Monday, September 3, 2012

ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ ልጅ ነው ምስጢረ ሥላሴንም አስተምሯል

በአካል በስም፣ በግብር ሦስት፣ በመለኮት፣ በባሕርይ በህልውና አንድ ሁኖ አንድ አምላክ እየተባለ ዘለዓለም ሲቀደስ ኑሯል፤ይኖራል፡፡
ሥላሴ በስም:- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡ በግብር አብ ይወልዳል፤ ያሠርጻል፤ ወልድ፤ ይወለዳል፤ መንፈስ ቅዱስ ይሠርጻል፡፡ በአካል አብም፤ ፍጹም አካል (ህልውና፤ ገጽ) አለው፤ እንደዚሁም ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ የተለየ ፍፁም አካላት አሏቸው። 

አካልና ሰውነትን ባለማወቅ ሰዎች ያደባልቋቸዋል፤ አካል ሦስቱም፣አብ ወልድ ፡ መንፈስ ቅዱስ ለእየራሳቸው አሏቸው ሰውነት ግን የሚጨበጥ የሚዳሰስ ያለው ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይኽውም ሥጋ በመልበሱ፡፡ በምስጢረ ሥላሴ አካል ለቀዋሚ ነገር ለመንፈስ ነው የሚነገረው፤ አይታይም አይዳሰስም፤ መንፈስ ነው፡፡ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ ረቂቅ አካሉ ስጋ ስለተዋሀደ የሚዳሰስ አካል አለው እንላለን፡፡

ባሕሪያቸው መለኮታቸው፣ መንግሥታቸው፣ ሥልጣናቸው ግን አንድ ነው፡፡ በአካል ሦስት ስለሆኑና በመለኮት፣ በባሕርይ አንድ ስለሆኑ፣ እኔ እያለ በነቢያት በክርስቶስ፣ በሐዋርያት፣ እግዚአብሔር ሲያናግር ኑሯል፡፡

  •   (ዮሐ. 1፡1-3) በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ይህ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ሁሉም በእሱ ሆነ፡፡ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም። ከዚህ ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ ጋራ ሌላ እግዚአብሔር ወልድ እንዳለ እና ያለእሱም ምንም እንዳልሆነ ይናገራል፤ በአካል የተለያዩ በመለኮት ግን አንድ የሆኑ፤ ሁለት አካላት፤ አንድ እግዚአብሔር እንድ እግዚአብሔር እንዳለ ወንጌላዊው ቁልጭ አድርጎ ገልጧል፤ ከዚህ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ አካላት አብና ወልድ ናቸው፣ ዝቅ ስንል ደግሞ ሦስት አካላት መሆናቸውን እናያለን፡፡
  •   (ማቴ.3፡16-17) ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኋ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ወርዶ ከእሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም ድምፅ ከሰማይት ወጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡ በዚህም በአምሰላ ርግብ የወረደው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፤ የምወደው ልጄ ያለ እግዚአብሔር አብ ፤ ተጠማቂው ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በትስብእቱ ዐማኑኤል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው፣በኋላ የቤተክርስቲያ ሊቃውንት ሥላሴ ብለው የሰየሟቸው አካላት፣ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡(ማር.1፡911፤ ሉቃ.3፡21-22)
  • ይኽው ታሪክ በድብረ ታቦርም ተደግሟል፣ ያውም ከትእዛዝ ጋራ፣ (ማቴ.17፡1-6፤ማር.9፡2-13 ሉቃ.9.28-36)"እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት፡፡"፥
  •   (ዮሐ.11፡4) ኢየሱስም ሰምቶ፣ ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ፡፡
  • (ዮሐ.11፡-፡27) አዎ!ጌታ ሆይ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ቁርአንና እስላሞች እንደሚሉት አምላክ ባይሆን ኑሮ፣ አይደለሁም ተሳስተሸል፣ እኔ አምላክ አይደለሁም ይላት ነበር፡፡
  • (ዮሐ12፡45) " እኔን ያየ የላከኝን አየ፡፡" ከዚህም ላኪና ተላኪ ሁለት አካል መኖራቸውን ይናገራል፡፡
  • (ዮሐ13፡3) ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደመጣ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ዐውቆ ከእራት ተነሥቶ ልብሱን አኖረ፡፡
  •   (ዮሐ14፡1) ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔርም እመኑ፣ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ---፡፡ ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት፣ ሕይወትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡ እኔንስ ብታወቁኝ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፡፡
  • (ዮሐ14፡15-17) ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ፡፡ እኔም አብን እለምነውዋለሁ፣ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላውን አጽናኝ እንዲሰጣቸሁ። እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ሰላሆነ ሊቀበለው የማይችል የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ከእናንተ ዘንድ በውስጣችሁም ስለሚኖርታውቁታላችሁ፡፡ በዚህም ሦስት መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አብን እለምነዋለሁ፤ መንፈስ ቅዱስ ይልክላችኋል ብሎ ፣ሦስቱንም፤ ተለማኝ ፣ ለማኝ ፣ተላኪ አድርጎ ሦስቱን አካላት ዘርዝሯል፡፡
  • (ዮሐ14፡23-24) ኢየሱስም መልሶ አለው፣ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፣ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን፡፡ የማይወደኝም ቃሌን አይጠብቅም (እንደአይሁድና እንደ አሕመድ ዲዳት ያለው)፡፡ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እጂ የኔ አይደለም፡፡
  • (ዮሐ14፡25) ከእናንተ ጋራ ስኖር ይህን ነገርኋችሁ፣ አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፣እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያስተውሳችኋል፡፡
  • (ዮሐ14፡31) ነገር ግን እኔ አብን እንደምወደው ዓለም ያውቅ ዘንድ አብ ያዘዘኝን ሁሉ እፈጽማለሁ፡፡
  • (ዮሐ.15፡9) አብ እኔን እንደ ወደደኝ እኔም እናነተን ወደድኋችሁ፡፡ (15) አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፡፡ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለነገርኋችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፡፡
  • (ዮሐ.15:21) የላከኝን ስለማያውቁ በእኔ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል፡፡
  •   (ዮሐ.15:23) እኔን የጠላ አባቴንም ይጠላል፡፡ (ዮሐ.15:26) ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ የምልከላችሁ የእውነት መንፈስ፣ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ፣ ስለኔ የመሰክራል፡፡ እናተም ከመጀመሪያ ጀምሮ ከኔ ጋራ አብራችሁ ስነበራችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡
  • (ዮሐ.16፡1-3) ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይህንም የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ሰለማያውቁ ነው፡፡
  • (ዮሐ.16:7-8) እኔ ግን እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፣ ምክንያቱም እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ (ጰራቅሊጦስ፣ መንፈስ ቅዱስ) ወደእናንተ አይመጣም፣ እኔ ከሄድሁ ግን ወደ እናንተ እልከዋለሁ፡፡ እርሱ በመጣ ጊዜ ስለ ኅጢአት፣ ስለፍርድና ስለጽድቅም ሰዎችን ያስረዳል፡፡
  • (ዮሐ.16:12-15) ገና የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ይከብዳችኋል፡፡ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ የመራችኋል፤ምክንያቱም እሱ የሚናገረወ የሰማውን እንጂ የራሱን አይደለምና ነው፡፡ እርሱ ወደ ፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግችኋል፤ የኔ ከሆነው ወስዶ ስለሚነግራችሁ ፣ እኔን ያከብረኛል፡፡---፡፡
  •   (ዮሐ.16:28) ከአብ ዘንድ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፣ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳሁ፡፡----፡፡ (ዮሐ.16:30) አንተ ሁሉን እንደ ምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማትፈልግ አሁን ዐወቅን፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፡፡
  • (ዮሐ.16:32፡) ነገር ግን አብ ከኔ ጋራ ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም፡፡
በጠቅላላ አባትና ልጅ መሆናቸውን ለማወቅ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ዐሥራ ሰባትን ያ፡፡
  • (ዮሐ.19፡7) አይሁድም እኛ ሕግ አለን፣ ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ስላደረገ በሕጋችን መሠረት ሞት ይገባዋል አሉ፡፡
  • (ዮሐ.10፡30) እኔና አብ አንድ ነን፡፡

ወስብሃት ለእግዚአብሄር
+++++የቅድስት ሥላሴ በረከት ረድኤት ቤተክርስቲያናችንን
አባቶቻችንን ኢትዮጵያ ሐገራችንን ይጠብቅልን++++++++

7 comments:

  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  2. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  3. በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚስጥረ ስላሴን አስተምሮአል?
    በአትናቴዎስ ድንጋጌ መሰረት አብ አምላክ ነው፣ኦልድ አምላክ ነው፣መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው ቢሆንም አንድ አምላክ እንጂ ሶስት አምላክ አይደሉም።በስላጣን አንዱ ከአንዱ አይበላለጡም፣በባህሪ አንድ ናቸው፣ሶስቱም ሁሉን ቻይ ናቸው. . . ታዲያ ኢየሱስ ይህንን አስተምሮአል?
    የጠቀስካቸው ጥቅሶች በሙሉ አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ በስልጣን፣በባህሪ በግብር አንድ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ?

    ReplyDelete
  4. Evidence for example these footprints, also as field observation by many researchers,
    indicate they they may be beings having an emotional
    and intellectual capacity very near those of human beings.
    Why not let all of the neighbors learn about your new arrival, by hanging a die-cut card stork from the
    porch, laminated to safeguard it through the elements.



    My web blog - best baby swing to buy [bookmark.softhc.com]

    ReplyDelete
  5. Robotic vacuum cleaner is the reality an automated gadget that tends
    to become that popularly used judging by doing work
    class it is undoubtedly plausible as though you do as pros also
    as cleansing their purchasing a household. Electrical suppliers can provide these
    gadgets and make our lifestyle simpler.

    Here is my web page - Different Vacuum Cleaner Styles For
    House And Workplace **

    ReplyDelete
  6. I'm not certain the place you are getting your info, but great topic. I needs to spend some time learning much more or understanding more. Thank you for wonderful info I used to be on the lookout for this information for my mission.

    Check out my web page: best stand mixers (tweet.nub.ro)

    ReplyDelete