Wednesday, August 15, 2012

በገዳማት ላይ እየተከሰተ ባለው ጥቃት በተመለከተ የተደረገው ስብሰባ

ባለፈው እንዳስነበብናችሁ በገዳማት ላይ እየተከሰተ ባለው ጥቃት በተመለከተ ስብሰባ

መጠራቱ ይታወሳል::   በተለያዩ ሃሳቦች ላይ ተወያይቷል ከሴቭ ዋልደባ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው ነው ከሴቭ ዋልደባ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው ነው 

የዋልድባ ጉዳይ ዋና መነጋገሪያው ነበር

  • ዋልድናን ለመታደግ ምን እንርዳ?
  • ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የቤተክርስቲያን ህልውና ለማስከበር መተባበር ግድ ይለናል
  • የዋሽንግተን ዲሲ ካህናት ለምን አይተባበሩም
  • ጥቂት ካህናት ዋልድባ ምንም እንዳልተነካ የሃሰት መረጃዎችን ለሰው እያስተላለፉ ይገኛሉ
 ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ዋልድባን ለመታደግ የሚንቀሳቀሰው የዋሽንግተን ዲሲ ንዑስ ክፍል የጠራው ስብሰባ ላይ ዋልድና እና በዋልድባ አካባቢ በሚደረጉት ሥራዎች ዙሪያ በርካታ ውይይቶች ተደረጉ። በዚህ ጉባኤ ላይ ካህናት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከደረሰን ሪፖርት ለማረጋገጥ ችለናል።


የጉባኤው ተካፋይ በርካታ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን በጉባኤውም ላይ በርካታ ቁምነገሮች ተነስተውበታል ከነዚህም በጥቂቱ:
  • ቤተክርስቲያን የወጣቱ ብቻ ሳይሆን የካህናት፣ የሽማግሌዎች፣ እና በአጠቃላይ የመላው ኢትዮጵያውያን ነች
  • ቤተክርስቲያን መጠቀሚያ ብቻ ሳትሆን በችግሯ ጊዜም ልንቆምላይ ይገባናል
  • እያንዳንዱ የኦርቶዶክስ አማኝ የየራሱን ተሳትፎ ሊኖረው እንደሚገባ ተጠቁሙዋል
  • ለቅድስት ቤተክርስቲያን በቁርጠኝነት ምን ማድረግ እንዳለበት በዝርዝር ተመክሯል
  • ዘርፈ ብዙ የሆኑ የቤተክርስቲያን ችግሮችን በጋራ እንዴት መቅረፍ መቻል እንዳለበት
  • በዚህ ጉባኤ መሳተፍ ያልቻሉት ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ይበልጡኑ ካህናት እንዴት ማምጣት እንችላለን
  • በቀጣይነት ሊሰሩ ስለሚችሉ ሥራዎች በዝርዝር ተጠቁመዋል
በጉባኤው ላይ በይበልጥ የተነሱት ይሄንን እንቅስቃሴ ሌላ የፖለቲካ ወይም የማኅበራት አጀንዳ ተደርጎ በተለያዩ ክፍሎች የሚነገረው ትክክል እንዳልሆነ እና ማንም በዚህ እንቅስቃሴ መጠቀም እንደሌለበት በአትኩሮት የተሰመረበት ጉዳይ ነበር። ይህ እንቅስቃሴ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኗን ችግር ለአለም ህብረተሰብ ችግሮቿን ማሳወቅ እና ችግሮቿንም በልጆቿ እንዲፈታ ያለ መንግሥት ወይም የሌላ ሃይል ሳይኖር ለቤተክርስቲያን የሚቆም Advocacy group ማቋቋም መሆኑን በጉባኤው ላይ የተነሱ ነጥቦች ነበር።

በሌላ በኩል በአካባቢያችን አንዳንድ ካህናት ከቤተክርስቲያን ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን አጀንዳ እና ጥቅም በማስበለጥ በየሰፈሩ እና በቤተክርስቲያናቸው አውደ ምሕረት ላይ በመቆም የተዛባ መረጃ በመስጠት ይህንን የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማኮላሸት የሚያደርጉትን ድርጊት እንዲታቀቡ፥ ችግራችን የዘር፣ የወንዝ፣ የጎጥ ሳይሆን ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን የአዳም ዘሮች ነን የምንል ክርስቲያኖች በሙሉ በአንድ ዓላማ ላይ መቆም እንደሚገባን የጉባኤው ተሳታፊዎች በአጽንዖት ገልጸውታል። 


ጉባኤውም ተጨማሪ ሃያ ሰዎችን መርጦ በሚቀጥለው ጉባኤ ላይ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ሥራ መግባት እንዳለብን በመጪው October 7, 2012 በድጋሚ ለመገናኘት ቀን ቆርጦ ተጨማሪ ጉባኤ ማዘጋጀት እና ለተጨማሪ ሥራ መዘጋጀት እንዳለበት በድጋሚ የተሰመረበት ጉዳይ ነበር። በመጨረሻ ለመጪው October በድጋሚ ቀጠሮ ይዞ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

እግዚአብሔር ገዳማቱን አድባራቱን ከጠላት ይጠብቅልን ፡፡ 

 

1 comment: