Tuesday, December 18, 2012

መንግሥት አቡነ ማቲያስ ዘኢየሩሳሌምን 6ኛው ፓትርያርክ ማድረግ እንደሚፈልግ ታወቀ


  • ምእመናን “ቅዱስ አባታችን” ብለው በሙሉ ልብና በፍቅር የሚታዘዙት አባት ይፈልጋሉ፤
  • ቤተ ክርስቲያን “እንቁላልና ቲማቲም የሚወረወርበት ሌላ ፓትርያርክ” አያስፈልጋትም፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 9/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 18/2012)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፕትርክና በ5ኛው ፓትርያርክ አረፍተ ሞት ባዶ ከሆነ ወዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያከራክር የነበረው ርዕሰ ጉዳይ እንደገና፣ እንደ አዲስ መወያያ መሆን ጀምሯል። በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃም፣ በግል ደረጃም የተለያዩ ሐሳቦችም በመንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ። በምእመኑ ደረጃ “ነገረ ፓትርያርክ”ን ከማንሣት በፊት ዕርቀ ሰላሙ መቅደም አለበት የሚለውን አበክሮ በማቅረብ ላይ ይገኛል። የተለያዩ ደብዳቤዎችንም ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አቅርበዋል። በሁሉም በኩል ሥጋት የሆነው ግን ክንደ-ፈርጣማው፣ እጀ ረዥሙ የኢሕአዴግ መንግሥት ለእምነቱ ተከታዮች ፍላጎት ሳይገዛ “የራሱን ፓትርያርክ” እንዳያስቀምጥ ነው።
በጥቅምት 6/2005 ዓ.ም ዘገባችን እንደገለጽነው በመንግሥት በኩል የመጀመሪያ የፓትርያርክ ምርጫው የምሥራቅ ሸዋ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ጎርጎርዮስ ሲሆኑ ይህ ካልሆነ በሁለተኛ ደረጃ የያዛቸው በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ የታመነ ነገር ሆኗል፡፡ የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአንዳንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንደ እንደራሴያቸውም እንደተተኪያቸውም አስተዋውቀዋቸው ነበር የተባሉት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ይኾኑ ዘንድ መንግሥት ወስኖ መግፋት ጀምሮ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ወደ ፕትርክናው መንበር መገፋታቸው÷ “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን አቋም እና አሠራር (እነርሱ ራእይ ይሉታል) ያስቀጥላሉ፤ ለመንግሥት ለመታዘዝና ፍላጎቱን ለማስፈጸም ይመቻሉ” በሚል ሐሳብ ነው ተብሏል፡፡


የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልተሳካ ሁለተኛ አማራጭ ኾነው የተዘጋጁት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ መሆናቸውን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡ ብፁዕነታቸው ለበርካታ ዓመታት በውጭ የነበራቸው ቆይታ፣ ከቤተ ክህነቱ ችግር ጋራ ብዙ ንክኪና ትውውቅ የሌላቸው መኾኑና ከመንግሥት ጋራ አብሮ በመሥራት ረገድ አላቸው የሚባለው አቋም በጉዳዩ እጃቸውን ባስገቡት የመንግሥት ሓላፊዎች እና እነርሱን እየተባበሯቸው በሚገኙት የቤተ ክህነቱ ሰዎች ዘንድ በዕጩነት እንዲያዙ እንዳደረጋቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአንድ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን የሚመራ ነው በተባለው በዚህ የ“ቀራቤ -መንግሥት” ፓትርያርክ ምርጫ ሂደት ድጋፍ እየሰጡ ናቸው የተባሉት የቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች’’ እንደሚገኙበት በጥቅምት 6/2005 ዓ.ም ዘገባችን ጠቅሰን ነበር፡፡

እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ በመንግሥት ዘንድ የመጀመሪያ ተመራጭ የነበሩት የምሥራቅ ሸዋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ለፕትርክናው ተጠይቀው ባለመቀበላቸው ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት ሹመቱ በኢየሩሳሌም  የኢትዮጵያ  ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሆኑት ወደ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ማጋደሉ እየተሰማ ነው። እንደ ታማኝ ምንጮቻችን መረጃ የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን በአካል ሄደው ጥያቄውን እንዳቀረቡላቸው፣ እርሳቸውም ሹመቱን ለመቀበል እንዳንገራገሩ ከውስጥ አዋቂዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ይሁን  እንጂ  የመንግሥት ባለስልጣኑ ካነጋገሯቸው በኋላ  ከቤተክህነት  ተወክሎ  ይሁን በራሱ ፈቃድ ባይታወቅም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑካንን የያዘ ቡድን ከብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር መነጋገሩ ታውቋል። ኢየሩሳሌም ድረስ በመሔድ ሊቀ ጳጳሱን ያነጋገሯቸው፦     
  1. ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
  2. አቶ ተስፋዬ ውብሸት  ምክትል ጸሐፊ፤
  3. አቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ ከሕዝብ ግንኙነት ክፍል እና
  4. መምህር ሰለሞን ቶልቻ፤
ሲሆኑ ወደ እሥራኤል በመሄድ ሹመቱን እንዲቀበሉ  የማግባባት ሥራ እንደሠሩና እየሠሩ እንደሆነ፣ ብፁዕነታቸውም ፕትርክናውን ለመቀበል ከመግደርደር አልፈው ወደመቀበሉ እንደደረሱ ከውስጥ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል፡፡ ልዑኩ ኢየሩሳሌም የሄደበትን ምክንያት ቅዱሳት መካናትን “ለመሳለም” በሚል እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል።

አሁን ጥያቄው “እንቁላልና ቲማቲም የሚወረወርበት፣ በምእመኑ ዘንድ ተቀባኢነት የሌለው፣ የመንግሥት ወኪል ተብሎ የሚፈረጅ አባት በዚህ ወቅት ያስፈልገናልን የሚል ነው። በርግጥም ጥያቄው ከብፁዕ አቡነ ማቲያስ ቀርቦላቸው ከሆነ በምን ልብ ሊቀበሉት ይችላሉ? የቀድሞው ፓትርያርክ በአሜሪካና በሌሎች አገሮች በሚያደርጓቸው ጉብኝቶች የገጠማቸውን ችግር፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን መከራ፣ እርሳቸው ራሳቸውም በቁርጥ ሲተቹባቸው የነበሩትን ጉዳዮች በተመለከተ መፍትሔ ሳይገኝ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነቷና ሰላሟ ሙሉ በሙሉ ሳይጠበቅ ወደ ሹመት መሔድ በርግጥ ማንን ይጠቅማል?

ዘመኑ ለብፁዓን አባቶቻችን እና ለመላው ምእመን ከባድ ጥያቄ አቅርቧል። ቤተ ክርስቲያኒቱ በሕጓና በሥርዓቷ እንድትመራ ማድረግ ወይም ፈቃደ-ንጉሥ ፈጻሚት (መለካዊት) ስትሆን በዝምታ መመልከት። በተለይም የፕትርክናውን ሥልጣን “በምርጫም ይሁን በስመ-ምርጫ ለሚቀበለው አባት እጽፍ ድርብ ዕዳ ይሆናል ብለን እናምናለን። ምርጫውም ይሁን ሲመቱ ለጊዜው ደስታ ካልሆነ በቀር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይረባታል ብለን አናምንም። የምእመኑ ድምጽ ከምንም ነገር በፊት “ዕርቀ ሰላሙ ይፈጸም፤ ቤተ ክርስቲአኒቱ አንድነቷ ይጠበቅ” የሚል መሆኑን በማያወላዳ መልኩ በመግለጽ ላይ ይገኛል። 
 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

የፓትርያርክ ተጠሪነቱና ጉዳይ ፈጻሚነቱ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለምድራዊ መንግስት ሆነ ማለት ነው? ርእሰ አበው የሚመረጠው በጸሎት በፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ : በፖለቲካ ፓርቲ ይሁንታ   ሆነ ማለት ነው?
1ኛ. መንግሥት ከቅድስት ቤተክርስቲያናቸን ላይ አጁን ያንሳ!!!
2ኛ. ቤተክርስቲያን በመንግሥት የሚወከል አባት አትፈልግም!!!
3ኛ. መንግሥት... "መንግሥት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም"  ሚለው ንግግሩን ተግባራዊ ያድርግ::

7 comments:

  1. I LOVE abune MATHIAS....... i will pray for him to be our pop for the holly church!

    ReplyDelete
  2. My brother suggested I might like this web site.
    He was totally right. This post truly made my day. You cann't imagine just how much time I had spent for this info! Thanks!
    My webpage - recent articles executive compensation

    ReplyDelete
  3. Іt's truly very difficult in this active life to listen news on Television, thus I just use web for that reason, and get the latest news.

    Here is my web page ... erotic massage
    Also visit my weblog ; erotic massage

    ReplyDelete
  4. midre koshasha yerasun blog kefto yerasun tikm bicha yantsebarkal. le ewnet kehone ke abune matias yemibelit be ahun papas yelem, bitwedum bititelum.

    ReplyDelete
  5. H.Grace Abune Matias is the right person for the position. I am happy with the nominatee father nominated by the holy synod. God Bless Ethiopia.

    ReplyDelete
  6. webwinkel beginnen libelle webwinkel beginnen goed idee

    Also visit my web-site telefoon Webwinkel beginnen

    ReplyDelete