መውተርተር
መግተርተር ይኑርህ መታታት
መማረክ
እጅ መስጠት ትሁን ለጠላት
ለማሸነፍ
ይሁን ሁሌም ፆም ፀሎት
ርዕይ
የሌለህ እንዳትሆን ከንቱ
ንደፍ
ተልዕኮህን አሳውቅ በብርቱ
መጓዝህን
አታቁም ለመድረስ ካሰብከው
ወደ
ኋላ አትይ ተስፋቢስ ዝርው ሰው
ነገ
ትደርሳለህ በአምላክህ ካሰብከው
ወላዋይ
ሰው ሆነህ አትጓዝ በሕይወትህ
አምላክ
ያለው አይቀር ይገባል ከእጅህ
ተፍጨርጨር
ሁል ጊዜም እስክታልፍ በሞትህ
አንኳኳ
አትሰልች እስኪከፈትልህ
እስኪሰማ
ድረስ በር መቺ መሆንህ
የበሰለን
ፍሬ አፍርቶ ታያለህ
ያሰብከው
ያቀድከው ውጥን ባይሳካ
እንዳልነበር
ቢሆን ሊጥህ ባየቦካ
አንደቀን
ይሆናል እያልክ ተመካ
ደግሞም
ካንተ አስወግድ መቀያየር አቋም
ቸር
አንደሆነ አስብ ሁሌም መዳሃኔአለም
የሚጎዳህን
አየቶ ከለክሎህ ቢሆንም
ይሰጥህ
ይሆንል ለአንተ ነገ የሚጠቅም
ታዲያ
መታገስህ ፍሬ ያፈራ ለት
ጾም
ጸሎት ስግደትህ ሲደርስ ከፀባዖት
ጊዜ
ያለው አምላክ ይሰጥሃል ወተት
አንተ
ብቻ ታገስ ፍሬዋን ለመብላት
Amen
ReplyDeleteIt is perfect time to make some plans for the long run and it is time to be happy.
ReplyDeleteI've learn this submit and if I may I wish to suggest you some interesting things or tips. Maybe you can write subsequent articles relating to this article. I want to read more issues approximately it!
my web page :: ballard massage center