(ምንጭ፡- ቤተ ደጀኔ)በጸሎተ ኪዳን ዘሠርክ ላይ እንደተነገረው፥
ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ለምትሆን፥ ጸጋን ኃይልን ለምታድል፥ አምነው ለሚቀርቡት ምስጋና አንድም በሃይማኖት ለሚገኝ ክብር ማረፊያ
ማሳረፊያ ላደረጋት ለቤተክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። የተገረፈላት፥ሥጋውን የቆረሰላት፥ ደሙን ያፈሰሰላት፦ ነፍሱንም
አሣልፎ የሰጠላት እርሱ ነውና። የሐዋ ፳፥፳፰።
ጥንት ሙሴን እና አሮንን ልጆቹንም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የመረጠ
እግዚአብሔር ነው። ዘጸ ፫፥፩-፳፪፣ ፳፰፥፩-፲፬ ። ይህንን ምርጫ ለመቃወም ወይም በምርጫው ጣልቃ ለመግባት የሞከሩ ዳታን፥ ቆሬንና
አቤሮን ፍጻሜያቸው አላማረም። “እናንተ የሌዊ ልጆች ስሙኝ፤ የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን የእግዚአብሔርን
ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ እንድታገለግሏቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱ ታላችሁን?” ብሎ
የመከራቸውን ሙሴን አልሰሙትምና ዘኁ ፲፮፥፩-፶። ከቤተ መንግስቱም ሰዎች እነ ዖዝያን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ገፍተው ቤተ መቅደሱን
ደፍረው ነበር። “ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፥ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ
ወደ መቅደስ ገባ ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። ንጉሡንም ዖዝያንን
እየተቃወሙ፥ ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተቀደሱት ለአሮን ልጆች ለካህናቱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ አይገባህም፥ ከእግዚአብሔር
ርቀሃልና ከመቅደሱ ውጣ፥ ይህ በአም ላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ክብር አይሆንህም፥አሉት፤” ይላል። የንጉሡም መጨረሻ አላማረም።
፪ኛ ዜና ፳፮፥፲፮-፳፫
እግዚአብሔር እርሱ ራሱ የመረጣችውንም ቢሆን የሚቀጣበት ጊዜ አለ።
“የቅርብ ጠበል ልጥ ያርሱበታል፤ ዝቋላ የቅርቡ ያርሰዋል፥ የሩቁ ይሳለመዋል።’’ እንዲል፥ ቤተ እግዚአብሔርን
ደፍሮ ማስደፈር በቀረቡት የሚብስበት ጊዜ አለና ነው። የሊቀ ካህናቱ የአሮን
ልጆች ናዳብና አብድዩ እግዚአብሔር ባላዘዛቸው እሳት፥ የእምነቱ ሥርዓት በማይፈቅደው መን ገድ የዕጣን መሥዋዕት
በማቅረባቸው በሞት
ተቀጥተዋል። ‘’እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ በላቸው፤ (አቃጠላቸው)፤ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ” ይላል። ዘሌ
፲፥፩-፪ ።
ሙሴና አሮንም በሕዝቡ ገልበጥባጣነት እጅግ የተቆጡበት ጊዜ ስለነ በረ፥ “ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ
በእኔ አላመናችሁምና፥ስለዚህ
ወደሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛች ሁ አትገቡም።” ተብለዋል። የእግዚአብሔር ቃል ነውና ከነዓን አልገቡም። ዘሌ
፲፥፩-፲፫
የሊቀ ካህናቱ የዔሊ ልጆችም በቅድ ስናው ሥፍራ ርኵሰትን ይፈጽሙ ነበር። አባታቸው ‘’ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ
እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፥ ሰው እግዚአ ብሔርን
ቢበድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸልዩለታል?’’ ቢላቸውም አልሰሙትም። ‘’እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው
ወድዶአልና የአባታቸውን
ቃል አልሰሙም። ‘’ ይላል። እግዚአብሔርም፥ ‘’ያከበሩኝን አከብራለሁ፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።
እነሆ፥ ዘርህንም
የአባትንም ቤት ዘር የማጠፋበት ዘመን ይመጣል፤ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። በዓይኖቹ የሚፈጽም በነፍሱም
የሚተጋ ሰውን
ከመሠዊያዬ አላጠፋም። ከቤትህ የሚቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጎልማሶች ሰይፍ ይሞታሉ።‘’ ብሎ ተናገረ። ፩ኛ ሳሙኤል
፪፥፳፪-፴፮ የተናገረውም
ጊዜውን ጠብቆ በልጆቹ ላይ ተፈጸመ። ዔሊም “በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለምን በክፉ ዓይን ተመለከትህ?
የእስራኤል ልጆች በፊቴ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳማያቱ ስለ አከበርኩህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን
ለምን መረጥህ?” ተብሎ ነበርና የልጆቹን መርዶ እንዲሁም የታቦተ ጽዮንን በአሕዛብ እጅ መማረክ ሰምቶ፥ ከወንበሩ
ወድቆ፥ አንገቱ
ተቆልምሞ አጉል ሞት ሞቷል። እናታቸውም ይህንኑ ሰምታ በወሊ ድ ላይ ሞታለች። ፪ኛ ሳሙ ፪፥ ፳፱፣ ፬፥፩ በአዲስ
ኪዳንም አገልጋዮችን
ይመርጥ የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‘’አሥራ ሁሉቱን ደቀመዛሙርቱን ጠርቶ ያወጡአቸው ዘንድ፥ በርኵሳን
መናፍስት ላይ ሥልጣንን ሰጣቸው።‘’ ይላል። የሐዋ ፲፥፩። ከዓለም ለይቶ የመረጣቸውን
እነዚህን ‘’እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ ፍሬም እንድ ታፈሩ፥ ፍሬአችሁም
እንዲኖር ሾምኋችሁ።
እርስ በእርሳችሁም እንድትዋደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ‘’ ብሎአችኋል። ዮሐ ፲፭፥፲፮። ቅዱሳን ሐዋርያት የተከተሉት
ይኽንኑ መንገድ ነው። “እንግዲህ ከዮሐንስ
ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት
ዘመን ሁሉ ከእኛ
ጋር አብረው ከነበሩት ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል፤’’ አሉ። ኢዮስጦስ
የሚሉትን በርናባስ
የተባለውን ዮሴፍን እና ማትያስን ሁለቱን ሰዎች አቆሙ፥ እንዲህም ብለው ጸለዩ፥ “አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ፥
ከእነዚህ ከሁለቱ
የመረ ጥኸውን አንዱን ግለጥ። ይሁዳ ወደ ገዛ ሀገሩ ይሄድ ዘንድ
የተዋትን ይህቺን የአገልግሎትና የሐዋርያነትን ቦታ የሚቀበላትን ግለጥ፤” አሉ። ዕጣም አጣጣሏቸው፥ ዕጣውም በማትያስ
ላይ ወጣ፥
ከአሥራ አንዱ ሐዋርያትም ጋር ተቆጠረ፥” ይላል። ማትያስን በዕጣ የመረጠ እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም ቅዱሳን
ሐዋርያት ዕጣ ያጣጣሏቸው
እግዚአብሔር እንዲመርጥ ነውና። የሐዋ ፩፥፳፪-፳፮። “በአንጾኪያ በነበረችው ቤተክርስቲያን ነቢያትና መምህራን
ነበሩ፤ እነርሱም
በርናባስ፥ ኔጌር የተባ ለው ስምዖን፥ የቄሬናው ሉቅዮስ፥ ከአራተኛው ክፍል ገዢ ከሄሮድስ ጋር ያደረው ምናሔ፥
ሳውልም ነበሩ። የእግዚአብሔርን
ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ፥ በርናባስን እና ሳውልን እኔ ለፈለግኋችሁ ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ያን ጊዜም ከጾ
ሙና ከጸለዩ፥
እጃቸውን በራሳቸው ላይ ከጫኑባቸው በኋላ ላኩአቸው።” የሚልም አለ። የሐዋ ፲፫፥፩-፲፫። ሲሞን መሠሪ ይህችን
የእግዚአብሔር ምርጫ
የሆነች ሥልጣን እንደ ሸቀጥ ለመሸመት ሞክሮ አልተሳካለትም። ቅዱስ ጴጥሮስ፥ “የእግዚ አብሔርን ጸጋ በገንዘብ
ልትገዛ አስበሃልና
ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። በዚህ ነገር ዕድልና ርስት የለህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ልብህ የቀና አይደለምና።
አሁንም ከክፋትህ
ተመለስና ንስሐ ግባ፥ የልቡናህንም ሃሳብ ይተውልህ እንደሆነ እግዚአ
ብሔርን ለምን፤ በመራራ መርዝ ተመርዘህ፥ በዓመፃ ማሰሪያ ተተብትበህ
አይሃለሁና።” ብሎታል። የሐዋ ፰ ፥ ፲፭ – ፳፬። በመጨረሻም በምትሐት ዐርጋለሁ ብሎ በሞከረ ጊዜ፥ ቅዱስ ጴጥሮስ
ቢያማትብበት
ወድቆ ተንቀጫቅጮ ሞቷል።
እንግዲህ አባቶችም ልጆችም የምናውቀውና የምናምነው እውነት ይኽንን
ቢሆንም፥ በቤተክርስቲያናችን የሚታ የውና የሚሰማው ሁሉ ግን ከዚህ እውነት እየራቀ ለመምጣቱ ምስክር መጥቀስ አያሻም። መንግስታት
በተለዋወጡ ቁጥር በተፅዕኖ ቀኖና ቤተክርስቲያን እየፈረሰ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ፀሐይ የሞቀውን እውነት መሸፈን አይቻልም።
የቤተክርስቲያንን መሪዎች የሚመርጠው እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ሌላ ኃይል ከሆነ ሊቀ ካህናቱ ዔሊ እንዳደረገው እግዚ አብሔርን ማሳነስ
ነው። እንደ ንጉሡ ዖዝያን እግዚአብሔርን መድፈር ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ተቀምጦ ከእንደዚህ አይነቱ ግብር ጋር መተባበርም እንደ
ዳታንና አቤሮን፥ እንደ ቆሬን ፥ እንደ አፍኒንና ፍንሐስ፥ እንደ ናዳብና አብድዩም መሆን ነው። በዚህን ጊዜ ለቤተክርስቲያን እንደ
ሙሴ እና እንደ አሮን ያለ ሰው ያስፈልጋታል። በዖዝያን ዘመን እንደ ነበሩት ያሉ ጽኑአን የሆኑ ካህናት ያስፈልጓታል። እንደ ቅዱስ
ጴጥሮስ ያለ ሐዋርያ ጠበቃ ሆኖ ሊቆምላት ይገባል።
ለጥፋቱ ለብቻው የሚጠየቅ ክፍል የለም፥ ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን። ቅዱስ ዳዊት “ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፥ አንድስ እንኳን በጎ ነገርን
የሚያደርጋት የለም።” ብሎአልና። መዝ ፶፪፥፫። የቤተክርስቲያኒቱ ችግር የሰነበተ እንጂ አዲስ አይደለም። ያለፉትን ሃያ ዓመታት
ልዩ የሚያደርገው ግን ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ፥ የአገር ቤት ሲኖዶስ፥ የው ጭው ሲኖዶስ፥ የሀገር ቤቱ ፓትርያርክ፥ ስደተኛው ፓትርያርክ መባሉ ነው። በዚህ ክስተት የተጎዳችው ቤተክርስቲያኒቱ
ብቻ ሳትሆን ሀገሪቷም ጭምር ናት። ክስተቱንም ይዞ የመጣው የመንግሥት ለውጥ መሆኑ ሁሉም የሚያምንበት ነው። አንድ መታወቅ የሚገባው
ትልቅ ጉዳይ ቢኖር፥ የዚህች ቤተክርስቲያን ጉዳይ የአርባ አምስት ሚሊዮን ምእመናን (ሕዝብ) ጉዳይ እንጂ የጥቂቶች ብቻ አለመሆኑን
ነው። የአንድ ሰው ድምፅ እንኳ ሊከበር ይገባል በሚባልበት ዓለም
ተቀምጠን የዚህን ሁሉ ሕዝብ ድምፅ አልሰማም ማለት ምንም አይጠቅምም። በመሆኑም የቤተክርስትያኒቱ ልዩነት ወደ ከፋ ደረጃ ከሚያደርስ
ተግባር ተቆጥበን ለዕርቅና ለሰላሙ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል።
እርቅን የምንፈጽመው ፥ ሰላምንም የምናመጣው ቀድሞም ለምን ተነካን?
አሁንስ ለምን እንነካለን? በሚል መንፈስ ሳይሆን በዚህ ምክንያት የሚመጣ ጉዳት ካለም ስለ ቤተክርስቲያን ብለን በመታገሥ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ የታረቀን ሰላም ንም የሰጠን መከራ መስቀልን ታግሦ በመስቀል ላይ በፈጸመው ቤዛነት ነውና። እኛ በበደልን እርሱ
ክሶ ነውና። ሁላችንም ልንከተለው የሚገባን መንገድ ይህ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “በድላችሁ የመጣባችሁን ብትታገሡ፥ ምስጋናችሁ
ምን ድን ነው? ነገር ግን መልካም እየሠራችሁ የደረሰባችሁን ግፍ ብትታገሡ ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የምታስመሰግን ይህች ናት። ለዚህ
ተጠርታችኋልና፤ ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአል። እርሱም ኃጢአት አልሠራም፥
በአንደበቱም ሐሰት አልተገኘበትም። ሲሰድቡት አልተሳደበም ፥ መከራ ሲያጸኑበት አልተ ቀየመም፥ ነገር ግን እውነተኛ ፍርድን ለሚፈርደው
አሳልፎ ሰጠ። ከኃጢአታችን ያወጣን ዘንድ በጽድቁም ያድነን ዘንድ እርሱ ስለ ኃጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ። በግርፋቱም
ቁስል ቁስላችሁን ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘ በዙ ነበርና፥ አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛ እና ጠባቂ ተመለሱ።” ብሎአል። ፩ኛ
ጴጥ ፪፥፳-፳፭።
ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ
ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ
ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት
ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን
በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ
ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው። በሀገር ቤት ያላችሁ
አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥
ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም። ማን ያውቃል? ዕርቅ ይውረድ ሰላሙ ይምጣ እንጂ እርሳቸውም
“እኔ ሥልጣኑን አልፈልገውም፥ በእንደራሴ ይመራ፤” ሊሉ ይችላሉ።
አንድነቱ ይምጣ እንጂ መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። በመሆኑም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ይህን ወስነናል፤”
እንድትሉን እስከ መጨረሻው ተስፋ እናደርጋለን። በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን
ይሰጣታል። ቤተክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች። አባቶቻችንም በጥቅምትና በግንቦት ሲኖዶስ ይታይ የነበረው
የእርስ በርስ ሙግት ይቀርላችኋል ። እኛም አባቶቻችን ተሰባስበው ተጨቃጨቁ ከሚለው ሰቀቀን እንድናለን። ሃይማኖት አጽንተው ሥርዓት
ወስነው አስተዳደሩን አስተካክለው በፍቅር ተለያዩ ብለን በአራቱም መዓዝን እንሰ ብካለን። እናንተም በሚቀጥለው ስብሰባ እስክትገናኙ
ትነፋፈቃላችሁ። እንዲህ ሲሆን በመካከላችሁ ነፋስ አይገባም። ማንም ተነሥቶ ቀን ከፈለኝ ብሎ “ጳጳሳቱ አይረቡም” አይላችሁም። ዓለም
ይፈራችኋል እንጂ አትፈሩትም። “እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት” ትሉታላችሁ። እንደ አባቶቻችሁ አራዊቱ እንኳን ይታዘዙላችኋል። ልዑላን
ትሆናላችሁ። ስለሆነም፥ ለራሳ ችሁም፥ ለቤተክርስቲያናችሁም፥ ታሪክ ሠርታችሁ እለፉ፥ እኛንም የአባቶቻችንን ገድል ለመጻፍ የበቃን
እንሆን ዘንድ አድርጉን። ይህ ካልሆነ ግን አድሮብን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ያዝንብናል። ኤፌ ፬፥፴።
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን።
La mujer encuеntга la alegr? Fοr bows: Үou can usе ѕugar or sаlt, to еlіminаte dead skin
ReplyDeletecеllѕ fгom the upper lауег
of epidеrmiѕ aгe removed by the аcid pгoduct.
If you nееd to read thrοugh thе finе print
and thе descriрtiοn to learn about
do-it yourself home tantra is rеally stressful.
Stоρ by my wеb blog spa
I loved as much as you will receive carried out right here.
ReplyDeleteThe sketch is attractive, your authored material stylish.
nonetheless, you command get got an edginess over that you
wish be delivering the following. unwell unquestionably
come more formerly again since exactly the same
nearly a lot often inside case you shield this increase.
Here is my web-site :: http://www.iamsport.org/pg/blog/pike1owl/read/16531239/a-guide-to-pilates