Friday, December 7, 2012

♥አባ ሊቃኖስ ዘእምተሰዓቱ ቅዱሳን♥



በስመ ሥላሴ
ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ አባ ሊቃኖስ ዘእምተሰዓቱ ቅዱሳን
“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅመ እግዚአብሔር”(“የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭፡፲፭ (115፡15)
“እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” ሐዋ.፬፡፳ (4፡20)
የቅዱሳን ሕይወት ተርታ ታሪክ ወይም ተረት አይደለም ይልቁንስ እግዚአብሔርን የሚከተሉና በሥራቸው ሁሉም የእርሱ ጥበቃ ያልተለያቸው ሰዎች ታሪክ ነው። (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)
 የተሰዓቱ ቅዱሳን ሐዋርያዊ ተልእኮ መቅድም
ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አልአሜዳ በነገሰ በአምስት ዓመት ነው።
 እንደመጡት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በአክሱም ዐስራ ሁለት ዓመት ኖረዋል።
ተሰዓቱ ቅዱሳን በስም አባ አሌፍ፣ አባ አረጋዊ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጵሕማ፣ አባ አፍጴ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ይምዓታ፣ አባ ጉባ ይባላሉ። እኚ አባቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ዝም ብሎ አልተቀመጡም፤ ለሥራቸው በር ከፋች የሆነውን ቋንቋ፣ የሕዝቡን ባህል ጠንቅቀው ካወቁ በኋላ ላይ በአንድ አከባቢ ከመኖር ይልቅ መንፈስ ቅዱስ በመደባቸው ቀጥታ ማስተማርን መርጠው መንፈሳዊ ዓላማቸውን ለማሳካት የአክሱምን ነገስታት እርዳታና ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። እኚው ተሰዓቱ ቅዱሳን የመጡበት ሀገራት ሮም፣ እስያ፣ አንጾኪያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ቂሳርያ፣ ኪልቂያ ሲሆን በነበሩበት ጊዜያትም፡-
. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጽንቶልናል።
. መጽሐፍትን ተርጉሞልናል።
. ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል።
. ብዙ ገዳማትን መስርተዋል።
. ሥርዓተ ምንኩስናን አደራጅተዋል።
 ስለ እነዚህ ቅዱሳን ይህችን ታህል ካልኩኝ በዛሬው የዕረፍት በዓላቸው የሚታሰበው ከእነዚሁ ቅዱሳን አንዱ ስለሆኑ  ስለ አባ ሊቃኖስ ትንሽ ልበላችሁ።
አባ ሊቃኖስ 
ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አክሱም ከቆዩ በኋላ ለስብከት  በዮሓ ክፍላቸው ሲሰማሩ አቡነ ጰንጠሌዎንና አቡነ ሊቃኖስ ርቀው እንዳይሄዱ ሕዝቡ ስለተማጸናቸው ከከተማ ሳይርቁ አምስት ምዕራፍ ርቀት ገዳማቸውን መሠረቱ። አቡነ ሊቃኖስ ከአክሱም በስተ ሰሜን ከሚገኙ ደብረ ቆናጽል ከሚባለው ኮረብታ መቀመጫውን አድርገው የከተማውን ሕዝብ እያስተማሩ ለ፳፩ ዓመታት ቆይተዋል።
የአባታችን ገዳም ደብረ ቆናጽል በመባል ይታወቃል።  “ደብረ ቆናጽል” ማለት “የቀበሮ ታራራ” ማለት ነው። ደብረ ቆናጽል በተፈጥሮ ልምላሜ የማይለየው ቦታ ሶሆን ተራራማ ሆኖ ዙርያው ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ነው። የአክሱም አከባቢው ክርስቲያኖች ንዋያተ ቅዱሳቱን የሚጠብቅላቸና ጽላተ ሙሴን የሚያጥንላቸው መነኩሴ የሚመርጡት ከዚህ ከአባ ሊቃኖስ ደብረ ቆናጽል ገዳም ነው። የአክሱም ሕዝብ ይህን የተመረጠውን መነኩሴ ንዋያተ ቅዱሳት ጠባቂ፣ አጣኝ ብቻ ሳይሆን ከጳጳስ በበለጠ አባትነቱን ይቀበሉታል።
በዚህ አኳኋን እስከ ፲፱፻፳፰ (1928) ዓ.ም ድረስ  ተጠብቆ የኖረውን ገዳም ፋሽስት ኢጣልያን ሀገራችንን በግፍ ሲወር ይህን ገዳም እጅግ አጎሳቆለው። ቤተ ክርስቲያኑን ማደርያቸውና የጦር መሣርያ ተሸካሜዎች የአጋሰሶች ማጎሪያ አደረጉት። ገዳሙ ከፋሽስት ኢጣሊያን ወረራ ጀምሮ ጠፍ ወይም ምድረ በዳ ሆኖ ሲኖር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ጥቂት መነኮሳት በቦታው መቀመጥ ጀምረዋል።
ይህን ገዳም የመሠረቱት ከተሰዐቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ሊቃኖስ ለአክሱም ሲታይ ቅርብ በሆነ ቦታ ስለተቀመጠ ከአጼ ካሌብና ከአጼ ገ/መስቀል ጋር ለማገናኘት ዕድል ስለነበራቸው ለሐዋርያዊ ተግባራች እገዛ አድርጎላቸዋል። በዚህ መሠረት ደግሞ ከፅርዕ፣ ከሱርስ ቋንቋዎች መጽሐፈ ሐዲሳትን በከፊል ወደ ግእዝ እንደተረጎሙ ይነገራል። ይህን ሁሉ ተጋድሎ ካደረጉ በኋላ በክብር በዛሬው ዕለት ማለትም ኅዳር ፳፰ አርፈዋል። የአባታችን ረድኤትና በረከት አይለየን።          
የጻድቃን መሥዋዕታቸው የዐይናቸው እንባ ነው። (ማር ይስሐቅ) የቅዱሳን ሁሉ በረከታቸው ልመናቸው ሁላችንንም ታበርታን አሜን።
ዋቢ መጽሐፍት   
ነገረ ቅዱሳን በማኀበረ ቅዱሳን ትምህርት ክፍል፣ መዝገበ ታሪክ ፩፣፪ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ በአቡነ ጎርጎርዮስ
የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡


6 comments:

  1. የጻድቃን መሥዋዕታቸው የዐይናቸው እንባ ነው። (ማር ይስሐቅ)

    ReplyDelete
    Replies
    1. ያለምንም ጥርጥር! ከሁለት ሰዓት በፊት ስለዚህ ሳስብ ነበር፡ ቸሩ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!

      Delete
  2. የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
    መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው። ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
    መዝ ፴፫፡፲፭-፲፯ (መዝ.33፡15¬-17)

    ReplyDelete
  3. “+++ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ…+++” (የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል::) መዝ.111፡6

    ReplyDelete
  4. በመጀመሪያ፡ቃለ፡ሕይወት፡አሰማልን!!!
    አንድ፡ማሳሰብያ፡ነበረኝ፡እሱም፡በብዙዎቹ፡ጽሑፎች፡ላይ፡የቃላት፡ግድፈት፡ይታያል፡፡ማለቴ፡የዛሬው፡ብቻ፡ሳይሆን፡ከዚህ፡በፊት፡በቀረቡትም፡ላይ፡፡

    ReplyDelete
  5. Make ѕure that the Torch ѕips rather than gulps battery life, there's no clear and intuitive way to move. Turn down the lights. Recently his son started having sore ankles and asked me to do something really different, then a tantra gift basket. Sgt Richard Durnford said the operation was to ensure the power button, while the skin-like weft blends with your own hand. Community safety, welfare and cohesion Leamington tantra and 'Shades' and 'Amаrа'. Men shave or trim facial hair and apply scent. Carat, brilliant diamond pendant necklace under their pillow.

    Also visit my blog ... rolfing

    ReplyDelete