Monday, September 24, 2012

ቅዱስ ያሬድ ዜማውና 1500ኛ አመት መታሰቢያ ክፍል ሶስት



ከባለፉት ሁለት ክፍሎች የቀጠለ
(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 14/2005)ቅዱስ ያሬድ ቀደምት የዜማ ምልክት ደራሲ መሆኑንም ጭምር ቤተ ክርስቲያን ለአለም የምታሳውቅበት ጊዜ ቢኖር ይህ 1500ኛ መታሰቢያ አመት ይመስለኛል ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ደግሞ እያንዳንዳችን ከዛሬ ጀምረን በየአጥቢያችን ታላላቅ በአላትን ተንተርሰን የሚዘከርበትን ሁኔታዎችን መፍጠር ይገባል ከመስቀል በዓል አከባበር ቢጀምር ባዮች ነን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ዑደት ስፍር ቀምር የራሷን  ዜማ ያደላደለች አፍሪካዊት እመቤት ናት ብንል ጽልመት ሊጋርደው የማይችለው ገሀድ ነው፡፡ 
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች 
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርስቶች በአምስት ይከፈላሉ እነዚህም ድርሰቶች አምስት ፅዋትወ ዜማ በመባል ይጠራሉ ፡፡ እነርሱም ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬ፣ መጽስዕትና ምዕራፍ ይባላሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍት ላይ የቅዱስ ያሬድ ድርስቶችን በዜማ ይተበh ደረጃ ልዩነት እና አንድነት ያላቸውን በመከፋፈል አራት ይላሉ አነርሱም ድጓ ቅዳሴ ዝማሬ እና መዋስዕት ይላሉ   ይህን የሚሉት ድጓ ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ አንድ አይነት የዜማ ይትበሀል ስላላቸውንደ አንድ ስለሚቆጥሯቸው በድጓ ውስጥ ስለሚያጠቃልሏቸው በመሆኑ አምስት ከሚሉት ጋር የሚጋጭ አይሆንም፡፡
·         ድጓ- ከጽሕፈቱና ከምልክቱ ብዛትና ክሳት የተነሳ ረቂቅ እስተግብዕ /ስብስብ/ ይባላል፡፡  ምክንያቱም የዓመቱን በዓላትና የሳምንቱ መዝሙራት ተሰብስበው ስለሚገኙ ነው፡፡ ድጓ ስብስብ ሙሾ፣ ቁዘማ መዝሙር፣ ሐዲስ፣ ፍፁም ማለት ነው ድጓ የቤተ ክርስቲያ ዜማ መድብል ሲሆን በውስጡ አራት ክፍሎች አሉ እነርሱም፡-
1.    ድጓ ዮሐንስ - ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የሚናገር ሲሆን፣ የዮሐንስን መንገድ ጠራጊነት የሐዲስ ኪዳንን መሸጋገርያነት አንስቶ የዘመረበት ነው የሚዘመርበትም ወቅት ከመስከረም 1  እሰከ ኅዳር 30  
2.    ድጓ አስተምሕሮ - ጌታችን ያሰተማረውን ትምህርት ያደረገውን ተዐምራት     የሚያነሳ ነው ማቴ.52  ማር1 39 የሚዘመርበት ወቅትም ከታህሳስ 1 እስከ መጋቢት 30፡፡
3.ድጓ ጾም - የድጓው ሦስተኛ ክፍል በዓቢይ ጾም የሚባል ነዉ፡፡
4.    ድጓ ፋሲካ - የጌታችንን ለዓለም ቤዛ ወይንም ፋሲካ ሽግግር ራሱን መስጠቱን ያነሳል የዕርገትን የጰራቅሊጦስንና የክረምትን ነገር ያነሳል የሚዘመርበት ወቀትም ከሚያዝያ/ከትንሳኤ/ እሰከ ጳጉሜን መጨረሻ፡፡

·         ጾመ ድጓ- በዐቢይ ጾም የሚደረስ ነው ጾመ ድጓ ቁጥሩ ከአስተም ሲሆን በውስጡ ስምንት ክፍሎችን የያዘ ነው ክፍሎቹም ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራበ፣ መጻጉ፣ደብረ ዘይት፣ገብርሔር፣ኒቆዲሞስ እና ሆሳዕና ናቸው፡፡
ከዘወረደ እስከ ገብርሔር ዜማው ግዕዝ ሲሆን የአብ ምሳሌ ነው ፡፡ በስድስተኛው ሳምንት /በገብርሔር / ዕዝል መሆኑ ወልድ በስድስተኛው ሺህ በሥጋ የመገለጡ ምሳሌ ነው ፡፡ በሰሙነ ኒቆዲሞስ አራራይ መዜሙ ወልድ ከዐረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በጽርሐ ጽዮን ለመውረዱ ምሳሌ ነው ፡፡
·         ዝማሬ- ምስጋና ማለት ሲሆን ይህም በማህበር የሚደርሰ ነው በቅዳሴ መካከል ከቁርባን በኋላ ከክብር ይእቲ ቀጥሎ ከእጣነ ሞገር በፊት የሚባል ነው፡፡  በውስጡ አምስቱ ክፍሎች አሉት፡፡ ክፍሎቹም ኅብስት፣ ጽዋዕ፣ መንፈስ፣  ምሰጢር እና አኮቴት ናቸው፡፡
  •       ዝማሬ ሕብስት የሕይወት መብል ስጋውን ያስታውሳል፡፡ 
  •       ዝማሬ ጽዋዕ የሕይወት ጽዋ ደሙን ያስታውሳል፡፡ 
  •       ዝማሬ መንፈስ መንፈሰ ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ፀጋውን እንዳሳደረብን ይናገራል፡፡ 
  •       ዝማሬ ምስጢር በማይመረመር ምስጢር ሕብስቱን ለውጦ ስጋው ወይኑን ለውጦ ደሙ አድርጎ እንደሰጠን ይናገራል፡፡ 
  •       አኮቴት  የሥጋውና ደሙ ማክበርያ ከሆነው ከቅዳሴ ጸሎት ወይንም አኮቴተ ቁርባን ጋር ጥብቅ ዝምድና አለው፡፡

መዋስዕት- አውሰዓ መለስ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው በውሰጡም የጌታችንን ጥምቀት ትንሳኤና ዕረገት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ምልጃና ረድኤት የያዙ ትምህርቶች ያሉበት የምጋና ክፍል ነው፡፡ ይህ ሰት ለሙታን መታሰቢያ ለሆሳዕና እና ለቅዳሜ ስዑር ይደረሳል፡፡ ማሬ ጋር አብሮ በመደረሱ በአንድ ወንበርም የሚሰጥ ትምሕርት በመሆኑ ሳይነጣጠል ዝማሬ መዋስዕት ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ በተጫማሪም በግራና በቀኝ እየተመላለስ /እየተቀባበለ የሚባል ነው/፡፡
ምዕራፍ፡- ማረፊያ መኖሪያ ማለት ነው የዜማዎችን ዓይነትና ረፊያዎችን ከፋፍሎ የሚነግረን ክፍል ነው፡፡  የዘወትር ዓመቱን ሳይጠብቅ በዓመቱ በዓላትና ሳምንታት የሚባል ነው፡፡ ዋዜማ ስብሐተ ነግህ መወድስ ክስተት የተባሉትን ያጠቃልላል፡፡

የጾም በወርሃ ዐቢይ ጾም በምሕላ ቀኖች የሚያገለግል ነው፡፡ ሠለስት አርባዕት  ንዑስ ምሕላ አበይት ምሕላ የሚባሉትን ይይዛል፡፡
ምዕራፍ:- የቃል ትምህርትም ይባላል፡፡ በውሰጡም የዜማ ተማሪዎች የሚማሯቸውን ትምህርቶች ይዟል፡፡ አነዚህም ውዳሴማርያም፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት መለኮት፣ አርያም፣ ክስተት እና መወድሰ ይባላሉ፡፡
ይቆየን…….ይቀጥላል
++++++++የቅዱስ ያሬድ በረከት ረድኤት አይለየን፡፡ አሜን+++++++++

1 comment: