ደቂቀ ናቡቴ

Monday, October 1, 2012

ቅዱስ ያሬድ ዜማውና 1500ኛ አመት መታሰቢያ ክፍል አራት


1500 ዓመት የቅዱስ ያሬድን በዓል ምክነያት በማድረግ ክፍል አንድ ክፍል ሶስት  "ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዜማውና 1500ኛ አመት መታሰቢያ"  በሚል ርእስ አስነብበናችኋል፡፡  ዛሬ ደግሞ በክፍል አራት የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች  በሚል ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶ ለዜማው መመሪያ እንዲሆኑ የፊደል ቅርጽ  የሌላቸው ስምንት ምልክቶ የፊደል ቅርጽ  ያላቸው  ሁለት የዜማ ምልክቶች አሉት፡፡ እነዚህ ምልክቶች በሙሉ ምሳሌነታቸው ስለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከልደት እስከ ዕርገት ላደረገው የመስቀል ጉዞ ነው፡፡

  •   ድፋት(  )ምሥጢሩ የክርስቶስን ከሰማየ ሰማያት መውረድ ያስረዳል፡፡

  •   ሂደት ( )ምሥጢሩ ጌታ በዚህ ዓለም እየተመላለሰ /እየተዘዋወረ/ ማስተማሩንና በተከሰሰም ጊዜ ከሐና ወደ ቀያፋ ወደ ሄሮድስና ወደ ጲላጦስ ምንም ሳይናገር መመላለሱን ያስረዳል፡፡

  •   ቅናት ( )ምሥጢሩ አይሁድ በጌታ ላይ መቅናታቸውንና ጮኸው አሳልፈው መስጠታቸውን ያስረዳል፡፡

  •  ይዘት ( ) ምስጢሩ አይሁድ ጌታን መያዛቸውን በሌላም በኩል እግዚአብሔር ዓለምን በመኃል እጁ የያዘ /አኃዜ ዓለም/ መሆኑን ያስረዳል፡፡

  •  ቁርጥ ( )ምሥጢሩ አይሁድ ጌታን ቢያሰቃዩትም አዳምን ለማዳን መቁረጡን ያስረዳል፡፡

  • ጭረት ( )ምሥጢሩ የጌታን ግርፋት /ሰንበር/ ያስረዳል፡፡

  •   ርክርክ ( )ምሥጢሩ ጌታ ሲገረፍ የተንጠባጠበውን ደም ያስረዳል፡፡

  •   ደረት( ) ምስጢሩ የጌታን ዕርገት ያስረዳል፡፡

  •   ድርስ // ትንቢት ሁሉ መድረሱን፣ መፈጷሙን ያስረዳል፡፡

  •   አንብር //ሁሉን ከፈ በኋላ በአባቱ ቀኝ መቀመጡን ያስረዳል፡፡

እነኝህ ምልክቶች ከሚዜመው ቃል በላይ የሚመለከቱ ሲሆን እስካሁን  በኮምፒውትር ለመፃፍ የሚያስችል ሶፍት ዌርም የሌለ ስሆን በቅርቡ ግን ይህ እንደተሞከረ ለማየት ችለናል ይህን እና ከቴክኖሎጂው ጋር ዜማውን እንዴት ማጥናት ይቻላል የሚሉትን ጉዳዮች ለወደፊት እንመለስበታለን ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ረድኤት አይለየን፡፡ አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment