Wednesday, September 5, 2012

ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት በመዝረፍ ላይ

በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር 
 ፕሮቴስታንት እምነቱ ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም ይልቁንም በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን በትርጉም በትክክል  ለመግለጥ ሁልጊዜ አስቸጋሪ ሆኖ ይኖራል፡፡ በአብዛኛውም ግሎባላይዜሽን ባመጣው አዳዲስ ኩነቶች እራሳቸውን  በማመሳሰልና ጊዜውን በመምሰል የሚያክላቸው እስካሁን አልተገኘም፡፡
ይሁን እንጂ መቃወም ተቃውሞአዊ ጠባይ የሚያይልባቸው መሆኑን ከአንዳንድ መረጃዎች መረዳት ይቻላል በየጊዜውም የሚነሡት ሁሉ ከእነርሱ በፊት የነበረውን ትምህርት እየተቃወሙ በየጊዜው አዳዲስ ትምህርት እንዲያመጡና ክፍልፋያቸው (Denomination) እንዲበዛ አድርገዋል፡፡
 በዚህ ጊዜ ውስጥ መሠረታዊና እውነተኛ ትምህርተ ሀይማኖት እንዲኖራቸው ከምክንያቶቻችን ይልቅ በመገለጥ  ሃይማኖት አምነው ትምህረተ ሥላሴን እንዲቀበሉ ያደርጉ ሰዎችም እንደ ተነሱ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በዓለም ላይ ከደረሱትም ጉዳት አንዱ የሰውን  ምግባር (moral) መለወጥና እንስሳዊና ሰይጣናዊ ማድረግ ነው፡፡
 እስካሁንም በነበራቸው አካሄድ እግዚአብሔርን እናመሰግንበታለን የሚሉት መዝሙራቸው ዘመናዊ ዘፈን እንደሆነ የራሳቸው ሰው የተናገረውን እናነሳለን ለእኛ እንደ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የሚያስፈልገን ሽብሸባ  እንጂ ዳንስ ሊሆን አይገባም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዓለም ከታወቀችበት ትውፊቶች የራሷ የሆነ አገራዊ ዝማሬ ያላት መሆኑ ነው፡፡ ይህም ብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ነው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የሚሰጠው ምልክት ቀውስ ዳንስ ወይም ጭፈራ ሳይሆን አምልኮ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የበገናን ስንትርትር ዜማ ስንሰማ ልባችን ይቀልጣል እንግዲያው እግዚአብሔር በባህላችን ውስጥ ባስቀመጠው በዚህ መልካም ነገር ተጠቅመን ለማገልግልና ለማነጽ  ብንሞክር መልካም ይመስለኛል፡፡ ቀናነት ካለን!  በማለት ብሶቱን አሰምቷል ዳንሳቸው እያደረሰ ያለውን ጉዳት ቀውስ ብሎ በመጥራት ገልጦታል፡፡  ይህ ግርማዊ የተባለ ፀሐፊ የብልፅግና ወንጌል ብሎ በ1992 ባሳተመው መጸሐፍ ላይ የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ ደግሞ ሰሞኑን ባሳተሙት የመዝሙር ካሴቶች ቅዱስ ያሬድን ሊያስተዋውቁን እንዲህ ዳዳቸው፡፡     ለቀባሪው አረዱ እንዲሉ:: ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ


ቤተክርቲያናችን ለዘመናት የሃይማኖትና የሥርዓት ብቻ ሳይሆን ታሪክና ቅርስ ጠባቂ ሆና የቆየች ናት አብዛኞቹ ታሪኮቻችንም የተመዘገቡት በብራና መጽሀፍት ላይ ሲሆን በቃል የሚነገሩትም ብዙዎች ናቸው፡፡  እነዚህም ለፕሮቴስታንት ስብከት የማይመቹ በመሆናቸው በሚገባውም በማይገባውም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየጠቀሱ እንደ ፈለጉትም እያጣመሙ በመተርጎም በቤተክርሲቲያናችን ተጠብቀው ለሀገር የቆዩትን የቤተክርሲቲያን ሀብት የሀገር ቅርስ የሕዝቡንም ባሕል በእጅጉ ለማጥፋት ሲጥሩ እና ሲያጠፋ እንዳልነበር ዛሬ የእነሱም ሀብት እንደሆኑ ሊነግሩን ሊያስረዱን ደከሙ ዛሬ ስለ ቅዱስ ያሬድ የነገሩን ከየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አገኘነው ይሉ ይሆን? አዋልድ መጻኅፍትን አይቀበሉ እንደሆን!  ምንስ ምክነያት ያቀርቡ ይሆን? የሆነው ሆኖ  ስርዓቱን ሳያጓድሉ ቢይዙት መልካም በሆነ ነበር ከውስጣቸው ሲዋሀድ ወደ ማንነታቸው በተመለሱ ነበር ነገር ግን ያሬዳዊ ብለው ጀምረው ካልበረዙ ካልቀላቀሉ ዓላማቸው እውን ሰለማይሆን ትክክለኛ ስርዓቱን ለማስቀመጥ አዳጋች ይሆንባቸዋል ፡፡
ይህን የቤተክርስቲያን ስርዓት የመበረዝ ተግባር የውስጥ ጠላቶቻችን ተሐድሶዎችም እየተጠቀሙበት ኖረዋል፡፡  ዛሬ ጋብ ያሉ ሲመስሉ ደግሞ ዋናዎቹ ፕሮቴስታንት ምን እንስራ ብለው ብቅ ማለታቸው በጣሙን ያስገርማል፡፡
በቅርብ ጊዜም ከበሮውና ፅናፅል መቋሚያ በመያዝ እና አባ ናትናኤል ተብየው  ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት ስርዓታችንን ሲበረዝ አና ንዋያቶቻችን ሲያራክስ ተመለከትን ፡፡ ሰሞኑን በወጣ አንደ ካሴታችውም ላይ ደግሞ ከዚህ በባሰ መልኩ የቤተክርስቲያናችንን የመዝሙር ዜማዎች፣ መሳሪያዎች በገናን ጨምሮ ቅጥ ላጣ ሙዚቃቸው ሲገለገሉበት እንመለከታለን፡፡ 
 እስካሁንም በነበራቸው አካሄድ ከዚህም ይባስ ብሎ በያሬዳዊ ዜማችን ከቅዳሴያችን ላይ ካወጡት ሀረግ ለካሴታቸው ማሻሻጪያ በያሬዳዊ ዜማችን ላይ ሲዘባበቱ ይታያል፡፡ ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

ሌላው ይቅርና የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ዛሬ ላይ እነሱ እንደሆኑ ለመግለጽም ለኢትዮጵያ የፅድቅ ፀሐይ ወጣ እያሉ ገና ለገና ፕሮቴስታንታዊ መሪ ሀገሪቱ እንደሚቀጥል ባልታወቀበት በዚህ አጭር ጊዜ እሰይ እስይ ዘመን መጣ ለኢትዮጵያ ፀሐይ ወጣ ፡ እንባዋ ታበሰ፡ ኢትዮጵያ ትነሳለች እግዚአብሄርን ታመልካለች ፀኻይ አሁን እንደውጣላት በዚሁ ቪሲዲ ላይ የተካተተ ነው እኛ ባናቀርበውም ፡፡ እዚህ ጋር ባለፈው “ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደች” በሚል  ባስነበበናችሁ ርዕስ ላይ ከተሰጠን አንደ የፕሮቴስታንት የውስጥ መልእክት ውስጥ አንዱን ለማንሳት እንወዳለን  you are surprised because our current prime minster is protestant? Just wait and see we will capture all the land of Ethiopia...I'm sure God will like that ተመልከቱ ከአሁን በኋላ ጊዜው የእነሱ እንደሆነ እና ማንም ሊቀናቀናቸው እንደማይችል የኢትዮጵያ ምድርን እንቆጣጠራለን ሲሉ ፕሮፓጋንዳቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚያስችላቸው በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
እየሆነብን ያለው ቤተሰባዊ ማህበረሰባዊ ሀገራዊ የሆኑ እሴቶቻችንም ጥላሸት መቀባት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ስርዓቶችን ማጥፋት በዚህም አዲሱ ትውልድ  የነገው ዜጋ በማንነቱ እንዳይኮራ የራሴ በሚላቸው ንዋያተ ቅድሳት  እንዲያፍር የእኔ አይደለም እንዲል በአጠቃላይ ፀረ ዜግነት ጦርነት ተከፈቶበታል፡፡
ጎበዝ ምንድነው እየሆነ ያለው  ቤተክርስቲያንን አምላክ መቼም እንደማይተዋት ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ግልፅ ነው ግን  ቤተ ክርስቲያናችን በፕሮቴስታንት በግልጽ የቅርስና የንዋያተ ቅድሳት ዘርፍ እየተደረገባትም እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡  ፕሮቴስታንት በዚሁ አሁን ባወጡት ሲዲ ላይ ቁልጭ ብሎ እንመለከታለን ከበሮ ጸናጽል መቋሚያ በገና ጽንሐ መረዋ መለከት መስንቆ ዋሽንት ሁሉንም የመዝሙር ንዋያትን ያለምንም ከልካይ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው በንዋየተ ቅድሳታችን ላይ ሲዘባበቱ  ይታያል ድሮ የመስቀሉ ጠላቶች እንዳልነበሩ መስቀሉን ይዘው እነሱም መስቀልኛ ነጠላ አጣፍተው እውነተኞች ለመምሰል ሲሯሯጡ ይሰተዋላሉ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የእኛው በሆኑ መዝሙር የመዝሙር ስንኞችን በመውሰድ ለመዝሙራቸው ተጠቅመዉበታል ለሁሉም ቀጥሎ ያለውን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

 •  ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ስርአት መከበር እና ማስከበር ከላይ እታች የሚል ትውልድ የጠፋው ለምን ይሆን?
 •  በቅርሶቻችን በመዝሙር መሳሪያዎቻችን በራሷበሆኑ ንዋያተ ቅድሳት የባለቤትነት መብትስ የማታስከብርበት እስከመቼ ነው? መናፍቃኑ ቀድመው የእኛ ነው እስኪሉ ይሆን?
 • ተሐድሶው ተነስቶ የፈለገውን ሃሳብ ሲያንፀባርቅ ብሎም ፕሮቴስታንቶች ከላይ እንዳየነው ለኢትዮጵያ ፀሀይ ወጣላት ሲሉ በእኛው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ዘማሪ ተብዬ ደግሞ ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት ይላል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን በአንድም በሌላም መልኩ የማፍረስ እስትራቴጄ በውስጥም በውጪም እንቅልፍ አጥተው ሲሯሯጡ ይታያሉ፡፡ በተሐድሶዉም ይሁን በፕሮቴስታንቱ ስርአትን የመበረዝ እንቅስቃሴዎች ቤተ ክርስቲያን የማታወግዘው እስከ መች ነው?
 • ስርአት በተጣሰ ቁጥር ምእመናን እስከመቼ ዝም ብሎ ይመለከታል?
 • ዛሬም በያሬዳዊ ዜማችን ሲቀለድ እንደለመድንው አሁንም ይህን አይተን  ዝም ብለን እንመለከት ይሆን?
ሁሉም ጥያቄዎች የእያንዳንዳችን ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል በጣም እናምናለን፡፡ መፍትሄውም የእያንዳንዳችን መሆን እንዳለበት ከማንም የተደበቀ አይደለምም የተደበቀም ሊሆን አይችልምም፡፡ እስኪ ምዕመናን እናስተውል ኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያናችን አጋዥነት መቼም ለጠላት  ተንበርክካ አታውቅምመቼም ተሸንፈን አናውቅም ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣልና ታዲያ በነዚህ ሚሲዮናውያን እየደረሰብን ያለውን ታላቅ የማንነት ወረራ የማንዋጋው እስከመቼ ነው እስኪ መፍትሄ እንፈልግ እንወያይበት ፡፡
በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ማቴ.16:18
ይቆየን
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከላይ በትንሹ ያሳየናችሁን ቪሲዲ ለማየት ብላችሁ ለመግዛት እንዳትሞክሩ ምክነያቱም አላማው ገቢው የእኛኑ ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት የሚውል ነው ከፈለጋችሁ በኢሜላችሁ እየሰሩብንን ያለውን ሌላውን እናስተምርበታለን  ብላችሁ ለምትፋልጉት ብቻ ሌሎቹንም መዝሙራት እንልክላችኋለን በኢሜላችን ፃፉልን፡:

 በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤ 2ጴጥ.3:3


64 comments:

 1. bado nacwe selzeh badontacwen l mdefen yetkmubetale twahedo den mulu nate k maniem atfelgem ymigeremwe menien endate b men seate metkem endalbacwe aywekume
  ena genie enineqa enwek k nshu gare kalwe ena gare ylwe endmibelte eysayunie nwe

  ReplyDelete
 2. Ahun yihe Haymanot new weyis mindin new????????????ene ewnet sirat ena hig yelelew dirijit(mesriya bet) enquan alawkin....gin yenezih beza..........zimitachin eko esu fetari silehone new.............Any ways it was a good job dekike nabutewoch...Egziabher Yibarkachihu

  ReplyDelete
  Replies
  1. ene migermegn ye protestant eminet teketayochu tilant mesikel ayiyazim, kidus ayibalim, mariamin atitru, orthodox huala ker new...etc siluachew amen,,,,,,,,zare demo tekebelut sibalu tinish enkuan tiyake ayichiribachewim,,,,,,, ke MENFES KIDUS yehone hayimanot be 1 milas 2 ayanagirim

   Delete
 3. Bee Seme Ab, WeWeld, WeMenfes Kidus Ahadu Amelak. Amen. Enesu meen yargu gobez. Engha tegheteen beru tekefetelacheew, maneen yeferu(Egzehabhern Ayaweku) selezeh mezerefun teyayezewetal. Ere gobez mendeeneew yemenetebekeew? Yehe eko yemanenet(Yene) yehoneewen mezereef neew yeyazut. Ahuun eko eyetetekemu baleew ye betekereseteyan newaye kedesat meneneet(teregum) beteyeku enkuan ayawekutem. Yehe eko "Yeras yalhone geet ayasgeet" endemebaleew neew. Abatochacheenem yeheen yeyayu zeem kalu, yehen guday egha wetatoch sele erascheen guday lela maneenem metebek yelebeneem. Lemaneghaweem "neger bebeza baheya ...." selehone. Yeheen lebeneet zare nege saneel masekoom alebeen. Lezeheem Egzehabheher Yerdan !!!

  ReplyDelete
 4. Yebalbetnet mebtm Yelenm Ende Yigermal sint Gud new Yemnsemaw

  ReplyDelete
 5. በመሰቀል አያምኑም ነበር አሁን ግን መሰቀሉን እየያዙት ነው ስለዚ እያመኑበትም ነው ማለት ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አያምኑበትም ! ቀላቅሎ መኖር አይቻልም! በማስመሰል የዋሁን ምእመን ለመንጠቅ ነው፡፡ ይህ ለእነሱ ለጥፋታቸው ነው፡፡

   Delete
  2. Egziabher yimesgen, Musilimochem bitekemubet leKirstos khone- Yaredawi zemam sijemer, lesew aydelem legziabher new, des lelen yegbal enji, Kiber ahunem lezelalem lersu yihun- wanaw gen fiker new, Protestantochen enwadachewalen woi? Fiker kelele Geta Yelem- Ersu fiker newuna- protestant hulu korthodox yefelese new enji kferenje ager yemeta hizib aydelem, they are our brothers and sisters as well

   Delete
  3. yich madenageria wetmed mezergiyachewu nate wegen nika

   Delete
  4. Wegen Hoyi ahunim, mastewal yemigeban YEBEG LEMID mindin newu!!! Tewahido Hayimanotachin Yetemeseretechewu Bedingay newu!! Enezi sowoch Menafikanoch min eyaderegu newu bilen binimeremer Bewunet Betam Yemiyasazin newu!!! Ye Bahel Mewurer Yemibalewu Yih newu!! Ebakachihu Ansat, Ensum beyazut des lilen yigebal kalinima wanawu alama ersu newu, beyewahinet des silen kes bilewu bewustachin Yemeberez menfes silalachewu, Enetenekek! Endezih ayinetu Aganenent DEGMO YEMISHSHESHEWU YEMITEFAWU, BETSOM BETSELOT BESIGDET NEWU!!! YANE LEMEKUKUWAM YAKITEWAL!! BENESU ADERO LISERIK YEMETAWU AGANININT NEWU "HASAWI MESIH", ..... YEWAHINET KE"BILHAT GAR NEWUNA!! ENETENKEK!! YEKIDUSAN HULU TSELOT< YE"ENEATACHIN YE'EMEBIRHAN REDIET FIKRUWA BEREKETUWA KEHULACHIN TEWAHIDO LIJOCH GAR YIHUN!!! AMLAKE KIDUSAN HAILE AGANINITIN YARIKILEN! YITEBIKEN!!! ++++

   Delete
 6. Anjeten aneferut !!! Tebekelun endeza bikibirina besisit mayachew lemenkat enko mintenekekewun manim wurgat tera gatewoti sichefirbet mayet alihonelignm !! Bewunet ebekelachewalehu bezihs Egziabher minim milegn ayimesilegnim !!

  ReplyDelete
 7. አሁን ጮክ ብለን ጠንከር ብለንና እንድነት ሆነን መናፍቃንን በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል

  ReplyDelete
  Replies
  1. በትክክል ጮኅን በቃችሁ ልንላቸው ይገባል፡፡

   Delete
  2. betikikil bekachuh linilachew yegebal egna gin ahuim yetewahido lijochi mebertat new yalebin kahunu bekachu kalalnachew yeselelu ena yaltsenu egrochin yenetkalu netakiwochi nachew kedemom yerasachew neger yelachewim yegnan ye orthodox tewahido yehone neger mewsed bettam adegegnawechi nachew ena kehadewoch hulum yetefalu kalum endemilew kehidet titefalech emnetachin gin lezelalem tinoralech be kiristo mekeran linikebel meskelun yezen guozo jemirenal tehadisom hone menafikan betifatachew yetefalu egnam metenker alebin bettam egziabher orthodox tewahidon ahunim yetebkilin

   Delete
 8. ደቂቀ ናቡቴዎች ስለልፋታችሁ ቅዱሱ ጌታ ይባርካችሁ፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ የማልስማማበት የመምህራን አመለካከት አለኝ፡፡ ይህም ምንድን ነዉ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ብዙ ጊዜ ስለሌሎች እምነት ተከታዮች ደካማነትና ክሃዲነት በማዉራትና በመዘርዘር የማይረባ ስራ እንሰራለን፡፡እኔ እንደመሰለኝ ሌሎች የኛን ቤት መጥተዉ አያፍርሱት እንጂ የኛዉ እምነት ተከታዮች የተሻለና ጠንካራ መሆን ባለብን ላይ ሁልጊዜ ብንሰራ በጎቸን ጠብቁ ያለዉን ትፈጽማላችሁ እላለሁ፡፡ ሁኖም እንዲህ ያሉ መመሳሰሎችን ህዝበ ክርስቲያኑ እንዲያዉቅ ማድረግ ግን አስፈላጊ ነዉ፡፡ ለሁሉም የጌታ ፈቃድ ይሆናል፤ብዙዎቻችን ለጥፋት እንበረታለንና፡፡ ሰላም ሁኑ፡፡ ክብርና ምስጋና የዘላለም ሃይል ለአምላካችን ለወልድ ፤ላፈቀረን ለአብ እና አባቶቻችንን ላፅናና ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ማነህ....ጠረጠርኩህ ...እራስህን ፈትሽ...ደቂቀ ናቡቴወችስ ምንም እንከን አላደረጉን....ያዉም የቀበሮዉን ስልት አጋለጡት እንጅ

   Delete
  2. awe yastereteral egeziabhir yebekel degemo ayekerm gn egna kerasachn engemerena yehaymanotachn sereat endayefas seyetan endayasten mastewalum yesten

   Delete
 9. እንኳን የቤተ ክርስቲያን ትውፊት አይደለም የራስ የሆነ ፈጠራ ሲነካ ያንገበግባል የቤተክርስቲያንማ ይህ ነው አይባልም እባካችሁ የእያንዳንዳችን ድርሻ እንወጣ እኔ ስርአቷ ሲፋለስ ዝም ብዬ ላላይ እንዲሁም ቅዱሳን ንዋያት ሲረክሱ እንዲሁ ላላይ ወስኛለሁ አምላክ ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በከበሮ፤ በበገና፤ በክራር…..ወዘተ ለምን ትጠቀማላችሁ ማለት አንችልም፡፡ ፕሮቴስታንቶች እነዚህን ዕቃዎች አይስረቁ እንጂ አሰርተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

   Delete
  2. protesetant'och ayesereku Enj aseretew betekimu menem chger yelewem le wera yelewem fera tirigum kifelachenin enasetekakil bakachu amelak egezehabeher yiker yebelen

   Delete
 10. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
  ስንት ጉድ ይሰማል ባካችሁ? በእርግጥ ይህ ሊገርመን አይገባም ሰይጣን የብርሀን መልአክ እስኪመስል እራሱን ይለውጣልና፡፡ እኛ ግን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ አሁን ሲኖዶሱ ባስተላለፈው ውሳኔም ሁላችን በእምነት ሆነን ምህላውን ከካህናት አባቶች ጋር አብረን እናድርስ … አንዳንዶችም ይህ ስራቸው ወጥ ስላልሆነ አይተው ወጥና ትክክል ወደሆነች ቅድስት ሀይማኖት ይመለሱ ይሆናል፡፡ አንዴ በኑፋቄ ትምህርት ስለተበከሉ እውነትን ሲያውቁ ምን ያህል እንደሚቸገሩ እነርሱም ያውቁታል …


  እራሳቸውን የሐዋሪያት እምነት ተከታዮች (Only Jesus) ብለው ከሚጠሩ፣ ምስጢረ ሥላሴን ከማያምኑ፣ ብሎም በቅዱሳን ምልጃና ጸሎት ከማያምኑ ጌታ ስጋና ደምን ከእመቤታችን አልነሳም ብለው ከሚያምኑ፣ ጥያቄ እንጂ መልስ ከሌላቸው ሰዎች አመራር ይጠብቀን ፡፡
  የቅዱስ ያሬድን የመዝሙር ስልት ከመላዕክት መማሩን ያውቁት ይሆን፣ የእመቤታችንን ትንሳዔ ሳያምኑ በመስቀሉ ስር የሚያዘውን እመቤታችን በዕርገቷ ለቅዱስ ቶማስ የሰጠችውን ሰበን ተረድተውት ይሆን?


  አረ ለመሆኑ የሚጣፋው የመስቀሉ ቅርጽ፣ የካህናቱ ጥምጥም፣ የተክሌ ዝማሜ … አውቀውትስ ይሆን? የቅዳሴውን ዜማ፣ እጣኑን፣ ደወሉን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ ሌላውን ንዋያተ ቅዱሳት ሁላ ትርጉሙ ገብቷቸው ይሆን? ትላንት ሲያጣጥሉ የነበረውን ሁሉ ዛሬ ተቀበሉ ማለት ነው? እኔ እስከሚገባኝ ይሄ ሁሉ ያካሄድ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሌላ አላማቸው አንድና ያው ነው፡፡ ይህቺን ዘመን ተሻጋሪ፣ ክርስቶስን ወልድ ዋህድ ብላ በአስተምህሮዋ ጸንታ የኖረችውን በቅዱስ ጴጥሮስ አለትነት ላይ በክርስቶስ የተመሰረተችውን እምነት ለመበጥበጥ ነው፡፡ እኛስ በይሁዳ መልዕክት ቁጥር 3 ላይ አንዲት ጊዜ ለቅዳሳን ስለተሠጠች ኃይማኖት እንድትጋደሉ እጽፍላችኋለሁ እንዲል በሀይማኖታችን ጸንተን እንኑር፣ በእምነታችን ላይ እውቀትን እንጨምር፣ ያላወቅነውን ነገር ስንሰማ አንደናገጥ፣ በህይወታችን ሁሉ ያልተመለሰ የሚመስለን ጥያቄ እንኳ ቢኖር ቤተክርስቲያናችን ስንዱ እመቤት ናትና ለሁሉ ጥያቄ መልስ እንዳለ እንወቅ፡፡ ቢቻለንስ መጻህፍትን ሁሉ እንመርምር ለእኛም ለሚጠይቁንም መልስ እንዲኖረን፡፡
  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

  ReplyDelete
 11. ፕሮቴስታንቶች ሌላው ቀርቶ ቤተመንግስቱንም ወስደውታል፡፡ እናንተ ግን ለከበሮና ለክራር ታለቅሳላችሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ የፖለቲካ አመራር ብቃት እንጂ ሀይማኖት ያመጣው ጉዳይ አይደለም.

   Delete
 12. ቃለህወት ያሰማቹህ....የነዚህን ቀበሮወች ርካሽ ስራ አወጣቹሁት።

  ReplyDelete
 13. We have to struggle to claim our properties.

  ReplyDelete
 14. ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቼ እስኪ እንደ ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እንምንወዳት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና እንደተከበሩት ቅዱሳን ልባችሁን ሰፋ አድርጉት፡፡


  ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮቴስታንት ብቻ ሳይሆን ሌሎች እምነቶችም ለመስፋፋታቸው ወደድንም ጠላንም በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች የቀደሙት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡
  ይኽን የምልበት ምክንያት ወንጌል ለሁሉም ብሔርብሔረሰቦች በሚገባቸው ቋንቋ በየቦታው ተዘዋውሮ ከምንም ነገር ጋር ሳይያያዝ ቢሰበክላቸው ኖሮ ሌሎች በሁዋላ የመጡ ሀይማኖቶችን የተቀበሉ ጽድቅን የሚፈልጉ የዋሀን በተቀበሉት ነበር ብየ ስለማስብ ነው፡፡


  ነገር ግን እኔ ነፍስ እንኳን ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን መሄድ አስቀድሶ ተዐምር ሰምቶ መመለስ፣ አጽዋማትን መፆም፣ ንግስ ማንገስ፣ . . . የመሳሰሉት ሀይማኖታዊ ተግባራትን ከመፈጸም ባለፈ አሁን እንደሚደረገው ቤተክርስቲያናችንንና የድህነትና ሌሎች አስተምሮቶችዋን እንድናውቅ የተደረገበት መንገድ አልነበረም፡፡ ዛሬም እንኳን በእውቀትና በመረዳት ቤተክርስቲያኑን የሚወደውንና በስሜት የሚነዳውን ቤት ይቁጠረው፡፡


  ታዲያ በዚህ ሁኔታ ወደ ፕሮቴስታንትም ሆነ ወደሌላ እምነቶች የሄዱ ወንድም እህቶቻችንን ለኑፋቄ የተፈጠሩ አድርጎ መመልከትና ቀስ በቀስ ወደቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ሲመጡ ቅርስ እየዘረፉ አድርጎ ማሰብ ተገቢ አይመስለኝም፡፡


  ፕሮቴስታንቶችን ቀረብ ብንላቸው ከጥቂት ስሜታውያን በስተቀር ጽድቅን የሚራብ መንፈሳዊ ልቦና ያላቸው ሁሉ አሁን አሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አስተምህሮዎችን በተለያየ መንገድ ሲሰሙ ልባቸው የማይነካና ለእናት ቤተክርስቲያናቸው ክብር የሌላቸው በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ በሰል ያሉትን ቀርባችሁ ብታናግሯቸው በየቀኑ እንደ አሜባ የሚቆራረጠው የእንትና ቤተክርስቲያን፣ የእንትና እየተባለ የዕለት እንጀራ ማብሰያ የሆነው ብዜት ናላቸውን አዙሯቸዋል፡፡

  ኦርቶዶክሳዊ የነበሩትም የእናንተ ወንድሞቻቸው የልብ ስፋትና የእናት ቤተክርስቲያናቸው የጥሪ ደወል ናፍቋቸዋል፡፡በቅርብ የማውቃቸው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን አጽዋማት ሳይቀር መጾም የጀመሩ አሉ፡፡ ግን በፕሮቴስታንትነታቸው ይታወቁ ስለነበር ብዙዎቹ ከቅርብ ጓደኞቻቸው በስተቀር ቢያንስ በአመለካከታቸው እንደተመለሱ የሚያውቅ የለም፡፡


  ስለዚህ ልባችንን ሰፋ ብናደርግና ሙሽራ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብናሳምራት፣ መንፈሳዊ ህይወታችን ቢያምር እነዚህን ወንድሞቻችን ወደዚች ባለግርማ ሞገስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መፍለሳቸው አይቀሬ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ ላሉ ሁሉ የወንጌል አደራ ያለባት ናትና ጉልበታችንን በከንቱ ነገር ባንጨርስ፡፡ ይልቁንም ሰሞኑን የተጀመረውን የአባቶቻችንን ሱባኤ እግዚአብሔር አምላክ ተቀብሎልን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የትውልድ ሁሉ መጠጊያ ያድርግልን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በእውነት በጣም ጥሩ አስተያየት ነው የሰጡት፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የምስራቅ አፍሪካ ሀይማኖት፤ የአማርኛ ቋንቋ የምስራቅ አፍሪካ ቋንቋ መሆን ይገባው ነበር፤ ነገር ግን በአስተሳሰባችን በጣም ጠባቦች ስለሆንን ዛሬ እንኳን ሌላውን ለመሳብ ይቅርና የተዋህዶ ሀይማኖታችን ህልውናም አጠራጣሪ እየሆነ መጥቷል፡፡
   ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አሉ፤ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተለይተው እንደሄዱ ይታወቃል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ እነርሱ ከእኛ ተለይተው በመሄዳቸው ሊቆጨንና ሊያንገበግበን ይገባ ነበር፤ ከተቻለም አስተምረን ልንመልሳቸው ይገባ ነበር፤ እኛ ግን ተለይተውን ስለሄዱ ጀርባቸው ላይ መናፍቅ የሚል ታፔላ መለጠፋችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ከበሮ ሰረቁን፤ በገና ጠፋብን እያልን እንጮሀለን፤የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ሃብት የሰው ልጅ እንጂ ከበሮ አይደለም፡፡ ወንድሞቼ እኛ እነርሱን ብንሰድባቸው የበለጠ ይርቁናል ይሸሹናል ብናስተምራቸው ግን ቢያንስ ጥቂቶቹን ማዳን እንችል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ስድቡን አቁመን እናስተምራቸው ስለእነርሱም ዘውትር እንጸልይ ክርስቲያናዊ የሆነ ስነ ምግባር ይኑረን እላለሁ፡፡
   አመሰግናለሁ

   Delete
  2. wow betam tiru tekame message(comment)new ewent new lebona yeseten yiker yibelen Abet Egezehabeher gen men yahil yazeneben yihon wondemochachenin eyesedeben eyanikwasheshn eyegefan fiker eyekeilkelin men yilen yihon abetu amelake hoy yiker belen ant tareken !!!

   Delete
 15. balebet yelelat betekiristian. yasazinal

  ReplyDelete
 16. amilak yemibejenin endiadereg entheliy

  ReplyDelete
 17. በጣም ይገርማል በአምነታቸው አቀም የላቸው በየቀኑ edit ነው የሚያደርጉት
  ይህ ለ ፕሮቴስታንት ተከታዮችም ታልቅ ሽንፈት ነው
  ዛሬ የባለቤት ንበረት በተርጋገጥበት ዘመን የሰውን ንብርት አንስቶ መፈንጨት ምን ይባላል? የምነቱ ተከታዮችስ ከዚህ ምንድነው የሚሩት ስርቆት ወይስ .... ?

  ReplyDelete
 18. በጣም ይገርማል በአምነታቸው አቀም የላቸው በየቀኑ edit ነው የሚያደርጉት
  ይህ ለ ፕሮቴስታንት ተከታዮችም ታልቅ ሽንፈት ነው
  ዛሬ የባለቤት ንበረት በተርጋገጥበት ዘመን የሰውን ንብርት አንስቶ መፈንጨት ምን ይባላል? የምነቱ ተከታዮችስ ከዚህ ምንድነው የሚሩት ስርቆት ወይስ ወይስ ..... ?

  ReplyDelete
 19. wud dekike nabute woch,eske balefew amet yimeslegnal yihin lemaskeber bizim gilits yehone hig alneberem,ahun gin higun mengist yawota mehonun andadrgen or deje selam lay auttewut neber, silezih yan hig bemtekem yalatin habit balebetinet behig emitaskebirbet hunetan hulum gifit ena yakimun yakil endinesa silehigu blogachu lay bitawtu

  ReplyDelete
 20. awo ahunes betam new yebezaw enzeh sewoch kaltewen ega tensten zem endelu yegebale haymanote kelele hager yelem .

  ReplyDelete
 21. እነደሚመስለኝ ከሆነ ፕሮተስታንቶች ቀስ በቀስ ከ መስቀል እስከ እመቤታችን አምነው ከዛም ወደ ሀይማኖታችን እንደሚመለሱ ነው እግዚአቢሀር ቀስ በቀስ ይመልሳቸው አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኣፙን ያሳየናል ገና በራሳቸው መቆም እንዳቃታቸው ነው ይሀ የሚያሳየው::

   Delete
 22. yih tarikin leras lemadired memoker,teyaki kelelachew yegna new bilew eskemeteyek.... silezih belegaw behig betekiristian habtochiwan yebalebetnet mebituan maregaget...

  ReplyDelete
 23. እኔ ግን ጥለውት የሔዱትን ታላቅ ሐይማኖት መርሳት ስላልቻሉ ይመስለኛል ግራ ሲገባቸው ውጥንቅጡን እያጠፉ የሚጨፍሩበት። ደግሞስ መጠየቅ ሲገባቸው ማን ይጠይቃቸው? እንኳን የቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን የአንድን ግለሰብ የስራ ውጤት ማንም እንዲህ ሊጫወትበት ቀርቶ ሊነካው አይገባም። ግን ማን የባለቤትነት ስሜት ይሰማው። ተራ የንግድ ስያሜ እንኳን ከተመሳሰለ እኮ ፍቃድ አይሰጠውም።

  ReplyDelete
 24. Zeme kalene gena bezu yeseral,yesemal,yetayal,yedersebenal

  ReplyDelete
 25. In my opinion they were doing nothing wrong. They are just praising the Lord the best they know how in their cultural/traditional way. Even if Saint Yared was alive today i don't think he will be crossed with them. And besides this is part of their Ethiopian heritage too...praise the Lord for the people who orcastrated the worship songs.

  ReplyDelete
 26. ere endet Yigermal EGEZIABHIR hoy Yemiyaderguten Ayawekumena Yiker Bellachew Eninm Barahen Yiker Belegn Abat hoy Asteway Libonnan Adelen Amen

  ReplyDelete
 27. But, isn't there any law realted to this?? malete zemachinen endefelegu metekem yechilalu ende?? specially parts of "KIDASE"?? bezhi aynet eko neg KIDASE megemerachew aykerem....errrrrrrrrr and libalu yegebal

  ReplyDelete
 28. ልዑል እግዚአብሔር ከሰምጡት ባህር ያውጣቸው
  (ከኣጋንንት ባርነት)ያላቃቸው

  ReplyDelete
 29. ተዋቸው ጅብ ሚጮኸው እኪነጋ ነው.and ken negito siyayu yafralu degimom le aemirobeshitegna bemin yishalalu

  ReplyDelete
 30. minm slelelachew min yadrgu bilachihu new?menfeskidus slelelebet bado new

  ReplyDelete
 31. << . . .እርግጥ ነው የኔ የሚለው የሌለው የጎረቤቱን ጓዳ ይመለከታል ፡፡ እነሱም እያደረኩ ያሉት ያንን ነው፡፡ በሁሉ የተሟላችውን ተዋህዶን ባይመለከቱ ነበር የሚገርመው፡፡ አንዳንዴ ሙስሊሞች በዚህ ሳያሻሉ አይቀሩም፡፡ የበዛ የማንነት ቀውስ የለባቸውም ፡፡የተሳሳተ ቢሆንም የራሳችን የሚሉትና የሚራመዱበት መንገድ አላቸው፡፡ እነዚህ ግን አሁን አሁን ዘመናዊነትን ከኢትዮጵያነት ጋር ለማያያዝ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እየተሳሳቱት ያለው ግን ምንም ለውጥ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ በተለይ በዚህ ሠዓት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ. ስርዓትና አስተሳሰብ ውጪ አይሆኑም፡፡. . .>> Read all Article on http://bisrat-views.blogspot.com/2012/01/blog-post_22.html?utm_source=BP_recent

  ReplyDelete
 32. yegeremal tenat tert naw dersat naw filesefina naw endalalu zira basu megelegal gameru men yetawekal nag damo yekerta tyekaw and yamenehonebat geza yematal meknyatum EGZYABEHER talk AMELK nawena....!!..

  ReplyDelete
 33. አያያዙን አይቶ ጭብጦውን ቀማው፤
  ከሞኝ ደጃፍ………….
  ባለቤቱን ካልናቁ…………
  እንግዲህ በሕንድ ቤ/ክን እነደሆነው ነገ ፍርድ ቤት ሲዳኘን እኛም ዘምረንበታል ለማለት ይመስላል፤
  የናቁትን ከበሮ፤መቋሚያ፤ፀናፅል ባህላዊ ልብስ ሳይቀር አንድም ሊፈረድላቸው/ሊፈረድባቸው
  የተዋህዶ ቤ/ን የሕግ ክፍሏ እንቅልፋም ቢሆንም ልጇቿ አፍንጫቸውን ጠምዝዘን መቀበል አለብን፡፡

  ReplyDelete
 34. beab beweld bemenfes qdus sem and amelak amie
  yehn vidio yeserut yetewahdo kahn yeneberut Aba Natnael ena yeortodoks diyaqonat yeneberu nachew::
  zarie bederesnbet yemastewalna yemebsel dereja protiestantoch kewechew bahl telaqo hagerawi bahln bemaberetatat lay lay yegegnalu
  aortodoksenem Enat angafa bietekerestiyan mehonuwan teqeblew akeberotachewn begehad bemegletse lay nachew
  Amneten kehagerna kebahl leytew bemayetachew ahun keferenjoch bahl lemelaqeq bemetagel lay nachew::
  neger yetebelashew yezarie 50 amet Penticostal yehonutn maserna bedebdeb bejemernebet giezie new::
  Aehunm and bemiyadergen beab beweld bemenfes qdus bemnamn sewoch mekakel feqeren mastemarna enji keberona kerar liyatalan ayegebam:: yalefew yebeqal

  ReplyDelete
 35. ለመመሳሰል በሚያደርጉት ቅሰጣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ያቆየችውን ትውፊት፣ ቅርስና ሀብት እንዲሁም ግእዝ ቋንቋና ያሬዳዊ ዜማን ማንም እንደፈለገ አስመስሎ ባልተገባ መንገድ የመቀራመቱ ድፍረት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ታየዋለች? ያውም ቤተ ክርስቲያን የማትፈቅደው የመናፍቅ ድርጅት በሀብቷ ላይ ሲፈነጭ፣ ይህስ ጉዳይ ከህግ አንጻር እንዴት ይታያል? አንድ ተቋም ያላትን ሀብት ያለፈቃዷ ማንም መጠቀም ይችላልን? ምእመናን በሙሉ በተለይ የሕግ ባለሙያ ልጆቿ እንዲነጋገሩበት የሚስፈልግ ጉዳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 36. ይምጡ ከ99 በጎች 1 ሲገኝ ደስ ይለናል ግን ሲምጡ የአምላክ እናትን መውደድ ያስፈልጋል::

  ReplyDelete
 37. Ahunis beza abezut .....berasazhew haimanot eminetina fikir silelachew new .....ye egnan lemeintek yemimokirut Amlak hoy betekirstianachin kenezih tekulahoch tebikat hulachin lintsely yigebal....

  ReplyDelete
 38. Er Wegen Mindaw NEGER er Gud Er Egzho Egezho Egzho Eskmca New Gin Endzi Zim Yeminalw Belycin Lay Betkirstancein Eskytfut Yun Er Ezeb Christand Er Egzho Enewt Mindaw Negeru...Alk eko ezbacen YESTEN Menfes Ezeban Asenfaw Er Mindaw yemiketalws ?? mINDAW NEGERU Becah yemiyadergun Aywkum Ena Yeker Yeblcaw Er Wegen....Albzem Telalcaw Minaws Mefthaw Er zim Anbel?????????Er Er ER

  ReplyDelete
 39. eny bemejemery ymelew ykedus Gberayl amlak ygesetachew enga ortodoxayan benberetache ena batekalay bedereseben neger hulu ahununu metagel mechal aleben zme malet ylebenem it yhe betam yasaferale i am really sad.......dengel hoy erjen

  ReplyDelete
 40. eni yemigerimegn leminidinew yebetekiristianin siriat yemiabelashut hig yelem ende yemenigist yaleh enizihin sewich mela belulin esike mech dires enitages

  ReplyDelete
 41. የሐሰት አባት የሆነው ዲያብሎስ የብርሃን መልአክ መስሎ የመምጣቱን ነገር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ስላስተማረን ብዙም አይገርምም- ነገር ግን ቤተክርስቲያናችን የማንነቷ መገለጫ የሆኑ ሀብቶቿን የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ ስላለብን መብታችንን ለማስከበር ልንንቀሳቀስ ይገባል

  ReplyDelete
 42. ማንነታቸው የጠፋባቸው ምስኪኖች,,,, ይልቁን ማስመሰል ሳይሆን መሆንን ተማሩ,,,, ዘላለማችሁን ለምድ ለብሳችሁ አትጓዙ ንስሃ ግቡና ወደ እውነተኛውንና የቀደመውን ጎዳና ያዙ!!!

  ReplyDelete
 43. ማንነታቸው የጠፋባቸው ምስኪኖች,,,, ይልቁን ማስመሰል ሳይሆን መሆንን ተማሩ,,,,, ዘላለማችሁን ለምድ ለብሳችሁ አትጓዙ ንስሃ ግቡና ወደ እውነተኛውና የቀደመውን ጎዳና ያዙ!!!

  ReplyDelete
 44. አሁን ጮክ ብለን ጠንከር ብለንና እንድነት ሆነን መናፍቃንን በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል

  ReplyDelete
 45. ገና ወላዲት አምላክ ታማልደናለች ይላሉ የናቁሽ ሁሉ ከእግርሽ ስር ይወድቃሉ የተባለላቸው እኮ ናቸው ይህቺ ብቻ መሰላችሁ እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳል ተብሏልና ገና ብዙ እናያለን

  ReplyDelete
 46. betselot,
  lenewagachew yegebal

  ReplyDelete