Thursday, October 4, 2012

"LAW አልተማርኩም"

(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 24,2005 ዓ.ም) አንድ ወጣት የህይወቱ መመሪያ የሚሆኑ ሃሳቦች ቢያገኝና መንፈሳዊ ህይወቱ እንዲጎለብት ይመኝ ነበር።
ለምሳሌ: ስለሐሜት ፣ ስድብ ፣ ትዕቢት፣ ክርክር እና ሌሎች የስጋ ፍሬዎች ለተባሉት መከላከያ ይፈልጋል።
 
አንድ ቀን አንድ አባት በቤተ ክርስቲያን ለወጣቶች በወንድም ላይ ስለመፍረድ እያስተማሩ "----በዚህ ዓለም እንክዋ መፍረድ የሚችለው ሕግ ወይም በእናንተ  ቋንቋ
ው (LAW) የምትሉት ትምህርት የተማረ ነው። ሌላው አውቃለሁ ብሎ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ  ቢፈርድ ፍርዱ ያዛባዋል።“ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥:20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። “ ገላ.5:14- 21 ታዲያ እኛስ መች ተምረን መችስ ተመርቀን ነው በወንድማችን ላይ የምንፈርደው?     ይልቅስ እንዲህ አይነት ሃሳብ ሲመጣባችሁ "LAW አልተማርኩም" እያላችሁ መልሱት ---------- "
አባት ትምህርታቸውን ቀጠሉ ወጣቱ ግን ይህቺ ሃሳብ ከሚፈልጋቸው መመሪያዎች አንዷ ነበረችና እንዳትጠፋው በልቡ ጥሩ ቦታ ለመስጠት ይጣጣራል + LAW አልተማርኩም + LAW አልተማርኩም።
ይህ ወጣት ከዚያች ቀን ጀምሮ የህይወቱ መመሪያ አደረጋት። በወንድሙ ላይ የመፍረድ ሃሳብ ሲመጣበት ፍፁም አይረሳትም።
በዕድሜ እያደገ ሲሄድ ትህትናውና የመንፈሳዊ ህይወት እድገቱም ባልታሰበ ሁኔታ እያደገ ሄደ። አንዳንዶች "ለበጎ ነው" የሚለውን ቃል እንደምዋሃዳቸው ይህቺ ቃልም ተዋሃደችው።
ህይወት በዚህ ሲቀጥል ከሰው ሁሉ የማይቀረውን ሞት ደረሰው። መላእክተ ብርሃንም እየዘመሩ በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡት። እግዚአብሔር የዚህ ሰው ትህትናው በዛ ለነበሩት ሊያሳያቸው ስለወደደ
"አንተ በምድር በሰራኸው ሥራ በገነት ትልቅ ቦታ ተሰቶሃልና ደስ ይበልህ።" አለው እግዚአብሔር።
ሰውየውም በታላቅ ትህትና ሰገዶ አመሰገነ።
"አንተ ከባለሟሎቼ አንዱ ሆነሃል ስለዚህ ይህችን ነፍስ (ለፍርድ የመጣችውን ሌላ ነፍስ እያመለከተ) ምን እንፍረድላት?" እግዚአብሔር ጠየቀ።
ሰውየውም እግሩ ስር በመስገድ "እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ እኔ LAW አልተማርኩም።" አለ የለመደውን።
እግዚአብሔርም "እንዴ ! ሕጌ ስላወቅህና ስለተገበርክ እኮ በገነት ታላቅ ቦታ ተሰጥቶሃል።"አለው
ሰውየውም እየተንቀጠቀጠ "አምላኬ ሆይ ! አሁንም ይቅር በለኝ አንድ የአንዲት ሀገር ዜጋ የሀገሪቱን ሕግ ማወቅ ግድ እንደሚልበት የአንተ ልጅ የመንግስትህም ዜጋ ለመሆን ስለምወድ ሕግህን አወቅኩ እንጂ ለመፍረድ የሚያበቃ ትምህርት አልወሰድኩም፣ አልተማርኩም፣ አልተመረቅኩምም።" ብሎ መለሰ
እግዚአብሔርም ይህ ሰው በወንድሙ ላይ ባለ መፍረዱ ሌሎቹ (ትዕቢት፣ ክርክር፣ ስድብ፣ ---- ) የስጋ ፍሬዎች እንደጠፉለት ነገሯቸው "ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" ብሎ መንግስቱን አወርሰው።
LAW  አልተማርኩም !
!

«የሚጐድለኝ ምንድር ነው»? (ማቴ ፲፱ ፥ ፳)... የሚታየን የሰው ጉድለት እንጂ የራሳችን አይደለም። ቃሉ «እንዳይፈርድባችሁ አትፍረዱ። (ንጹሕ ሳትሆኑ አትፍረዱ)። በምትፈርዱት ፍርድ ይፈረድባችኋልና ፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋልና። በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ (ትንሹን ኃጢአት) ለምን ታያለህ? በአንተ ዓይን ያለውን ምሶሶ (ታላቁን ኃጢአትህን) ግን አታስተውልም? ወንድምህን በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ተወኝ እንዴት ትለዋለህ? (በኃጢአትህ ልፍረድብህ ለምን ትለዋለህ)? እነሆ ፥ በአንተ ዓይን ምሶሶ አለ። (በሰውነትህ ታላቅ ኃጢአት ተሸክመሃል)። አንተ ግብዝ አስቀድመህ በአንተ ያለውን ምሶሶ አውጣ ፥ (በመጀመሪያ ስለ ታላቁ ኃጢአትህ ፥ ስለበዛው ጉድለትህ በራስህ ላይ ፍረድ) ፥ ከዚህ በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።» እያለን ወደ ራሳችን መመልከት ፥ ጉድለታችንን ማየት አልተቻለንም። ማቴ ፯፥፩። ጌታችን የወንድምን ኃጢአት በጉድፍ ፥ የራስን ኃጢአት በምሶሶ ፥ በሰረገላ መስሎ ያስተማረው የባልንጀራችንን ኃጢአት የምናውቀው ጥቂቱን ስለሆነ ነው። የራሳችንን ግን ከራሳችን ጠጉር ቢበዛም ሁሉንም እናውቀዋለንና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ፦ « አንተ ሰው ሆይ ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልሳለህ? በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠራዋለህና . . . . . አንተ ሰው ሆይ ፥ በሌላ ላይ አይተህ የምትጠላውንና የምትነቅፈውን ያን አንተ ራስህ የምትሠራው ከሆነ ፥ ከእግዚአብሔር ፍርድ እንደምታመለጥ ታስባለህን? »ብሏል። ሮሜ ፪፥፩-፫፦ እኛስ የሚጐድለን ምንድነው?....

ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን !

3 comments:

  1. Kale Hiwot Yasemalen

    ReplyDelete
  2. kale hiwot yasemalen!!!

    ReplyDelete
  3. kale hiwot Yasemalen. teru mekere nawu leyame lebona yesetane.

    ReplyDelete