Monday, August 6, 2012

ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ጀርባ


መናፍቅ ማለት ከፍሎ የሚያምን ሙሉ እምነት የሌለው ማለት ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማያምን ሰው መናፍቅ አይባልም። ከሀዲ ወይም አህዛብ ይባላል እንጅ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ አምናለሁ ብሎ ነገር ግን ሙሉ የክርስቶስንና የአባቶች ውሳኔዎችን የማይቀበል አካል መናፍቅ ይባላል። መጸሐፍ ቅዱስ እና አዋልድ መጻሕፍት ስለአምላክ ማንነት የሚናገረውን የማይቀበል፡ የአምላክን ፈቃዳትና ትእዛዛት በተዛባ መልኩ የሚያስተምር መናፍቅ ይባላል።
 
ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት በተሃድሶ መናፍቃን ዙሪያ የተለያዩ ስልት በመጠቀም ቤተ ክርስቲያኒቷን ለመከፋፈል ብዙ ብዙ ጥረት ማድረጋቸውን አስነብበናችኋል ዛሬስ የሚጠቀሙበት ስልት አላዋጣ ሲል ምን እየሰሩ ይገኛሉ? ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሁለት ሺሕ ዓመት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርሰቲያን ትሁን እንጂ መንበሯን ከሊቀ ጵጵስና ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን ገፍታለች፡፡
በዚህ ማለፏ ደግሞ ሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት የአደረጃጀት ችግር እንዳጋጠማትና ልጆቿን ጊዜው በሚጠይቀው መንገድ ለመሥራት የሚያስችላትን አካሄድ እንዳትጠቀም አድርጓት መቆየቱን በሚገባ እንገነዘባለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ያለማቋረጥ የተደራረበባት ችግር ሐዋርያዊ ተልእኮዋን እንዳዳከመውና ሊቃውንቷንም ተጠራጣሪና ተከላካይ ብቻ እንዳደረጋቸው ሁሉ የራሷ ሲኖዶስ ሳይኖራት ለረጅም ዓመታት መምጣቷም አሁን ያሉባት ችግሮች የአሁን ብቻ ላለመሆናቸው ጠቋሚ መሆናቸውንም እንረዳለን፡፡ ይሁንና  በአሁን ጊዜ ግን በጣም በተቀናጀና በተጠና ስልት የቤተክርስቲያን አስተምሮ ያልቀየሩ በማስመሰል የአቋም ለውጥና የአቅጣጫ ለውጥ በማድረግ የተማሩ  ብለን የምናስባቸውን  ሊቃውንት በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ የስልጣን ደረጃ ያሉትን የቤተክርስቲያን አመራር አካላትን ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ጀርባ በመጠቀም የተጠና የረቀቀ ስልታቸውን አጠናክረውበታል በተለይም በቤተክህነት ደረጃ ያሉትን ካህናትን ለዚህ አላማቸው ማስፈፀሚያ ሲጠቀሙባቸው እንመለከታለን፡፡በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን ሳያምኑ እኲይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ቤተ ክርስቲያኒቷን ጥግ ያደረጉትን እንደ ሰሞኑን የተሐድሶ መናፍቃን መልክ ያሉትን የጥፋት ቡድኖች ደግሞ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም በሃይማኖታዊ ጥብዓት ሁሌም የምንታገላቸው ይሆናል፡፡


በተለያዩ ጊዜም እነርሱ ገነው የሚወጡበት የአመራር ደረጃን የሚቆናጠጡበትን ጊዜ ሲናፍቁ እና ሲያልሙ የሰነበቱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው አድርባዮች፣ ባይሳካ ደግሞ ጊዜው ሳይነጋብኝ በማለት ሌት ተቀን እነ እገሌን በምን መልክ እናጥፋቸው እነ እገሌንስ በምን ኃይል አቅም እናሳጣቸው የሚሉ የነገር አባዜ ሲያውጠነጥኑ የሚኖሩ እና ያሉ ከቤተ ክርስቲያን ልዕልና ይልቅ የራሳቸውን  ጥቅም በማስቀደም ቤተ ክርስቲያንን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት የሚራወጡ እረ ምኑ ቅጡ…………ለሁሉም በአሁን ጊዜም ያለውን የእነዚህን እንቅስቃሴ ለወደፊት ከመረጃ ጋር የምናስነብባችሁ ይሆናል፡፡
በአሁን ጊዜ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች  ላይ ስለሚወጡ ኢኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎችን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመንዛት ላይገኛሉ፡፡ ተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴዎችን እያጠናከሩበት  ያለው ሁኔታ እያመጣ ያለው ተፅእኖ ይህ ነው የሚባል አይደለም:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ  በማስመሰል ነገር ግን ማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው  የሚያወጣቸው ጽሑፎች ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የሚቃረኑ የምዕራባውያኑ የፕሮቴስታንቶች ልሳን በማዋዛት የእኛ አስተምህሮ በማስመሰል በከፍተኛ ሁኔታ ሲያጧጡፉት እናያለን:: ቤተ ክርስቲያናችን ለሚያውቃት ምልዑ ናት:: ለሁሉም መልስ አላት:: የቀደሙት አባቶቻችን ብራና ፍቀው በደማቸው ቀለም በጥብጠው ሁሉንም ነገር አሟልተው መጽሐፍት አስቀምጠውልናል:: በየጊዜው ለተነሱት መናፍቃን ተገቢውን ምላሽ እየሰጡ አሳፍረው መልሰዋቸዋል::  አሁን እደ አዲስ የተነሱት የተሐድሶ መናፍቃን አቀንኞች የቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት/መድረክ ሲያጡ የቅሰፋ ትምህርታቸውን በኢንተርኔት ማሰራጨታቸውን ቀጥለውበታል:: 

በቤተክርስቲያኒቷ ስም ድረገጾችን በመክፈት የተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴዎችን የሚረዱ እውነተኛ መስለው የተሃድሶ አስተምህሮችን የሚያወጡ ብሎጎች ዛሬ ዛሬ  በጣም ተበራክቶና ተጠናክረው የቀጠሉት ጊዜ ነው ያለንበት ሌላው ይቅርና ቅዱስ ሲኖዶሱ በትክክል አስተምህሮችውን መርምሮ አካሄዳቸውን አጥንቶ ቤተ ክርስቲያኗን እንደማይወክሉ አውግዞ የለያቸውን ማህበራትን እና ግለሰቦችን ለምን ተነኩብን በማለት “እገሌ እኮ የፃፋቸው ፅሑፎች ሊያስወግዙት አይገባም“ በማለት ምዕመናኑን ለማደናገር ሲኖዶሱን ከተአማኒነት፣ በውሳኔውም ምዕመናን እምነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ እና ለወደፊትም ቅዱስ ሲኖዶሱ መረጃዎችን በመመርመር በሚያወግዛቸው እና በሚያስተላልፈው ውሳኔዎች ላይ ህዝቡን በውንዥብር ውስጥ  ለመክተት፣ ምዕመናኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ተአማነት እንዲያጣ እና ከዚህ በፊት እና እገሌን በተሳሳተ መረጃዎች አወገዘ ዛሬ ደግሞ እነ እገሌን ማውገዙ ፈጽሞ ስህተት ነው ለማለት የሚያስችላቸው አቅም ለማግኘት ሲጣጣሩ ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ፡፡ እኛ ግን ዛሬም ብፁዓን አባቶቻችንም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን እና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት አድርገው በፕሮቴስታንታዊ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችና እንዲሁም አቀንቃኝ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የማያዳግም ውሳኔ ይወስናሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡
በማኅበራው ድህረ ገፆች በመጠቀም ምዕመናኑን የሚያደናግሩ ብሎጎች በተቻለ ለወደፊት የምንገልፅላችሁ ቢሆንም በፌስ ቡክ ገፆች ላይ መንፈሳዊ ወይም ኃይማኖት ነክ መልዕክቶችን የያዙ ጽሁፎች በሰፊው ሲወጡ ይታያሉ ብዙውን  ቦታ የሚይዙት ደግሞ የእኛን እምነት እና ትውፊት ተመርኩዘው የሚወጡ የተለያዩ ፅሁፎች ናቸው::ታዲያ ርዕሳቸው ተዋህዷዊ የያዙት ስዕላትም የእመቤታችንን አሊያም የቅዱሳን ሆኖ ውስጡ ግን የያዘው የመናፍቃን መልዕክትና ሃሳብ ነው:: በዚህም የብዙ የዋህ ምዕመናን ልብ ለመክፈል እና ተጠራጣሪ ለማድረግ እየተሞከረ እና እየተደረገም ነው:: በፌስ ቡክ ገፆች ላይ የሚወጡ ፅሁፎችን ምዕመናን ከመጠቅማቸው በፊት እና የፌስቡክ ጓደኛም ከማድረጋቸው በፊት ማንነታቸው በተቻለ መመርመር ይገባል፡፡ አንዳንድ ገፆች የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ ለማስመሰል ብዙ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የቤተክርስቲያናችንን ለዛ የያዘ መሆን አለመሆኑን አንድ በቤተክርስቲያን ካደገ ምዕመን የሚጠፋ አይደለም፡፡
የቤተ ክርስቲያን የቋንቋ አገላለፅ፣ የቋንቋ አጠቃቀም ውበት፣ የእመቤታችንን ክብር እና የቅዱሳንን ክብር የሚገልፁ ፅሁፎች የማይታይባቸው፣ የቤተ ክርስቲያንን ቃና የምናጣባቸው ይባስ ሲለ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን  ሰላምን ከመስበክ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ሰላም እንዳይኖር መለያየትን የሚሰብኩ ሁል ጊዜ የአንድ ማኅበሩን ጥፋት ሲከሱ እና የእርሱን ውድቀት ሲመኙ የሚታዩ ድረገፆች ከቀን ቀን እየተፈለፈሉ ያሉ የሳጥናኤል ቀኝ እጅ ሆነውለት ሳጥናኤል በስራ እያገዙት የሚገኙ የትየለሌ ናቸው በተለይ ፈጽሞ የመናፍቃንን ስራ የሚሰሩት ድረገፆችን ብንመለከት አባ ሰላማ፣ አውደ ምህረት፣ ደጀ ብርሃን፣ መረዋ ፣ጮራ፣ ደጀ ሰላም(በእንግሊዘኛው DejeSelaam)…… ከዋናዋናዎቹ መሃከል ሰሆን በፌስ ቡክ ገፆች ደረጃ ግን ብዛታቸውን የትየለሌ ነው አንዳንድ የፌስቡክ ገፆች በሰም ደረጃ እንኳን  አባ የሚሉ ቅፅሎችን በመስጠት ምዕመናንን  ትክክለኛ አባቶች በመምሰል በውስጥ መፃፃፊያ (messages) በመጠቀም የሚያወናብዱ………. ይህን ሁሉ ማንሳታችን ምዕመናን በቤተክርስቲያናችን ዙሪያ እና ውስጥ የሚሰሩ ድብቅ ተንኮሎችን ተረድተው የየራሳቸውን ጥረት እንዲያደርጉ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እና ሁሉንም አስተምህሮ ዝም ብሎ ከመቀበል መመርመር ስለሚገባ ጭምር ነው ምዕመናን በተቻለው አቅም ፅሑፎችን ለጓደኞቻቸው ከማስተላለፋቸው በፊት ፅሁፍን መመርመር ይገባል እያልን በዚህ እኩይ የጥፋት መንገድ ግንባር ቀደም አባላት ተደርጋችሁብሎጎች፣ በፌስ ቡክ ገፆች በድብቅ ይህን የምታራምዱ የቤተ ክርሰቲያናችን ተባባሪ መምህራን እና ሊቃውንትም ጊዜው ሳይረፍድ ከዚህ የጥፋት ቡድን ራሳችሁን ነጻ በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ጥብቅና ትቆሙ ዘንድ ከልባችን እንለምናችኋል፡፡
ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት፤ በአንዲት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከመናፍቃን ይጠብቅልን፡፡

13 comments:

  1. ሌሎች ብሎጎች እና የፌስ ቡክ ገፆች አሉ ሊጠቀሱ የሚገባቸው ባይ ነኝ

    ReplyDelete
  2. ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት፤ በአንዲት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን

    ReplyDelete
  3. እረ እባካቹ Font-Color ሌላ አድርጉ!!! background: black አድርጋችሁ ይህን የጽሁፍ ቀለም መጠቀም በጣም የማይስማማ ነገር ነው::

    ReplyDelete
  4. yasikal Yebekristian anegager yetignawu newu???

    ReplyDelete
  5. betam bezu merejawoch alugne gen bezi zemen man tameno leman yenegeral medehenalem kirestos ersu becherenetu betekirestianachenen yetebek

    ReplyDelete
    Replies
    1. wendimachin ene yemlew mereja yizo maskemet new yemishalew weyis bemerejaw lelaw endimar lelelaw masawek? ene yemimekireh eda endayihonbih!!!

      Delete
  6. በርቱ በርቱ በርቱ

    ReplyDelete
  7. Bete Pawlos,deje semay lemn Alitetekesem minim ortodoxawi leza yelewum bay negn

    ReplyDelete
    Replies
    1. Bete Pawlos ewenetegha yetewahedo astemeherote yalewena maneneme yemayekese yewenegelune ewenatena yemadanune eweneta yememasekere dinke yebetechrestyane bloge newe GOd bless Bete Pawlos

      Delete
    2. And tiyake Alegn meche new Bete Pawlos sil Kidusan Amalaginet Afun molto Yiminagerew ? yimeleslgn yetu gares yihin endemeseker

      Delete
  8. wengel yashnifal sewer deba yelem

    ReplyDelete
  9. Bete pawelose ena mesekere negn egeziyabehar benesu laye adero gobegnetognal..bezu neger asetemerognal!!! laloch belogoch yegatan yemadanune sera tetewe sele,sewe siyaweru newe yemiwelut ..pete pawelose gene bedenebe mesebeke yalebeten Crisetosen asayetewenal...Egeziyabehar yebarekachew!!!!!

    ReplyDelete