Friday, October 12, 2012

የታሪካዊው እና የጥንታዊው የጋዴና ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

  •          ይህ ቤተክርስቲያን የሚገኜው በድቡብ ወሎ ሐገረ ስብከት በደሴ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት ከደሴ ከተማ ወደ ወራኢሉ እና ለጋምቦ ወረዳ አቅጣጫ 64 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው ፡፡
  •          በሐገራችን ብሎም በሐገረ ስብከታችን በውጭ ሀገራት ሁሉ የሚታወቁ 3 ታላቅ አድባራት አሉ እነርሱም 1ኛ. በሐይቅ አስተዳደር  የሚገኜው ደብረ እግዚአብሔር 2ኛ. በደሴ ዙሪያ የሚገኙት መካነ ሥላሴ እና ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ናቸው፡፡
  •     ይህ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተው በአፄናኦድ ዘመን በከበሩ ድንጋዮች እና እነ ቅዱስ ላሊበላ ባነጹበት ተመሳሳይ ድንጋዮች የታነጸ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በዚህ ቤተ ክርስቲያን የነበሩት  ካህናት ብዛት 1000/አንድ ሺ/ ነበሩ፡፡
  •          በዚህ ቤተ እግዚአብሔር በምላት መንፈሳዊ አገልግሎት እየተሰጠበት በገቢረ ተአምራቱ ካህናቱና ምዕመናኑ እየተጠቀሙበት ከኖረ በኋላ ክፉ ዘር የሆነ ሰይጣን የግብር ልጁን ግራኝ አህመድን በማስነሳት ህዳር 7ቀን 1524 ዓ.ም ይህን ቤተ ክርስቲያን አቃጥሎ ከካህናቱ አንዱ ሲተርፉ 999 ካህናት በአንድ ቀን ሰማዕት ሆነዋል በተለይም 5ቱ ካህናት በቤተ መቅደስ በአገልግሎት ላይ እንዳሉ በደንደሳቸው አርዶአቸዋል የእነርሱም ደም እንደጎርፍ ፈሶ የተቀላቀለበት ወንዝ ደም ባሕር ተብሎ እስካሁን ይጠራል ሲጠጡት ጨው ጨው ይላል ምክንያቱ የእነዚህ የሰማዕታት ደም ስለተቀላቀለ ነው ፡፡
  •         የጥንቱ ቤተ ክርስቲያን ከቃጠሎ የተረፉ 4ትክል አምዶች እና ዙሪያውን የተቃቀፉ 13 የጥድ አጸዶች ከዚህ ደብር መካነ ሥላሴ የሚያገናኝ የተዘጋ ዋሻ ያለው ሲሆን ይህን ቦታ ሄዶ ላየው ቤተ ክርስቲያኑ ቢቃጠልም ጸጋ እግዚአብሔር ያልተለየው  ከነ ግርማው ጉብ ብሎ የሚታይ ቦታ ነው ፡፡
  •          ከ600 ዓመት በላይ መስዋዕተ እግዚአብሔር ሳይሰዋበት የእጣኑ መዓዛ ሳይሸትበት የኖረ ሲሆን አሁን በእግዚአብሔር  ፈቃድ እሱ ወዶ ባስነሳቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች አነሳሺነት በሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አትናቴዎስ እና በሐገረ ስብከቱ እና በደሴ ዙሪያ ቤተ ክህነት  የክፍል  ኃላፊዎች መልካም ፈቃድ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከምዕመናን በሚገኝ ድጋፍ 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ወደ መጠናቀቅ ደርሶአል
  •          ይህንን ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ነገር አጠናቆ በዚሁ ዓመት በቅርብ ጊዜ  እንደሚመረቅ ይጠበቃል ፡፡
       ስለዚህ አሁን እንደ አዲስ የሚቋቋም ቤተ ክርስቲያን በመሆኑ ብዙዎች ለዚህ ጥሪ ቀልጠፍ ብለው ምላሺ ሰጥተዋል  እርስዎም ለዚህ ጥንታዊ ደብር በገንዘብዎ፣በጉልበትዎ፣በጸሎትዎ፣በሙያዎ የበኩልዎን ድርሻ እንዲወጡ ይጠበቃል ፡፡
አሁን የሚቀሩን ስራዎች
·         የቤተ ክርስቲያኑ የማጠናቀቂያ ስራዎች
·         የቤተ ክርስቲያኑ ዕቃ ቤት/ሙዜም /መገንባት
·         ለካህናት ማረፊያ ቤት
·         የቤተ ክርስቲያኑ አጥር
·    ከዋናው መንገድ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የ4ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ
·         ንዋየ ቅድሳት
·         ዙሪያውን በአሕዛብ የተከበበ 3ቤተ ሰብ ምዕመናንብቻ ያሉት በመሆኑ እና  ካህናት ከሌላ ገዳማት በማስመጣት ለካህናት ደመዎዝ በዚህ ስሪት ለመስራት ዘላቂ የልማት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ እነዚህን ስራዎች ለመስራት በርካታ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑ እርስዎም በሚቻልዎት አቅም ለመለገስ  ፈቃደኛ በመሆን በደብሩ ስም የተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ጦሳ ቅርንጫፍ ደብተር ቁጥር 36 ብለው መለገስ ይችላሉ፡፡
·        በአካል መርዳት ከፈለጉ የኮሜቴዎች ስልክ ቁጥር 0910139967፣0913821001፣0914715828፣0920128536
በእነዚህ መንገዶች የተቻለዎትን ትብብር እንዲያደርጉ በቅዱስ ዮሐንስ ስም እናሳስባለን ፡፡
   የጋዴና ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ 

" በኃይልህ ሰላም፥ በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን::" መዝሙረ ዳዊት 122፥7        

2 comments:

  1. Too much caffeine consumed from the mother can pass via a breast feeding mother's milk and cause the baby to be fussy, irritable and possess a difficult time sleeping. Next, plan out a finances for the infant shower menu and divide the expected charges evenly.

    My blog ... best portable baby swing - http://www.healthmassagechairs.org/Programs-In-Baby-Swing.htm -

    ReplyDelete
  2. Hi there I am so grateful I found your site, I really found
    you by error, while I was researching on Yahoo for something else,
    Anyhow I am here now and would just like to say thanks a lot for a fantastic post and a all round enjoyable blog (I also
    love the theme/design), I don’t have time to browse
    it all at the minute but I have saved it and also
    added your RSS feeds, so when I have time I will be back to read more, Please do keep
    up the fantastic b.

    My homepage :: Beats Monster

    ReplyDelete