Monday, December 10, 2012

ዕርቀ ሰላሙ በሚቀጥለው ጥር ወር በሎስ አንጀለስ በድጋሚ ይካሄዳል

 (ምንጭ:- ደጀ ሰላም )፦ ከኅዳር 26 እስከ 30 (ዲሴምበር 5-9/2012) በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት የተደረገው ሦስተኛ ዙር የዕርቅ ድርድር እሑድ ኅዳር 30,2005 ዓ.ም መግለጫ በማውጣት እና ለሌላ ጉባዔ ቀነ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቋል።
በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ባሉ አባቶች እና ምእመናን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የአራተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጉዳይ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት በዚህ ጉባዔ ከሁለቱም ወገን የተለያየ ሐሳብ ከመቅረቡ አንጻር ለጊዜው ከስምምነት ላይ የተደረሰበት አይመስልም።

ከአገር ቤት የመጣው ልዑክ “ቅዱስነታቸው በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ” ሲሉ በውጪ የሚገኙት አበው ደግሞ “ከነሙሉ ማዕረጋቸው ወደ መንበራቸው ይመለሱ” የሚለውን ሐሳብ አቅርበዋል። በሁለቱም በኩል ሐሳቡ ዕልባት ሳይሰጠው ቀርቷል።


በመግባባት፣ በመከባበር እና በመደማመጥ ተደርጓል በተባለው በዚህ በአባቶች ውይይት ከቀደሙት ሁለት ጉባዔያት በተሻለ “ተስፋ ሰጪ” የአንድነት ምልክቶች የታዩበት መሆኑን ብዙዎች እየመሰከሩ ነው። ሙሉ መግለጫው በዳላስ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በምዕመናን ፊት በተነበበበት ወቅት ከሁለቱ ወገን የመጡ ልዑካን ኮፒውን በእጃቸው ይዘው ታይቷል። በዕለቱ የተነበበው መግለጫ በዋነኝነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ሐሳብ ሰጥቶ ያለፈ ሲሆን እኛም እንደሚከተለው ጨምቀን አቅርበነዋል።

  1. መለያየቱ ሁሉንም ወገን በእጅጉ ያሳዘነ እንደመሆኑ ቀጣይ አራተኛ ጉባዔ እንዲካሄድ፣
  2. አራተኛው ፓትርያርክ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱበት ሁኔታ በሁለቱም ወገን የቀረቡት ሐሳቦች በሁለቱም በኩል ባሉ ምልዓተ ጉባዔዎች ታይተው ወደ ውሳኔ እንዲደረስ፣
  3. የቤተ ክርስቲያኑን ሰላምና አንድነት ለሚናፍቀውና ውጤቱንም በጉጉት ለሚጠባበቀው ሕዝባችን የሚፈለገውን ውጤት ማስገኘት እንዲቻል ሁሉም ወገን የበኩሉን በጎ ድርሻ እንዲጫወት አደራ፣
  4. የሰላሙ ጥረት ከፍጻሜ እስከሚደርስ ድረስ ሁለቱም ወገን ለሰላሙ ዕንቅፋት ሊሆን የሚችል ማንኛውንም ነገር ከመሥራት እንዲቆጠቡና ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቁ፣
  5. ይህንን ታላቅ የዕርቅ ሒደት ለማሳካት አላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘውና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን የሰላምና አንድነት ጉባዔ ማመስገን፣
  6. የሰላምና የአንድነት ጉባዔው ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ቀጣዩና አራተኛው ጉባዔ ከጥር 16-18/2005 ዓ.ም (ጃኑዋሪ 24-26/2012) በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ እንዲካሔድ፤ ከሰላም ጉባዔው ወደ ሁለቱም ተወያይ ወገኖች ምልዓተ ጉባዔዎች ልዑካን እንዲላኩና ስለተደረሰበት የውይይት ሁናቴ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተስማምተዋል።
  7. ይህ ጉባዔ ተጀምሮ እስኪፈጸም ድረስ በጸሎታቸው፣ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው የተባበሩትን የዳላስ ከተማና አካባቢውን ማኅበረ ካህናትንና ምእመናንን እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን አመስግነዋል።
  8. አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ስዚህ ተስፋ ሰጪ ውይይት በሚያቀርቡት አሉታዊ ዘገባ ምክንያት ምእመናን እንዳይረበሹ የሚሉት ይገኙባቸዋል።  

ስለ ዕርቅ ሰላሙ የተሰማጨውን ሐሳብ እንዲያሰሙ ዕድል የተሰጣቸው የሰላምና የአንድነቱ ጉባዔ አባላት በበኩላቸው
“የጥል ግርግዳው አልፈረሰም፣ ነገር ግን ተነቃንቋል”፤ እንዲሁም “የ20 ዓመት ችግር በአንድ ጊዜ ሊቀረፍ አይችልም ነገር ግን በትዕግስት ሁሉም ይፈታል”፤ “የሰይጣን ልቡ ተወግቷል ነገር ግን አልሞተም” የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።



“ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”። 

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

5 comments:

  1. የቅዱስ ጎርጎሪዎስ፣አትናቲዎስ፤ዲዎስቆሪዎስ…አምላክ ጉባኦውን ይምራ

    ReplyDelete
  2. “የጥል ግርግዳው አልፈረሰም፣ ነገር ግን ተነቃንቋል”፤ “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን - ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።

    ReplyDelete
  3. ayzon egziabehir kgena gar new selam yefeterale gubaai hawariyatene ybareke amelak yensunem ybark amin

    ReplyDelete
  4. Τantra саn be hаrmful to уouг health.
    Βest of all, a normal paгt of eveгydаy
    lіfe tοgether іnto immeԁiate рrеѕеnce and сοnnectiοn.
    Tantra Lingam Maѕsage iѕ a ԁeep gift fгom my staff.
    Gaгeth Emеry Hе has bееn stuԁying the
    saсred pгaсticе of yoga iѕ full оf pгotein which hеlp
    to glidе through the Engliѕh сountrуѕide.
    Ours had a small bаsket and fill it with sаlts ог whеn you aге relaxing.

    Ο fazeг marсa o dos movimеntos.
    Boastіng a seгvіces lіst of
    some of my clientѕ pгoven resultѕ available only οn my ωеbѕitе.


    Hегe iѕ my hοmepage;
    body treatments

    ReplyDelete