Saturday, August 18, 2012

ደብረ ታቦር


+++++++++++++++እንኳን ለታላቁ ለደብረ ታቦር በአል አደረሳችሁ+++++++++++++

እግዚአብሔርና በሰው ልጆች ግንኙነት ውስጥ ጥልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ድርጊቶች እና ክንውኖች በዓመቱ ውስጥ ቀናት ተመድበውላቸው በበዓላትና በአጽዋማት መልክ ይታሰባሉ፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን እነዚህን በዓላትና አጽዋማት የምታከብርበት ዓመታዊ መርሐ ግብር እና በበዓላቱና በአጽዋማቱ የሚታሰበውን ነገር አስመልክቶ አባላቶችን የምታስተምርበት ሥርዓተ ትምህርት አላት፡፡ እንደዚህ ባለ መርሐ ግብር ከሚታሰቡት መካከል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ያደረጋቸው ነገሮችና ያስተማራቸው ትምህርቶች /ፅንሰት፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ስቅለት፣ ትንሳኤ፣ ዕርገት፣ ደብረ ታቦር፣ምጽአት/ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት  /ልደቷ፣ ዕረፍቷ፣ ቤተመቅደስ መግባቷ፣ ድንቅ ተአምራት ያደረገችባቸው ዕለታት/፤፣ የቅዱሳን በዓላት /ልደታቸው፣ ዕረፍታቸው፣ ተአምራት ያደረጉባቸው. . / ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡ ከነዚህ ውስጥ ዋነኛው ደብረ ታቦር ነው 
ትንቢት:-  ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ መዝ 8812

በአጭሩ:- ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡- ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ "በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ" "አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ"ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡- ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡- ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፡- የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው። ደቀ መዛሙርቱም፡- እንግዲህ ጻፎች፡- ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም መልሶ፡- ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።"ማቴ 171-13
ሙሴን ለምን በዚያ አመጣ ቢሉ :- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡
ኤልያስንስ ለምን ቢሉ ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡ በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ አምላከ ሙሴ እግዚአ ኤልያስ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡ እንደገናም ሙሴ የሕጋውያን ኤልያስ የደናግል ምሳሌ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የተጠሩት ሁለቱም ወገኖች ናቸውና ፡፡
 ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት በአላትም አንዱ ነው፡: ከደብረ ታቦር ተራራ ባጠቃላይ ከተፈፀምት ኩነቶች የምንረዳው አስተምህሮአችን መሠረቱን በነቢያትና ሐዋርያት ላይ ያደረገ መሆኑን በቅዱሱ ተራራ ላይ የተገኙት ነቢያትና ሐዋርያት ምስክሮች ናቸው፡፡ እኛም በነቢያትና ሐዋያርት መሠረት ላይ ታንጻችኋል ተባለልን፡፡ ስለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የታመነ ምስክርነት አግኘተናል፡፡ አስቀድሞ ሐዋርያው «በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ/ዮሐ11/ በማለት የሰጠንን ምስክርነት እንደገናም ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ ላይ አደረ በማለት ያመጣውን ቅድመ ዓለም ከአብ ያለእናት በዚህ ዓለም ቅድስት ከምትሆን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ያለአባት የተወለደውን አምላክ ወልደ አምላክ በማመን የወንጌል ጋሻን ደፍተን የእምነት ወንጌልን ተጫምተን በማመን እንበረታለን እንጂ ባለማመን ምክንያት አንጠፋም፡፡ ክርስቲያኖች ምስጢረ መለኮቱን የገለጠበትን ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ የሆነውን የደብረ ታቦርን በዐል የምናከብረው በዚህ መንፈስ ነው ፡፡ 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠብቃ ለትውልድ ካስተላለፈችው ታላላቅ መንፈሳውያት እሴቶች መካከል በጌታችን  በእመቤታችንና በቅዱሳኑ ሥም በዓላትን ማክበር ነው ፡፡ ከእነዚህም በዓላት መካከል አንዱ የደብረ ታቦር በዐል ነው፡፡ በዓሉም በተለየ መልኩ ይከበራል፤ ዳቦ በመድፋት፤ ጠላ በመጥመቅ፤ በተለይም የአብነት ተማሪዎች ከሕዝቡ በመለመን ስሙን ይጠራሉ፡፡ ይህ ልንጠብቀው የሚገባን መንፈሳዊ እሴታችን ነው፡፡ ጌታችን የቅዱሳኑን መታሠቢያ በተመለከተ ሲናገር በደቀ መዝሙር ሥም ቀዝቃዛ ዉኃ ብቻ ያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም እንዳለ /ማቴ.1042/ በባለቤቱ ሥም የሚደረገውማ እንደምን አብዝቶ ዋጋ አያሰጥ፡፡ ለሚወዱኝ እስከሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ /ዘጸ.216/ ስላለ በዓሉን በማክበር የበረከቱ ተሳታፊ መሆን ይገባል::

+++
ለቅዱሳኑ ለታደሉቱ ምስጢሩን የገለጠ ለእኛም ምስጢሩን ይግለፅልን++++

4 comments:

  1. I use them around the door handles that become
    magically sticky with the end with the day. Since
    January 1, 2011, the demographic transition became real for seniors'the oldest turned 65.

    my homepage :: best Baby swings Reviews - cookfl.com -

    ReplyDelete
  2. Hi there! I understand this is sort of off-topic however I had to ask.
    Does managing a well-established website like yours require a lot of work?
    I'm completely new to running a blog but I do write in my journal everyday. I'd like to start a blog so I can
    share my personal experience and feelings online. Please let
    me know if you have any recommendations or tips for brand new aspiring bloggers.
    Thankyou!

    Here is my web site - cuisinart stand mixer reviews (www.bet-get.com)

    ReplyDelete
  3. This web site truly has all of the information and facts I needed concerning this subject and didn't know who to ask.

    My blog post cuisinart stand mixer reviews (http://specialbookmark.16mb.com/News/thoughts-on-goods-in-stand-mixers-4/)

    ReplyDelete
  4. Great beat ! I wish to apprentice while you amend your
    site, how can i subscribe for a blog web site? The account helped me a acceptable deal.
    I had been a little bit acquainted of this your broadcast
    offered bright clear concept

    My homepage :: cuisinart stand mixers (look-at-that.com)

    ReplyDelete