳ ብቅ አለች "ጥያችሁ ጠፋሁ አይደል?" አለች፡፡ እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም የተወሰነ አካሏ ብቻ ነው ሰው የሚመስለው በዛላይ ማስፈራቷ ወደ ጎዳ አስክትገባ ናፈቀ "ከዚህች ጋር አንዴት ትኖራለህ?" ብሎ አስኪጠይቅ ተጣደፈ፡፡ ወደ ጎዳ ገባች ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው የኛ አባት ምክር "በማያገባህ አትግባ" የሚለው፡፡ ሆዱ መጠየቅ አየፈለግ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ ፡፡ ደግሞ ሌላ ፈተና ጠዋት የቤቱ ባለቤት "ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ " ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አፅም የሞላበት ሜዳ አሳየው አንግዳውም ደንግጦ "ይሄ ደሞ ምንድነው?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን አየነቀነቀ ዝም አለ፡፡ የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ እንዲህ አለው "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ ይህ የምታየው ሁሉ ስለ ሚስቴ የማየገባቸውን አስተያየት ስለ ሰጡ የተገደሉ እንዳንተ አዚህ ቤት በእንግድነት የመጡ ነበሩ፡፡ አንተ ግን ታላቅ ሰው ሰለሆንክ የሀብቴን አንድ አራተኛ (1/4) ሰጥቼሀለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ በደስታ  ሄደ፡፡
እዛች ደሳሳ ጎጀ የደረሰው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም በትልቅ አንጨት የምትዘጋ (የምትደገፍ) በሩን ቀስ ብሎ ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች፡፡ አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች ጎንበስ ሲል ጎራዴውን አየ አነሳው አንገታቸውን ሊቆርጠው በንዴት ጦፎ እጁን ወደ ላላላላላላላለይይይይይ አነሳ የእኛ አባት 3ተኛው ምክር ትዝ አለው "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው፡፡ ወዲያው ከቤቱ ውጪ በተጋደመው ዛፍ ላይ ወጥቶ ቁጭ አለ በተቀመጠበት ንብረቱን እንደያዘ አንቅልፍ ይዞት ሄደ፡፡ ወፎች ተንጫጩ ለሊቱም ነጋ ሚሰት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን አየችው አልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት ከአንቅልፍ የነቃው ባል በመደናገጥ ስሜት ሳለ አጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎረምሶች አስተዋወቀች "ይህ የመጀመሪያ ልጅህ ነው ይህ ደሞ ሁለተኛው" ብላ፡፡ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል"  የልጆቹን ነፍስ ከማጠፋት ረዳው ማለት ነው፡፡
ሁላችሁም አስቲ ራሳችሁን ጠይቁ ይህ ሰው ያለነዚህ ምክሮች ቢመጣ ምን ይፈጠር ነበር? የሚያስተምረን ነገር ካለ ምን ያስተምረናል አናንተ ምን ተማራችሁበት?
አንድ አኔ ከብዙው አንዱን የተማርኩበትን ልጥቀስላችሁ እኔ ይህ ነገር ትዝ ባለኝ ቁጥር የሚያስታውሰኝ በትንቢተ ኤርምያስ 6 16 ላይ "በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱን መንገድ ወዴት አንደሆነች ጠይቁ፤ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም መድሀኒት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን "አንሄድባትም" አሉ፡፡" ካንድ ቦታ የሚያደርሱ የሚመስሉ ብዙ መንገዶች ሊኖሮ ይችላሉ፤ ሐዋርያው "ቅን የምትመስል መንገድ አለች" እንዳለው፡፡ አንዳንዶች መፆም ሲከብዳቸው አቆራጭ መንገድ ይፈልጋሉ ከዚያም ጌታ ፆሞልኛል ይላሉ፤ አነዚህን ሰዎች ግን አንድም ቀን ጌታ በልቶልኛልና አልበላም ብለው አያውቁም፡፡ አንዳንዴም ስታናግሯቸው አኛ ጌታን ምሰሉ ነው የተባልንው ይላሉ ታዲያ ጌታን መምሰል እንዲህ ነው? መልሱን ለናንተ ትቼዋለሁ፡፡ እንደ ይሁዳ ወደ ገነት ለመግባት አቋራጭ መንገድ መፈለጉ ብልጣ ብልጥ ለመሆን መሞከሩ መጨረሻው ሞት ስለሚሆን በመጽሐፍ የተፃፈውን ተምሮ ጠይቆ ተረድቶ በቀደመችው መንገድ መጎዝ እንጂ አቋራጭ መፈለጉ አያዋጣም፡፡ "የዋሃን ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን የወርሳሉና" አንዲል ማቴ 5:-5 የተባልንውም እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ ነው፡፡ ከታሪኩ ከያዝኩት አንድ ካልኩ እናንተ ደግሞ በሕይወታችሁ መንዝሩት "-- ሃይማኖት አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አነዲት ናት--" ኤፌ 4:-4 ::
 አምላከ ቅዱሳን ይጠብቀን፡፡ አሜን፡፡

7 comments:

  1. Amen Egziabher yibarkachu Tiru Mikir azel new!!








    ReplyDelete
  2. qale hiwote Yasemalen tiru temehert neber

    ReplyDelete
  3. kALE HIWOT YASEMALEN BEWENET TILEK TIMHERT NEW

    ReplyDelete
  4. ድንቅ ምክር ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    ReplyDelete
  5. እግዚአብሔር ይስጥልን ። የማይገኝ ምክር ነው

    ReplyDelete
  6. Amazing!
    This is for my life!

    ReplyDelete
  7. የጥበብ ባለቤት እግዚአብሄር አምላክ ከዚህ የበለጠ ጸጋ ያድልልን መካሪ አያሳጣን

    ReplyDelete