Thursday, December 20, 2012

ጥሪ - 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ጊዜውን ያልጠበቀ ሩጫ ለማትደግፉ በሙሉ

  • መፈክራችን - “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛልየሚል ነው።
 (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 .ም፤ ዲሴምበር 20/2012) በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ተጠናክሮ በመቀጠል አሁንአስመራጭ ኮሚቴበማቋቋም ትልቅ ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ መምረጡ እየተጓዘ ነው። 
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥም፣ ከአገር ውጪም፣ በመላው ዓለም ያለው ኦርቶዶክሳዊ ድምጹን ማሰማት እንደሚፈልግ ይታወቃል። የአቅሙን የመፍትሔው አካል መሆን ይፈልጋል። ታዲያ ምን ይሻላልከጥቃቅን የጽዋ ማኅበራት እስከ ግዙፎቹ፣ ከማኅበረ ካህናት እስከ ማኅበረ ምዕመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚገደን መናገር የሚገባን አሁን ነው። ስለዚህም ነው ይህንን የመወያያ ርዕስ የከፈትነው። መፍትሔ የምትሏቸውን ሐሳቦች በማቅረብ፣ በየአካባቢያችሁና በየአጥቢያችሁ በአካል በመሰባሰብና በመነጋገር ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁ አለኝታነት እንድታሳዩ ይጠበቃል። እምነት በሥራ እንጂ በምን ይገለጻል? ለመነሻ እንዲሆን ይህንን እንጠቁም። እናንተም አክሉበት።
  • መረጃውን ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን ማድረስ፣ (በስልክ የኤስ.ኤም.ኤስ መልእክቶች፣ በፌስቡክ፣ በትዊተር)
  • በየአጥቢያችን ድምጻችንን ልናሰማ የምንችልበት ስብስብ መፍጠር፣
  • ዜናውን ለመገናኛ ብዙኃን ማድረስ፣
  • ብፁዓን አባቶችን በስልክም በአካልም በመቅረብ ስለ ጉዳዩ ማነጋገር፣ በውሳኔው እንደማንስማማ ማሳወቅ፣ (አስፈላጊ ነው ብለን በምናምነው ጊዜ ስልኮቻቸውን በይፋ ለማቅረብ እንገደዳለን)
  • ጉዳያችን እና ዓላማችንድብቅ የፖለቲካ አጀንዳሳይሆን የቤተ ክርስቲያናችን አባት የመምረጥ ጉዳይ መሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት አለ ፍርሃትና ያለ ሥጋት መግለጽ፣
  • ከመንግሥት አካላት የተደበቀ የመሥራት ፍላጎት እንደሌለን ከወዲሁ በተደጋጋሚ መግለጽ፣
  • በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለጉዳዩ ሽፋን እንዲሰጡት ማበረታታት፣
  • የውጪ አገር ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎችም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ በሚል በዚሁ ሰበብ ኢሕአዴግን ለመተቸት ሳይሆን ጉዳዩን ለክርስቲያኑ ሕዝብ በማይጎረብት መልክ እንዲያቀርቡት ማገዝ፣
  • ኦርቶዶክሳውያን ጡመራ መድረኮችም ዜናዎችን በትብብርና በኅብረት ለምእመኑ ማድረስ፣
ጨምሩበት!!!!

3 comments:

  1. mechem abune mekarios yimtuna menbere patriarichnetun yiyazu atlum!? kehone ke 4 wer belay gize min yadergal? b/c he is engaged in politics.

    ReplyDelete
  2. bezih mnegd meketel kefelegu ejig asafari new.

    ReplyDelete
  3. Moѕt tantras offег masѕage, saunаs, аnd hydгothеrapies using water to heat oг сool the body tempeгature and
    will cause fluid loss and dehydration and can be
    oνeгwhelming anԁ can bгing even the most experiеnced masseuses.



    Also visit mу wеbpage kneading

    ReplyDelete