ደቂቀ ናቡቴ

Monday, December 24, 2012

የ ግብጹ የሙስሊም ብራዘር ሁድና ማህበረ ቅዱሳንን ምን አገናኛቸው ???

(በሁሉባንተ አበበ)

ጽሁፎችን በተለያየ መልኩ ስንጽፋው ለመነበብ አሰልችነቱን እንቀንሳለን ዛሬ እንዲህ  አስቤአለሁ አስኪ  . . . .  ከተመቻችሁ ተከተሉኝ  አስተያየት እቀበላለሁ ካልሆነም ደግሞ በፍጥነት ብሎጉን ዘጋ ማድረግ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም እድሜ ለነ ጎግል ዛሬ የኢሜል ያክል ብሎጎች እንደ አሸን ፈልተዋል   እያንዳንዱን በእያይነቱ ማግኘት ቀላል ነው ። ይኸው እኛም ይህንን ተከትለን ያላቅማችን ዳንኤል ክብረት እይታወች ብሎ አሳየን እይታ ዕያልን እንከተላለን አይቀርበት ይኸው እንጽፋለን እድሜ  ለኮፒይ ፔስት ቴክኖሎጅይ መጻፍ ባንችል እንገለብጣለን ።
ስሙ ሰሞኑን እንዴት እንዳለፈ እኔ ነው የማቀው  . . . ቀድመን ስንጠረጥራት የነበረች ድራማ ይኸው እውን እየሆነች እንደሆነ ተመለከትናት /እንዴት ነው ሰውለሰው እንበላት ወይስ ፓትርያርክ ለመንግስት/  ። አባት የተባሉትም ምን እንደነካቸው አላቅም ይመስለኛል ቤተክህነቱም እንደ ቤተመንግስቱ የ ቀድሞ መሪውን /የአቡነ ጳውሎስን/ ራዕይ ለማሳካት እየጣረ ይመስላል።    እንዴት ነው ይህ ነገር የራሷ  ራዕይ የሌላት ሀገር፤ የራሷ ራዕይ የሌለት ቤተ መንግስት፤ አሁን ደግሞ የራሷ ራእይ የሌላት ቤተ ክህነት ልንፈጥር ይመስላል እንዴት ነው ራዕይ የሌለው ትውልድ መረን ይሆናል እያላችሁን ? ለሁሉም መጠርጠር መልካም ነው ብየ ነው እንጂ የፓትርያርካችንን  ራእይ ለማሳካት ብላችሁ በግልጽ አልነገራችሁንም ነገሩ ሰውን እኮ ተግባሩ ነው የሚገልጠው አይደል እንዴ ? ግራ ገባን ኮ ምን እንበል ብላችሁ ነው ? ግን በእውነት ድራማዋ አፈጣጠኗም ሂደቷም ትመቻለች
 ምርጫውም ደግሞ በካርድ ነው አሉ እንዴት ነው ታዛቢስ ከውጭ አይመጣም እንዴ ? የምረጡኝ ቅስቀሳም እኮ ሳያስፈልገው አይቀርም በዚህ ዐይነት ?  ይቅርታ ይቅርታ ነገሩ ተመራጩ በታወቀበት ምርጫ ላይ ለካ ይህ አያስፈልግም ።ነገሩ መዘዙ ነው የሚብሰን ደግሞምኮ ይሁን ቢባል  ባበው ጨነቀኝ እንተወው . . .  / መቸም ይህችን ምርጫ ግብጻውያኑ የ አቡነ ሺኖዳ ልጆች  ቢሰሙ ፍርፍር ብለው ነበር የሚስቁብን/። እውነት እውነት የዚህች እቅድ አቃጅ ግን እውነተኛ ቃሉን ጠባቂ ነው የመሪውን ራዕይ የሚከተል የሚያሳካ።  ከ ቤመንግስቱ ባለራዕዮች ከሆነ ያው መቸስ የአገሪቱን  አብዛኘውን ቁጥር የያዘ እምነት መሪን በቁጥጥር ስር ማድረግ የትራንስፎርሜሽኑን እቅድ ለማካት ዋናና ዋና ተግባር መሆኑ የማይጠረጠር ነው ስለዚህ የመሪውን ራእይ ለማሳካት ይህንን ማከናወን የግድ ነው ። ከቤተክህነቱም ከሆነ ደግሞ ያው በጥቂት አመታት ውስጥ ቤተክርስትያኗን የተሃድሶወች መሮጫ ለማድረግ ለታቀደው የተሃድሷውያን የትራንስፎርሜሽን እቅድ መፈጸም ዋናውን መቆጣጠር የማይጠረጠር አስፈላጊ ነው ። ለሁሉም ከሁለቱም ቢሆን የሚደነቅ ቃል ጠባቂነት ነው ? አንዳንዴ ትክክል የሆነ ብቻን ሳይሆን ሁሉንም ማድነቅ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም …. ነገር ግን ይህ ሃይማኖት ነው ቀልድ አይደለም ይመስላል እንጂ መጨረሻው እንደ አቃጆቹ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው ። መቸም ለመልካም ነገር ለመንፈስ ቅዱስ ስራ የምርጫ ካርድ መፍትሔ እንዳልሆነ  መነገር የሚያስፈልገው አይደለም  
ደግሞ መቸነው ከእንቅልፌ ብድግ ስል ስለ ግብጹ የሙስሊም ብራዘር ሁድና ማህበረ ቅዱሳን የተጻፈ ጽሁፍ ፌስ ቡክ አካውንቴ ላይ ተለቆ አገኘሁት ። ይህ ነገር እንዴ ነው ? ጹሁፉ ከ ሰማይ ቤት ነው ?  ብየ አሰብኩ ያለፈው የፓርላማ አስቂኝ ንግግር ትዝ ቢለኝ /ድንገት ዳግም ትዝብሏቸው በመንፈሳቸው በኩል ተናግረውት ከሆነ ብየ ነው/  ምን አልባት ደግሞ  ራእያቸውን ለማሳካት የሚታገሉት ትጉ አገልጋዮች ለክ እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋብተውት ከሆነስ ??? እኔ እንጃ ብቻ እያሰብኩ ማፈንጠርያውን /link/ ከፈትኩት  ከፍቸ ሳየው ለካ እነእንቶኔ  ናቸው እነርሱ እንኳ ግራ የገባቸው በኦርቶዶከስ ማሊያ ለነ ማርቲን ሉተር የሚጫወቱት  እሰይ አወቃችኋቸው ? ከዚያውላችሁ እኔም ተረጋጋሁ ። “እሰይ ኤፍሬም እሸቴ አረፈ” አልኩ ደግሞ ዳግም እርሱ የጠቅላይ ሚንስትሩ መንፈስ  ባለው አልስማማም ብሎ ከመጻፍ ስንት ነገር የሚሰራበትን ሰዓቱን ከማባከን ተረፈ።  / ለነዚህ የጥቃቅን ጥቃቅኖች  እኛ ጥቃቅኖች እንበቃለን ብየ ነው / ።
አይ አውደምህረቶች ሃራ ዘተዋህዶ ወ አባስላማ  የእናንተን ብሎግ ለማንበብ እኮ በራሱ መንፈሳዊ መሆን ያስፈልጋል ። እኔ እናንተን ብሆን ምን ብየ እንደምጀምር ታቃላችሁ “ ለ ኦርቶዶክሳውያን የተከለከለ …” ነገሩ ቀለል አደረኩት ይህ ይሻላል “ ኦርቶዶክሳውያን ከማያነቡበት ቦታ ብቻ ይከፈት።” አንዲህ ነው የሚስማማው። ነገሩ አሁን በዚህች ተጽፋችሁም ደስእያላቸሁ ይሆናል እኮ ግን ደግሜ ልጠይቃችሁ አላማችሁ ምንድን ነው ? ብላችሁ ብላችሁ  እናንተም ማህበሩን አሸባሪ አረጋችሁት  ኸረ ተው  የአንዱ ይበቃል ። / ዕየለመንኳችሁ አይደለም ደስ እንዳያላችሁ ቢገባችሁ ብየ ነው/  ።ነው ወይስ የጠላቴ ጠላት ወዳጀ ነው ብላችሁ ነው ?  ነገሩ ጉርብትናችሁንማ እያሳያችሁን እኮ ነው / ኢትዬጵያ ጨለመባት ለድርድር የቀረበች ቦነሳችሁ ናት እንዴ ?/ አንድ ነገር ልንገራችሁ ከዚያ በፊት ግን መጀመርያ  እኔ  የደ/ቅ/አብነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አባ እንጂ የማህበሩ አባል እንዳልሆንኩ እወቁ / ነገር ግን አንድ ዓላማ  ያለን የ ቤክርስትያን ልጆች ለማመዛዘን እነዲረዳችሁ ብቻ /  እናንተ እኮ የማህበሩ አንድ አባል ሲናገር ትዝ የሚላችሁ አጠቃላይ ማህበሩ ነው ብየ ነው . . .  ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ ተናገረ ብላችሁ አይደል እንዲህ ያስቀባጠራችሁ  ። ሲቀጥል  ግን  ማርያምን . . . ወደዳችሁም ጠላችሁም አሁን ከሲኖዶሱ በላይ ለቤተክርስትያን የሚያስፈልጋትም እየጠቀመም ያለ የቤተክርስትያኒቷም ምሰሶ ማህበረ ቅዱሳን ነው ስለ ተንጰረጰራቸሁ የትም አትደርሱም ያው ከግድግዳ ጋር መጋጨት እኮ ውጤቱ እብጠትና ወደኋላ መውደቅ ነው።  
ቆይ ቆይ ምነው ማህበሩ ሲነሳ አይናችሁ ይቀላልሳ ? ነገሩ አልፈርድባችሁም ምን ታደርጉ ከላይ በአንዴ ወደ እንጥሮጦስ መውረድ ችግሩ እኮ ይህ ነው ።ፍልስልሳችሁ ወጣ ተበታተናችሁ ድሮስ ስለ ጥቅሙ ብቻ የተጠራቀመ ለቤተክርስትያን ሊሆን ? ለራሳችሁ እንኳ ከሆናችሁም ይደንቃል / የሰላሜ ሰው ያልኩት እንጀራየን የበላ …/ እያላችሁ የዘፈናችሁለትስ ለማን ይሆን ልቦናው ለተመለሰው ወይስ ለካደው ? ይኸው አለቃችሁ የማይፈነዳውን ያፈንዳችሁ እያለ ራሳችሁ  ፈንድታችሁ ቁጭ አላቸሁ ? ጋዜጣችሁ የቡና መጠቅለያ ነው የሆነው ሲል የነበረው ዛሬ የ ጋዜጣው ስርጭት ሲጨምር እርሱ የትገባ ? የት ተጠቀለለ ?  አቤቱ ባለግርማ ሞገሱ ወዴት አለህ ? አቤቱ አንተብቻ አዋቂው የት አለህ ? አቤቱ አንተ ካልኖርክ የሚበተን የሚመስልህ ህዝብ አንተን አጥቶ ስላሙን አግንቷልና  ድምጽህን አጥፋ ብቅም አትበልብን ? ሥላሤ እያለ የኖረውን ህዝብ አትበል ያልከው ወዳጄ ሆይ የት ነህ ? የማይደፈረውን ደፍረህ የማታውቀውን ቀላቅለህ የማይናቀውን ንቀህ የት ገባህ  ? አቤቱ ወዳጀ ሆይ የንስሀ ጊዜህን መጠቀም አቅቶህ ወደኋላ ስትጎተት ባየውህ ጊዜ አዘንኩ ውድቀትህን አላምን ብለህ ሰውን ይዘህ ለመውደቅ ስትታገል ባየውህ ጊዜ ማንነትህን በርግጥም ተረዳሁት ወዳጅሆይ  እንደይሁዳ ጠፍተህ ከመቅረጥህ በፊት ንስሐ ግባ ካልሆነም ማስመሰያ ማሊያህን አውልቀህ ተላቀቀን ።
አሁንስ እናንተም አቃታችሁ መሰል ።  አምላክንም አብዝቶ ዝም አለ እያላችሁት ነው ወላዲተ አምላክን …አርሱ ምንም አብዝቶ  ዝም አላለም አርሱም ምንም አብዝቶ ዝም ያለበት ነገር የለም  እያሳያችሁ እኮ ነው በቤቱ ተመሳስሎ መኖር የለም በቤቴ መኖር የሚችለው የእኔ የሆነ ብቻ ነው አለሽ እኮ የእርሱ ስላልሆንሽ በጅራፉ ገርፎ  ሲያስወታጣሽ ዝም አለ  ዝምታ ነገር አለው እያልሽ ህዝቡን የምትሸውጅ መስሎሽ ራስሽን አትሸውጅ ይልቅስ ምን እያለኝ ነው ብለሽ ራስሽን ጠይቂ ምን እያለሽ እንደሆነ ስሚው ንስሃም ግቢ በትችይ ሰውን ታድኝበታለሽ ካልሆነም ረስሽን ታድኝበታለሽ ።
ለሁሉም  አሁን እኮ ቦታችሁን እየያዛችሁ ነው ብዙ አትንጠልጠሉ ተረጋጉ ብሎጎቻችሁም ይረጋጉ ዓላማቸውን ይለዩ ዝም ብሎ ያለ ዓላማ የሚከወን ስራ ትርፉ እንደ ነፋስ ወዲያ ወዲህ መንሳፈፍ ብቻ ነው ።  . . . . . እኔ እኮ ልጨርስ እፈልግና ውስጤ እንቢ ይለኛል ለካ ረስቸው ነው ። “ እንቁራሪት ዝሆን አከልኩ ብላ ፈንድታ ሞተች ። ” አሉ ደግሞ ዳንኤል ክብረትንም መነነካት ዳግም ቀጠላችሁ ለዛሬ ሰለእርሱ አንድ ነገር ብቻ ልበላችሁ  የቤተክርስትያን አገልጋዮችን አካሄድ ወደአንድ እርምጃ ያሻገረ የቤተክርስትያን የቁርጥና የቁርጥ ቀን እና ሊተካ የማይችል ምርጥ ታላቅ ሰው ።  በእውነት ሊኖርበት የሚገባ ራእይ ያለው  /በእውነት አድሜ ይስጥልን እንጂ አትጠራጠሩ ራዕዩን ለማሳካት ቃል እምገባ አንደኛ እኔ ነኝ/   እውነተኛ ባለራእይ ሰው ።   ለሁሉም ይህንን በክፍል ሁለት እመለስበታለሁ ስለእርሱ ተናግሬ እንዲህ ባጭር ስለማልጨርስ 
ሳጠቃልል አንድ መልእክት ብቻ ላስተላልፍ  ማህበሩን  ለቤረክርስትያናችን እየሰራው ስላለው ስራ አገልግሎት እንወደዋለን ፤እናከብረዋለን ፤እንጠብቀዋልን  ዓላማውን ለማሳካትም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን መሆን ያለብንን ሁሉ እንሆናለን አትድከሙ ማህበሩ ከ ግብጹ የሙስሊመም ብራዘር ሁድ ጋር የሚያመሳስለው ዓላማም ግብርም የለውም  ታቃላችሁም የምትሉበት ዓላማ ተረድተነዋል አትድከሙ  . . . .።
                   ይቆየን 
                    ባህርዳር ኢትዮጵያ
 
 

11 comments:

  1. also in www.hulubanteabebe.org i read it . . . . .

    ReplyDelete
  2. አይ አውደምህረቶች ሃራ ዘተዋህዶ ወ አባስላማ የእናንተን ብሎግ ለማንበብ እኮ በራሱ መንፈሳዊ መሆን ያስፈልጋል ። እኔ እናንተን ብሆን ምን ብየ እንደምጀምር ታቃላችሁ “ ለ ኦርቶዶክሳውያን የተከለከለ …” ነገሩ ቀለል አደረኩት ይህ ይሻላል “ ኦርቶዶክሳውያን ከማያነቡበት ቦታ ብቻ ይከፈት።” አንዲህ ነው የሚስማማው።
    "ዳንኤል ክብረት የቤተክርስትያን አገልጋዮችን አካሄድ ወደአንድ እርምጃ ያሻገረ የቤተክርስትያን የቁርጥና የቁርጥ ቀን እና ሊተካ የማይችል ምርጥ ታላቅ ሰው ። በእውነት ሊኖርበት የሚገባ ራእይ ያለው /በእውነት አድሜ ይስጥልን እንጂ አትጠራጠሩ ራዕዩን ለማሳካት ቃል እምገባ አንደኛ እኔ ነኝ/ እውነተኛ ባለራእይ ሰው ።"

    ReplyDelete
  3. ማህበሩን ለቤረክርስትያናችን እየሰራው ስላለው ስራ አገልግሎት እንወደዋለን ፤እናከብረዋለን ፤እንጠብቀዋልን ዓላማውን ለማሳካትም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን መሆን ያለብንን ሁሉ እንሆናለን አትድከሙ ማህበሩ ከ ግብጹ የሙስሊመም ብራዘር ሁድ ጋር የሚያመሳስለው ዓላማም ግብርም የለውም ታቃላችሁም የምትሉበት ዓላማ ተረድተነዋል አትድከሙ . . . .።

    ReplyDelete
  4. I don't think this article is constructive. When you have the truth you are the Champion. Insulting others mean helping. Just be good ,keep yours and let reader to judge all the rest.

    ReplyDelete
  5. please,Hara zetewahido is not menafikan blog!

    ReplyDelete
  6. I agree with all what you wrote. But please do not rush to defend individuals like Dn Daniel Kibret. It is not good for two reasons: first it will be wudase kentu for him. Second, u can not know every thing about him and he has his own problem at this moment. So, please hold on for the time being.

    Andu

    ReplyDelete
  7. Egziabher Yabertachu!

    ReplyDelete
  8. የ ህንድ ቤተ ክርስቲያን ላይ የ ደረሰውን ጥፋት አዚህ ለ መድገም አንደሚሞክሩ አንውቃለን........ማህበረቅዱሳን ደግሞ የሚጠሉት አንደልብ ኣላንቀሳቅስ ስላላቸው ነው፤ማህበረ ቅዱሳን የ ቤተ ክርስቲያን መከታ ነው....
    ያሬድ ዘ መንበረጸባኦት

    ReplyDelete
  9. አሁንስ እናንተም አቃታችሁ መሰል ። አምላክንም አብዝቶ ዝም አለ እያላችሁት ነው ወላዲተ አምላክን …አርሱ ምንም አብዝቶ ዝም አላለም አርሱም ምንም አብዝቶ ዝም ያለበት ነገር የለም እያሳያችሁ እኮ ነው በቤቱ ተመሳስሎ መኖር የለም በቤቴ መኖር የሚችለው የእኔ የሆነ ብቻ ነው አለሽ እኮ የእርሱ ስላልሆንሽ በጅራፉ ገርፎ ሲያስወታጣሽ ዝም አለ ዝምታ ነገር አለው እያልሽ ህዝቡን የምትሸውጅ መስሎሽ ራስሽን አትሸውጅ ይልቅስ ምን እያለኝ ነው ብለሽ ራስሽን ጠይቂ ምን እያለሽ እንደሆነ ስሚው ንስሃም ግቢ በትችይ ሰውን ታድኝበታለሽ ካልሆነም ረስሽን ታድኝበታለሽ ።

    ReplyDelete
  10. Hello to every one, because I am truly eager
    of reading this website's post to be updated on a regular basis.
    It includes good material.

    Review my weblog: Louis Vuitton Outlet

    ReplyDelete