Friday, September 28, 2012

ብዙኃን ማርያም



መስከረም ፳፩
ብዙኃን ማርያም  
መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው። አንዱ ጉባኤ ኒቂያን ይመለከታል።
፩ የመጀመሪያው ከተፍጻሜተ ሰማዕት አንዱ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተማሪዎች አንዱ አርዮስ “ትቤ ጥበበ ፈጠረኒ አብ ከመ እኩን መቅድመ ኩሉ ተግባሩ” ያለውን ንባብ ይዞ “ወልድ ፍጡር ነው” ብሎ ተነስቶ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ እለእስክንድሮስ አውግዞት በዚህ ምክንያት በጉባኤ እንዲነጋገሩ የሮም ንጉስ ደጉ ቆስጠንጢኖስ በኒቂያ ጉባኤ ይሁን ብሎ አዋጅ አስነግሮ የመስከረም 21 ዕለት በ2340 (43) ሊቃውንት በኒቂያ ተሰብስበዋል።
፪. “መስቀልን ይመለከታል።”
“በምድር ላይ ኃጢአትን አሰረ፤ በሲዖል ሞትን አሸነፈ፣ በመስቀል ሳለ መርገምን ሻረ፣ በመቃብር ውስጥ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አስቀረ። (ቅዱስ አትናቴዎስ)
የጌታ ግማደ መስቀል በብዙ እንግልትና መከራ በግብጻውያን ከተወሰደብን በኋላ የግብጻውያንንም ኑሮ በግዮን ውሃ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ይግዮንን ውሃ በመገደብ በኋላ ላይ ግብጻውያን አማላጅ ልከው መስቀሉን እንመልስላችኋለን ውሃውን ልቀቁልን በማለት በብዙ መከራ እንደመጣ የቤተ ክርስቱያናችን ታሪክ ይገልጻል።   በወቅቱም በሀገሪቱ ሰማይ ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከልክሎ ምድርም የዘሩባትን ከማብቀል የተከሉባትን ከማጽደቅ ተከልክላ ረሃብ ሆኗልና፤ ምናልባት ጌታ ቢታረቀን ከመስቀሉ አንዱን ወገን ላኩልን ብለው ጽፈው እጅ መንሻ ጨምረው ላኩ። ይገባዋል ብለው መክረው ዘክረው የቀኝ ክንዱ ያረፈበትን፣ ስዕለ ተኮርዖውንና ቅዱስ ሉቃስ የሳላትን ስዕለ ማርያም ላኩላቸው።
 ደግማዊ ዳዊትም ሊቀበሉ ስናር ድረስ ወርደው በእልልታ በሆታ ተቀብለው ሲመለሱ እሳቸው ባዝራ ጥላቸው ከመንገድ ዐርፈዋል።
ከእርሳቸው በኋላ ንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ ወዴት ባኖረው ይሻላል? እያሉ ይህን ሲያወጡ ሲያወርዱ ጌታ በታላቅ ድምጽ “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል” ብሏቸው አርአያ መስቀል ናትና አዋጅ ነግረስ በዓል አድርገው መስከረም 21 ዕለት ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አኑረውታል።   ብዙኃን ማርያም  መባሉ ቅሉ እንዲህ ብዙኃን የተገኙበት ስለሆነ ነው።
ስለዚህ መስቀል ለምዕመናን የነፃነትታቸው፣ የዕርቃቸውና የሰላማቸው ምልክት በመሆኑ ለመስቀል ልዩ ክብር ይሰጣሉ፤ ይሰግዱለታልም። ማንኛውም ተግባር፤ ጸሎትን፣ ምግብን፣ ጉዞን፣ከመጀመራችን በፊትና ከጨረሱም በኋላ በትእምርተ መስቀል ያማትባሉ፤ በፈተና፣ በሐዘን፣ ክፉ ሐሳብ በሕሊናቸው በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ያማትባሉ። በከበረ ደሙ መስቀልን የቀደሰ ጌታቸው በኃይለ መስቀሉ ሁሉን ሊያደርግላቸው እንደሚችል በመታመን ይህን ያደርጋሉ፡፡ “እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ በሚበልጥ ዓለምን ሁሉ ያዳነበት ከጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ ጥበብ ይህ ቅዱስ መስቀል ነውና!”  ለዚህ ነው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር” (መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው)” ያሉት። ይህ የመስቀሉ ነገር አምላክን ሰው የመሆንና እስከ መሪር ሞት ያደረሰውን ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ከማንከር በስተቀር ሊመረመርና ድርሰ-ነገሩ ሊስተዋል የማይቻል ረቂቅ ነው። በመሆኑም ነገረ መስቀሉ ለአንዳንዶች ፈተና ለሌሎችም ስንፍን ሆኖባቸዋል። ለሚያምኑ ምዕመናን ግን ከተና እንደወርቅ ነጥረው የሚወጡበት ነው።
በእውነት ጠላቶች እውነትን ለማጥፋተ ቢዘጋጁም በእርሱ ለዓለም እውነት ተሰብኳል። አይሁድ ሰዎችንና ክርስቶስን ለማራራቅ በመስቀል ቢሰቅሉትም በመስቀል ያፈሰሰው ክቡር የሚሆን ደሙ  ዓለሙን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቧል። የመስቀሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደር አሜን።
የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ መዋ.ን ከ1427-1440 ዓ.ም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡


2 comments:

  1. I know this website gives quality depending posts and other material,
    is there any other web site which presents these information
    in quality?
    Also visit my weblog :: manchester united transfer rumours today

    ReplyDelete
  2. webwinkel online webwinkel beginnen kosten

    Here is my page www.nuwebwinkelbeginnen.nl

    ReplyDelete