Wednesday, October 10, 2012

የፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩት አባላት በእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ተወያዩ



ከጥቅምት 6-11 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሠላሳ አንደኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ይካሔዳል፡፡ 
የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋናው ስባሰባ ደግሞ ጥቅምት 12  እንደሚጀመር እየተጠበቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት እንዱና አንገብጋቢው አጀንዳ የፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከውጪው ሲኖዶስ ጋር ያለውን እርቀ ሰላ በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው አቡነ መልከፄዴቅ ጋር ብቻ ውይይት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ሰሞኑን የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩ ሰባ አባላት    ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ወይይት ማድረጋቸው ተነግሯል ፡፡

በውይይቱም አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ በፊት እንደሚገመተው ሁሉ በገዳም መኖርን እንደሚመርጡና አንድ  ጊዜ የተጣሰው ስርዓት እሳቸው በህይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ እንዲመረጥ እንደማይፈቅዱና እሳችው እስኪያርፉ አሁን እንዳለው ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርክ እየተመራች እንድትቆይ እንደሚሹ ማስታወቃቸውን ምንጮቻችን ዘግበውልናል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤  አሜን፡፡

የፓትርያርክ ምርጫ 

ቅዱስ ሲኖዶስ 1991 . ባወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  ስለ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ምዕራፍ አራት ላይ ያሉትን አንቀፆች እንመ 


አንቀጽ 13
ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ
  1. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ቀኖና በሚፈቅደው መሠረት ተመርጦ ይሾማል፡፡
  2. ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ፓትርያርክ ምርጫ በሚወስነው ቁጥር መሠረት አስመራጭ ኮሚቴ ይቋቋማል::
  3.   ለፓትርያርክነት የሚመረጡት ዕጩዎች ከሊቃነ ጳጳሳት ከጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳት መካከል ሲሆን ብዛታቸው ከሦስት ያላነሡ ከአምስት ያልበለጡ ይሆናል፡፡
  4. አስመራጭ ኮሚቴው እጩዎችን ጠቁሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርባል፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት መሠረት ምርጫው እንዲካሔድ ይደረጋል፡፡
  5. መራጮች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የየመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የጥንታውያን ገዳማት አበምኔቶች የአድባራት አስትዳዳሪዎች ከየሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤያት በዕድሜ ከሠላሳ ዓመት ያላነሱ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች እንዲሁም ዕድሜያቸው 22 አስከ 30 ዓመት የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ሲሆኑ በጠቅላላው በሰበካ ጉባኤው የሚወከሉት ከአንድ ሀገረ ስብከት አሥራ ሁለት ሆነው በሥጋወደሙ የተወሰኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የጸኑ መሆን አለባቸው፡፡
  6. የምርጫው አፈጻጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
  7. የተመረጠው ፓትርያርክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትንና ቀኖናዋን ሊጠብቅና አድልዎ በሌለው መልኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊያስተዳድር ቃለ መሐላ ይፈጽማል፡፡
  8. ከዚህ በላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ ፓትርያርክ ምርጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ ያወጣል፡፡
አንቀጽ 14
የፓትርያርኩ የማዕረግ ስምና መንበር
  1. ፓትርያርኩ ከተሾመበት ቀን ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እገሌ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ይባላል፣ ስሙም በመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጸሎት ይጠራል፡፡
  2. ፓትርያርኩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጨ አገር ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን መንፈሳዊ አባት ነው፡፡
  3. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ መንበር በአዲስ አበባ ከተማ በቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ነው፡፡
አንቀጽ 15
የፓትርያርኩ ሥልጣንና ተግባር
  1. ፓትርያርኩ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቃል፣ ያስጠብቃል፡፡ 
  2.  በዚህ ሕግ አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ በሊቀ መንበርነት ይመራል፡፡
  3. ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 እና በዚሁ ሕግ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 13 መሠረት ፓትርያርኩ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር ሆኖ ኤጲስ ቆጶሳትን ይሾማል፣ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ሲስማማበት ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና ማዕረግ ይሰጣል፡፡
  4. በዚህ ሕግ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 15 መሠረት የተመረጡትን የሥራ ሓላፊዎች ይሾማል፤ በቀደምትነትና በታሪክ የታወቁትን የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና የከፍተኛ አድባራት አስተዳዳሪዎች በየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመረጡ ሲቀርቡለት የማዕረግ ስም እየሰጠ ይሾማል፡፡
  5. ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የመንግሥትን ፈቃድ ማግኘት በሚያስፈልግበት ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰነ በተግባር ላይ ያውላል፡፡
  6. ቅዱስ ፓትርያርኩ በዓበይት ጉዳዮች ላይ ሁሉ በቅዱስ ሲኖዶስ አያስወሰነ ይሠራል፡፡
  7. በቅዱስ ሲኖዶስ የወጡ ሕጐች፣ የተላለፉ መመሪያዎችና ውሳኔዎች ሁሉ በተግባር ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
  8. በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጡትን ሕጐችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በፊርማው ያስተላልፋል፡፡
  9. ከመንግሥታውያንም ሆነ መንግሥታውያን ካለሆኑ /ቤቶች ድርጅቶችና ግለሰቦች የሚቀርቡ ደብደቤዎች ወይም አቤቱታዎችን ደረጃቸውን ጠብቀው በሕግ መሠረት ይፈጸሙ ዘንድ ለጠቅላይ /ቤት ያስተላልፋል፡፡
  10. በውጭ አገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ለማገልገል ወይም የነፃ ትምህርት ለመማር የሚላኩ ካህናት በዚሁ ሕግ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 11 መሠረት ተመርጠው ሲቀርቡ እንዲላኩ ያደርጋል፡፡
  11. ከውጭ የሚመጡትን እንግዶች በውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቅራቢነት እየተቀበለ ያነጋግራል፡፡
  12. ፓትርያርኩ በውጭ አገር በሚደረግ በማናቸውም ስብሰባ ላይ ለመገኘትና ጉብኝት ለማካሔድ በሚያስፈልግ ጊዜ ስለተልዕኮው ጉዳይ አስቀድሞ በቅዱስ ሲኖዶስና በቋሚ ሲኖዶስ ያስወስናል፡፡
አንቀጽ 16
የፓትርያርኩ ከማዕረግ መውረድ
  1. ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ሓላፊነት በመዘንጋት፡-
        ሀ. የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ ቤተ ክርስቲያንን የሚያሰነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣
    ለ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሠረት በደለኛ መሆኑ ከታመነበት፣
     ሐ. በቃሉ የማይገኝና በዚህ ሕግ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 7 ድንጋጌ መሠረት በተሾመበት ቀን የፈጸመውን ቃለ መሐላ ያልጠበቀ በአጠቃላይ ታማኝነቱና መንፈሳዊ አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነትን ያጣ ሆኖ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከሥልጣኑ ይወርዳል፤ በምትኩም ሌላ ፓትርያርክ ተመርጦ ይሾማል፡፡
     2.  ከዚህ በላይ በተደነገገው መሠረት ከሥልጣኑ የተገለለ ፓትርያርክ በቀኖና ተወስኖ በገዳም ይቀመጣል፡፡
    3. ከሥልጣን የተገለለው ፓትርያርክ በገዳም አልቀመጥም በቀኖናም አልወሰንም በማለት እምቢተኛ ከሆነ ተወግዞ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይለያል፡፡
      4.  ፓትርያርኩ መንፈሳዊ ሥራውን በማካሔድ ላይ እያለ እሥራትና ግዞት ቢደርስበት ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ትመራለች እንጂ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም፡፡
       5. ከዚህ በላይ የተዘረዘረው ሁሉ ፍትሕ መንፈሳዊ በሚያዝዘው መሠረት ይፈጸማል፡፡
አንቀጽ 17
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ 
  1.  ፓትርያርኩ በሞት ሲለይ ወይም በዚህ ሕግ አንቀጽ 16 መሠረት ከሥልጣኑ ሲወርድ ቅዱስ ሲኖዶስ በሹመት ቀደምትነት ካላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በዕለቱ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ መርጦ ይሾማል፡፡ የተተኪው ፓትርያርክ ምርጫም ይካሔዳል፡፡
  2. የተተኪው ፓትርያርክ ምርጫ አፈጻጸም እንደጊዜውና እንደሥራው ሁኔታ እየታየ 40 እስከ 80 ቀን ባለው ጊዜ ይሆናል፡፡ 
  3.  የዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ተግባር
. ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ጊዜያዊ ጉደዮችን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር እየመከረ ያከናውናል፡፡
. በፓትርያርኩ ምርጫ ጊዜም የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ሆኖ ምርጫውን ያስፈጽማል፤ እርሱ ግን ከምርጫው አይገባም፡፡
/ምንጭ፦ ሕገ ቤተ ክርስቲያን 1991 ./


11 comments:

  1. በእውነት ደስ የሚል ዜና ነው!!!
    እንዲህ ከሆነ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነቷ በቅርብ ይመለሳል:: አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ትሆናለች!!!

    ግን ለምንድን ነው እናንተ በዚህ ሰአት የፓትርያርክ ምርጫ እንዴት እንደሚከናወን የምትጽፉልን? ፓትርያርክ መመረጥ የለበትም እየተባለ፣ ፓትርያርክ በዚህ በዚህ ሁኔታ ይመረጣል ትሉናላችሁ! እርቀ ሰላሙን የሚያጠናክር ስራ ለምን አትሰሩም ?
    ስለ እውነት ሃሳባችሁ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወንድማችን ሃይሉ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ለማሳየት እንጂ እርቁ የሚያደናቅፍ ምንም እዚህ ላይ የፃፍንው የለም ሁሌም ቢሆን የምናስቀድመው እርቀ ሰላም መኖሩን ነው፡: መለያየቱ ጉዳት እንዳለው ሁሉ አንድነቱ ደግሞ እጅግ በጣም ላቅ ያለ ጥቅም አለው። አሁን በምናየው ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን እንደተከፈለች ብትቀጥል ጉዳቱ ምንድን ነው ? እርቀ ሰላም ተደርጎ ቤተ ክርስቲያን አንድ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? የሚሉትን መዳሰሱ የሚመለከታቸው ሁሉ ጉዳዩን ተረድተው እና አምነውበት የድርሻቸውን እንዲወጡ መደረግ አለበት። መለያየት መድኃኒት የሚያሻው የነፍስ በሽታ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሥጋ ሥራዎችን ሲዘረዝር ከጠቀሳቸው መካከል አንዱ መለያየት ነው። ገላ ፭፥፳፩ ። ፈውስ የሚያስፈልገው ሕማም ከሆነ ዘንድ እስኪሽር ድረስ መከታተል እና ወዲያውኑ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል። ሁሉ ነገር ከመደረጉ በፊት እርቅ የቀድማል ባዮች ነን ስለ አስተያየትህ ግን በጣም እናመሰግናለን፡፡

      Delete
  2. ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እግዚአብሔር ይጠብቀወት!

    በ እውነት በህይወት ይህንን ማየትዎ በጣም አስደስቶኛል! ፍጻሜውን ያሳምርልን!

    ReplyDelete
  3. "የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅ የተሰወረ የለም" እንዳለው ወንጌሉ ሁሉም በጊዜው ይሆናል!!!

    አባቶቻችን ታሪክን የሚሰሩበት ጊዜ አሁን ነው! እኛም በጸሎትም በሃሳብም አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል:: የ20 አመት ዘመን ክፍፍል ይበቃናል::

    ReplyDelete
    Replies
    1. lante gondera kaltemerte hulm neger tikekil aydelem?

      Delete
  4. የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ጉዳይ ምን ደረሰ??
    እሳቸው በህይወት እያሉ ሌላ የጠ/ሚኒስትር ምርጫ መደረግ የለበትም፡፡
    ችግሩ እሳቸው በገዳም ለመኖር የሚፈቅዱ አይመስለኝም፡፡
    ለማንኛውም ይጠየቁ እና ሀሳባቸውን እንስማ፡፡

    ReplyDelete
  5. ዋልድባንና ገዳማቷን አሐቲ ቤተክርስቲያናችንን ህዝቧን ከመከራ የሚጠብቅ አባት ያምጣልን አሜን፡፡ ፈጣሪ የመንግስት ምርጫ አያድርግብን

    ReplyDelete
  6. zenaw ewunet kehone ewunet Ejig des yemiasegn new

    ReplyDelete
  7. God bless ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ

    ReplyDelete
  8. Abune Merkoryos is not a legitimate patriarch for our church, not accepted by Egypt Orthodox Church too.
    So with what legal ground could he be the next?
    Remember fellow Ethiopians, this is not about political power but it’s about serving our lord Jesus Christ and its people.
    Some people acts and think abnormal. What race got to do in the case of religion? His holiness suffered too much because he is from Tigrai and blaming his association with the government, but why?
    Why don’t you raise a single question when Abune Merkorios keeps silent when civilians suffer from bombardment in the time of Mengestu? Yes cuz he is not Tigra!
    When we will emancipate ourselves from such a kind of devilish thinking?
    May God help those who stuck on the mentality of zemene mesafent………
    God bless Ethiopia

    ReplyDelete
  9. የተሳሳተ መረጃ ያየሁ መሰለኝ የሚሾመው ፓትርያርክ መጠሪያ ስም ወይም የማእረግ ስም ብጹእ ወቅዱስ እገሌ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ብቻ እንጂ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም አልመሰለኝም…..ይህን መረጃ ከተሳሳትኩ አርሙኝ…ስለመረጃችሁ እንመሰግናለን…..

    ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን፡፡

    ReplyDelete