Friday, October 5, 2012

ሙሽራው ተሰወረ እውነተኛ ታሪክ



ሰሞኑን የተፈፀመ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው ሙሽሪት እና ሙሽራው የተክሊል ስርዓታቸውን ሊፈፅሙ ከሚዜዎቻቸው ጋር ወደ ታላቁ ደብር  በጣም ብዙ ህዝብ የሚበዛበትም ቤተ ክርስቲያን  ያመራሉ  ::
በዚያም ሙሽሪት በሴቶች መግቢያ : ሙሽራው በወንዶች መግቢያ ከሚዜዎቻቸው ጋር እንዲገቡ ይሆንና በየመግቢያቸው ገብተው ስርዓተ ተክሊሉ ከሚፋፀምበት ለመገናኘት ይለያያሉ፡፡ 
ሙሽሪት መንገዱ ቀና ሆኖላት በስርዓቱ ላይ የታደሙትን እና ለቅዳሴ ለፀሎት የቆሙትን ሁሉ አላፋ ስርዓተ ተክሊሉ ከሚፋፀምበት ትደርሳለች::  ደቂቃዎች አለፉ ስርዓተ ተክሊሉን የሚፈፅሙት ካህናት ግራ ተጋቡ ሙሽሪት ብቻ ቀርባለችና::  ሙሽራን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ ግራ የተጋቡት ካህናትም ምዕመናን መንገድ ዘግተውበት ከሆነ ብለው "እባካችሁ ሙሽራውን መንገድ አሳልፍት" እያሉ በድምጽ ማጉያ ደጋግመው መልእክታቸውን አስተላለፉ :: ከሰዉ መብዛት የተነሳ  መንገድ ተዘግቶበት ከሆነ ይመጣል የተባለው ሙሽራ ግን የውኃ ሽታ ሆነ፡፡ መቼም አያድርስ ነው የሚባለው ሙሽራው ወዴት ተሰወረ?፡፡ መቼም     "LAW አልተማርኩም" እናዳለው እኔም    "LAW አልተማርኩም"    እና በማንም አልፈርድም ግን ሁሉንም አምላክ ለበጎ አደረገው እላለህ ፡፡ እርሶ በሙሽሪት ቦታ ቢሆኑ ምን ይላሉ?

2 comments:

  1. ለበጎ ያድርግላቸው: ነገር ግን እኔ ሙሽሪትን ብሆን ብሎ የሚናገር ያለ ካለ የተሳሳተ ነው ሆኖ መገኘትና ቆሞ ማየት ምን ያህል ልዩነት እንዳለው ግልጽ ነው : እግዚአብሄር ያስባቸው አሜን

    ReplyDelete
  2. betam ymigrem new ena behonma neseha gebech menane megebat new lela mene maderg echelalhu amelak ken hatyateghwa gar endynor felego lihon yechelale man yawkal!!!!!!!!!!

    ReplyDelete