Thursday, August 16, 2012

የፓትርያሪኩ እረፍት


ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት ንጋት ላይ አርፈዋል፡፡
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር! 
አባ ጳውሎስ ባደረባቸው ህመም ዛሬ ነሐሴ 10 ከንጋቱ 11.00 ሰዓት ላይ በ76 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡

ባለፈው እሁደ ነሐሴ 6 2004 የመጨረሻ የቅዳሴ ሰነስርአቱን በቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የመሩት ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያናችንንም በፓትርክና ለ20 አመታት ያህል ሲገለግሉ ነበር፡፡
ጠዋት ላይም እንዳስነበብናችሁ ፓትሪያርኩ ማረፋቸውን ገልጸንላችኋል ከስፍራው ተገኝተን የቅዱስነታቸውን ዕረፍት አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ለተገኙት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለምእመናንና ምእመናት ባስተላለፉት መልእክት የቅዱስ ፖትርያርኩ ዕረፍት የመላው ዓለምና የቤተ ክርስቲያኒቱ ኀዘን መሆኑን ገልጸው የቀብራቸውን ቀን እና ስነስረአት አስመልክቶና ተያያዥ ጉዳዮችን በቀጣይ የሚገለጽ እንደሆነ እና አሃት አብያተ ቤተክርሲቲያናት እና የአለም ሃይማኖቶች የሰላም አባቶች ተወካዮቻቸውን እስከሚልኩ የሚጠበቅ መሆኑን ተገልጧል፡፡
በስፍራውም በነበርንበት ሰዓት ከፍተኛ ሀዘን የሚታይ ሲሆን ብዙዎችም በእንባ ታጥበው ጮኽው በማልቀስ ላይ ነበሩ ፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቅዱስነታቸው ማረፋቸው በአሁኑ ሰዓት ካለው የቤተክርስቲያን ሁኔታ አንፃር ብዙዎች ነገር በስጋት ላይ ይገኛሉ፡፡
ብዙዎቹን እንደሚያሰጋውም የፓትሪያርኩ ደጋፊዎች የነበሩ ክፍተቱን ተጠቅመው ሊፈጥሩት የሚችሉት ብጥብጥና ተጽእኖ በቤተክርስቲያን ላይ ግጭት እንዳይነሳና ምክንያት እንዳይሆን ተፈርቶአል፡፡
ሌሎችም ስልጣናቸውን ተጠቅመው ድብቅ ሴራቸውን እና ቤተክርስቲያንን ወደ ማያባራ ችግር እንዳይከቷት የቤተክርሲቲያን አባቶች ሊያስቡበት እንደሚገባ እየተነገረ ነው፡፡
ይህንኑ ተከትሎ የቤተክርስቲያናችንን ታላላቅ ቅርሶችና ሀብቶች ሊያሸሹ የሚችሉ ኃይሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተፈርቶአል፡፡
ምንም እንኳን የቅዱስነታቸው እረፈት ያልታሰበ አደጋ ቢሆንም ከዋልድባ  ገዳም ላይ ሊገነባ ከታሰበው የስኳር ፋብሪካ  ጉዳይ ጋርም ያያዙትም አሉ፡፡
ሌላው ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በቤተክርሲቲያኗን ላይ ሊደርሱት የሚችሉት ችግሮች ከመታደግ አንፃር  ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ እና ምዕመናኑን ሊያረጋጉ እንደሚችሉ  ይጠበቃል፡፡ 
ከዛሬ ጀምሮ ቅዱስ ሲኖዶስም ወይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ 



በቀጣይስ ማን በወንበሩ ይቀመጣል?
በ1991 ዓ.ም የወጣውና በሥራ ላይ የሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያን
ፓትርያርክ ድኅረ ዕረፍት ወይም ከሥልጣን መውረድ (አንቀጽ 16) ኹኔታዎች
በአንቀጽ 17 ንኡስ አንቀጽ 1 – 3 የሚከተለውን ይላል፡፡
አንቀጽ 17 - ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ
  1. ፓትርያርኩ በሞት ሲለይ ወይም በዚህ ሕግ አንቀጽ 16 መሠረት ከሥልጣኑ ሲወርድ ቅዱስ ሲኖዶስ በሹመት ቀደምትነት ካላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በዕለቱ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ መርጦ ይሾማል፡፡ የተተኪው ፓትርያርክ ምርጨም ይካሄዳል፡፡
  2.  ተተኪው ፓትርያርክ ምርጫ አፈጻጸም እንደጊዜውና እንደ ሥራው ኹኔታ እየታየ ከ40 እስከ 80 ቀን ባለው ጊዜ ይኾናል፡                                                                                        የዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ተግባር፡-
ሀ) ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ጊዜያዊ ጉዳዮችን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋራ እየመከረ ያከናውናል፡፡
ለ) በፓትርያርኩ ምርጫ ጊዜም የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ኾኖ ምርጫውን ያስፈጽማል፤ እርሱ ግን ከምርጫው አይገባም፡፡
ሌሎች ዜናዎችን ይጠብቁን
ቸር ወሬን ያሰማን፡፡

38 comments:

  1. God bless Ethiopia Ebakachihu Ahun Bole medahinialem Ylewu Hawult Endiferess Ahun bidereg Egnam dimtsachinin Enasema

    ReplyDelete
    Replies
    1. Oh my GOD... this website does not look like a religious one. I can't understand the agenda behind...Please, if you are Orthodox act like Orthodox christian. Abune Pawlos has been our religious father till this day. Give recognition for this Big religious father. He has done many things for the church and also to the country. When we are

      Delete
    2. Ahun sile Hawelt Mafres yeminegerbet gize aydelem. Keahun jemiro kiffiflun masawek new... Tilk abat nachew Haweltum ygebachewal. Endene Amelekaket Yihnu talak sew lebete kiristianwam yhun leageritu tilik neger sertewal. Yegil amelekaketachin ena sebawi amelekaketachin titen ende haymanot sewoch binasibis.

      Delete
    3. Ere endehaymanotawi bicha sayhon endesewm mehon yakaten ymeslengal. He has been a good leader. So give recognition

      Delete
  2. May Lord have mercy upon the soul of His Holiness Patriarch Abune Paulose of Ethiopia

    ReplyDelete
    Replies
    1. liked that. May HE bless you too!

      Delete
  3. ትክክል እነ ሆደ አምላኩ ዛሬ ሊጠቀሙ ይችላሉ በቁራኛ ልንመለከታቸው ይገባል ባይ ነኝ እሳቸውን ግን አምላክ ነፍሳቸውን ይማር፡፡

    ReplyDelete
  4. ሰው ጥሩም ሰራ መጥፎ ከሞተ ብኋላ አይከሰስም ክፋቱም አይነገርም ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን በጎ ስራ ማጉላቱ የተሸለ ነው ባይ ነኝ፡፡

    ReplyDelete
  5. . አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
    . ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
    . የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
    . ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል:: (ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
    . “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን” ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
    . በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል

    ReplyDelete
    Replies
    1. God gave wisdom to human creature so that Ethiopia a Gd blessed country never & ever colonized whatever methodolgy used by the west111

      Delete
  6. ብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቀ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሓይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዘዳንት ንጋት ላይ አርፈዋል፡፡

    ReplyDelete
  7. May Lord have mercy upon the soul of His Holiness Patriarch Abune Paulose of Ethiopia

    ReplyDelete
  8. May Lord have mercy upon the soul of His Holiness Patriarch Abune Paulose of Ethiopia

    ReplyDelete
  9. ምንድነው ለሀሜት መቸኮል መሞታቸው ትንሽ ያሳዝናችሁም እንደሰው? ሥልጣንና ለገንዘብ መባላት ምን ማለት ነው? እግዚአሔር ወደ ታች ይመለከተናል

    ReplyDelete
  10. እውነት ነው አቡነ ጳውሎስ አርፈዋል ነፍሳቸውን ይማረው

    ጥያቄው ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? ነው የሚያስጨንቀንና እስቲ በሰከነ መንፈስ እንወያይበት ማን ያውቃል ከኛ ከደካሞች የቅዱሳን አምላክ ጠቃሚና አባቶቻችን ሊጠቀሙበት የሚችሉት ሃሳብ እንዲፈልቅ ያደርግ እንደሆን?

    ReplyDelete
  11. O Geta Hoye Betekerstiyanachenen Tebek!

    ReplyDelete
  12. Hawulet mesrates ahune new

    ReplyDelete
  13. Egzeabhare sira yemiserabet gize alew. lebete kiristianachin yemibejewun yamtalin!!!

    ReplyDelete

  14. አባ ጳውሎስ የመለሰ ዜናዊን መታመም ሰምተው ለማጥመቅ መስቀላቸውን ይዘው መለሰ ዜናዊ ካለበት ክፍል ይደርሳሉ።
    ልክ እንደ ደረሱ:-
    መቼም አንተ እምነት የለህም። ላጥምቅህና ከዳንክ ታምናለህ ይሉታል።
    መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- በጣም ተጨንቋልና ኧረ አሁንም አምናለሁ አጥምቁኝ ይላቸዋል።
    አባ ጳውሎስም:- መስቀላቸውን አንስተው ማየ ጸሎቱን ከባረኩ በኋላ አጠምቀከ በስመ ሕወሃት፤አጠምቀከ በስመ ብአዴን፤አጠምቀከ በስመ ኦሕዴድ ሲሉት ይጮህ ጀመረ።
    አባ ጳውሎስም:- ማነህ ልቀቅ ? ሲሉት
    መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- አልለቅም አበበ ገላው ነኝ ፤ አልለቅም አበበ ገላው ነኝ ፤አልለቅም አበበ ገላው ነኝ፤ አልለቅም አበበ ገላው ነኝ እያለ melese zenawi is Dicator, melese zenawi is Dicator, melese zenawi is Dicator Free Iskinder Nega and all political prisnors! We need freedom! Food is nothing without freedom! እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲያንጎደጉድባቸው።
    አባ ጳውሎስም:- መጮህህን ትተህ ትለቃለህ አትለቅም? ሲሉት
    መለስ ላይ ያለው አጅሬ:-:- ሳልገድል አልለቅም ይላል።
    አባ ጳውሎስም:- እንባ እየተናነቃቸው እባክህ ልቀቀው ይሉታል።
    መለስ ላይ ያለው አጅሬ:- እለቃለሁኝ ግን እሱን ከለቀቅኩኝ ወደ አንተ ተዛውሬ አንተን ነው የምገድልህ ይላል።
    አባ ጳውሎስም:- አይ በቃ ተው። እዛው እንደ ጀመርክ ጨርስ። እኔ ትንሽ ልሰንብትበት ብለው ማጥመቁን ትተው ወደ ቤታቸው ሄደው አልጋ ላይ ሰነበቱ።
    ትንሽ ልሰንብት እንዳሉ ላይመለሱ ሄዱ።
    ነፍሳቸውን በመለስና በሕወሃት አጠገብ ያሳርፍልን። አሜን!!!!!!



    ReplyDelete
    Replies
    1. ወለተ ማርያምAugust 16, 2012 at 11:14 PM

      ወንድሜ ይህን ቀልድ ብለህ ከሆነ በጣም ያሳዝናል ትንሽ ሰብአዊነት የሚባል ነገር አታውቅም፡፡ ደግሞ አንተ እውነት ክርስቲያን ከሆንክ ክርስቲያን በወንድሙ ጉዳት አይዘባበትም እሳቸው ወደማይቀርበት ሄደዋል ፍርድ ድግሞ ከእግዚአብሄር ነው ደግሞ አትርሳ እግዚአብሄር የፍቅር፣ የምህረት፣ የቸርነት አባት ነው፡፡ እንደሚመስለኝ መሞታቸውን ከእግዚአብሄር የመጣ ቅጣት አድርገኸዋል አትሳሳት ሞት በማንም የማይቀር እዳ ነው፡፡ ለማንኛውም በሰዎች ላይ ለመፍረድ አንቸኩል በጉዳታቸውም አንደሰት ፍርድ ከእግዚአብሄር ነው ይቅር ማለትንም እንልመድ ፡፡

      Delete
    2. ቀልዶች ሁሉ ቢልቁበሀ ነድዚሀ አይነት ቀልድ አይቀለድምቀልዶች ሁሉ ቢልቁበሀ ነድዚሀ አይነት ቀልድ አይቀለድም

      Delete
    3. believe or not- u gonna be under we tigrians for the next 20-30 year...bitch!!...u will remain shouting all your life,ahya!!

      Delete
    4. I think you are among the donkey once and nothing is expected from you except this

      Delete
  15. Please our brothers and sisters let us not be curse other whatever did they made,this is not what the Bible teach us. Most of us did not now the patriarch but we judge as if we have been with him,without knowing the different side of the did why he did so.finally, even Christ was crucified by his own people due to the accusation of individuals.so that let us pray to rest in peace.

    ReplyDelete
  16. Nefese yemar Leabewu Ayebalem! Yeh Blog ye Othodox kehone yesetekakel

    Bereketachew Yedereben Yebale!!!

    Amene Bereketachew Yedereben

    Dn. Ledet Z Awassa

    ReplyDelete
  17. god bless his soul and don't worry god know about Ethiopia!

    ReplyDelete
  18. አምላክ ሆይ ነፍሳቸውን ይማር..

    ReplyDelete
  19. May God put His soul as His dead on Erth!!!

    ReplyDelete
  20. ቦሌ መድሐኔአለም ያለውን የበፊቱን ሃውልት አፍርሰን አሁን አዲስ ሃውልት መስራት አለብን ለእኔ ታላቅ አባት ናቸው፡፡

    ReplyDelete
  21. Yalefew alefe mut mewkes eko bebahilachen newer new. yilik ketay yebetekirstiyanachen eta mindinew negeroch memer lekew ye menafekan mezebabecha endanhon egziabher amlak betekristiyanachenen yitebkelen. Amen!

    ReplyDelete
    Replies
    1. በርግጥ የሳቸው ሞት ለቤተክርስቲያኒትዋ እረፍት ነው እንዲሁ ስታዘባቸው አንባገነን መሪ/አባት/ ነበሩ፤ ለእርቅ የተሰበረ ልብና ሃሳብ ያልነበራቸው ገታራ አባት! የቀድሞው ሊቀ ጳጳስ በህይወት እያሉ መንበረ ስልጣኑን መቀበላቸውንም ሲተቹበት ነበር ! ያም ሆነ ይህ ያለፈው አልፎአል! የቀድሞው ፓትሪያሪክ ወደ መንበሩ መመለስ አለበት! ነብሳቸውን እግዚሃብሄር ይማርልን!

      Delete
  22. በኢትዮጵያ ቤ/ን ታሪክ ቤተ ክርስቲያኒቱን ካስተዳደሩ አባቶች መካከል እጅግ አነጋጋሪና አከራካሪ የነበሩ ሰው ቢሆንም በፓትሪያሪክነት ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንኙነቷንና ተሰሚነቷን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ አስተዋእፆ የነበራቸው አባት እንደነበሩ በብዙዎች ዘንድ ይነገርላቸዋል፡፡ RIP

    ReplyDelete
  23. This is a really good tip especially to those new to the blogosphere.
    Short but very accurate information… Thanks
    for sharing this one. A must read article!
    Also visit my blog :: my blog named kip

    ReplyDelete
  24. This article is really a nice one it assists new net visitors, who are wishing
    for blogging.

    my page ... Cooking Simple Vegetables

    ReplyDelete
  25. An impressive share! I have just forwarded this onto a coworker who
    was doing a little research on this. And he actually
    ordered me lunch due to the fact that I discovered it for him.
    .. lol. So allow me to reword this.... Thanks
    for the meal!! But yeah, thanx for spending the time to discuss this issue
    here on your site.

    Here is my web site Cooking Simple Vegetables

    ReplyDelete
  26. Well, with natural care and some planning, you'll be able to experience the bliss of pregnancy. Finally, when selecting a daycare center, consider one close to home to help you at least try and reduce the danger of your child falling asleep around the way home.

    My web blog: Obtaining No-Hassle Merchandise For baby swing

    ReplyDelete
  27. Your area is no cost from clutter, like objects are grouped with
    each other and all the things has become put into its
    logical spot. This is often why these mat cleaners even need to
    get the job done overtime in the course of weekends or in the night so as to survive
    within the career devoid of obtaining fired.

    my webpage A Guidebook To Speedy Methods In vacuum cleaner

    ReplyDelete