ደቂቀ ናቡቴ

Saturday, December 22, 2012

መንግስት በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ በይፋ ጣልቃ ገባ

ዋና ዋና ጉዳዮች:-
  • አስመራጭ ኮሚቴው እስከ ጥር 18 ድረስ እጩዎችን እንዲያቀርብ ሲኖዶሱ አዟል፡፡
  • የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ቅ/ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴ ከመሠየም እንዲታገሥ ጠየቁ::
  • የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ አራተኛው ፓትርያሪክ ስለሚመለሱት ኹኔታ ምልአተ ጉባኤው እንዲመክር ጠይቀዋል:: 
  • የልኡካኑ አብሮ መቀደስ በአንዳንድ አባቶች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል ተብሏል
  • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ መንግሥት የፓትርያሪክ ምርጫውን የሚከታተል ባለሥልጣን መመደቡ በግልጽ ተቃውመውታል::
  • የአስመራጭ ኮሚቴውን መቋቋም የተቃወሙ አባቶች በከባድ ጫና ሥር ወድቀዋል::
  • አቡነ ማቴዎስ ከሲኖዶሱ ራሳቸውን አግልለዋል
  • የአስመራጭ የኮሚቴው አባል አቡነ ቄርሎስ ‹‹አልሠራም፤ አላምንበትም›› በሚል ራሳቸውን አግልለዋል::
  • የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል ‹‹መግለጫ አልሰጥም›› በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል:: 
 መንግሥት ‹‹ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ›› በሚል ከፍተኛ ባለሥልጣኑን የመደበው ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ ባለሥልጣኑ አቶ ትእዛዙ ደሳለኝ የሚባሉ ሲኾኑ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ይኹንና አቶ ትእዛዙ በዛሬው የመንበረ ፓትርያሪክ ውሏቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ለማግባባት ያደረጉት ጥረት የሠመረላቸው አይመስልም፤ ‹‹ዕርቀ ሰላሙ በምርጫው ሂደት አይሰናከልም፤ ወደፊትም ሊካሄድ የሚችል ነው፤›› ቢሉም የሰማቸው ባለመኖሩ ይህንኑ ለበላይ አካል አስታውቀዋል ተብሏል፡፡ የእርሳቸውን ሪፖርት ተከትሎ ከእርሳቸው ከፍ ያሉ ባለሥልጣን በአቋማቸው የጸኑትን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬውኑ ማምሻውን ወይ ባሉበት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አልያም ወደ ውጭ አስጠርቶ የማወያየት፣ የማስፈራራት፣ የማስጠንቀቅ አካሄድ ሳይኖር እንደማይቀር ተገምቷል፡፡ ከዚህ በባሰ የመንግስት ጣልቃ ገብነት የለም፡፡ ምናልባትም በእስልምናው የታየው ሁኔታ በኦርቶዶክሱም ይከሰታል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ይሆነል፡፡
መንግስት በእኛ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!!!!!!!!  መልእክታችን ነው፡፡

ከኅዳር 26 – 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ የተሳተፈውና ከአራት ቀናት በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ የተገለጸው የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡካን ቡድን አባላት÷ በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ በመወያየት ላይ የሚገኘው ምልአተ ጉባኤ ሕጉን ከማጽደቅና አስመራጭ ኮሚቴ ከመሠየም እንዲታገሥ መጠየቁ ተሰማ፡፡ የልኡካን ቡድኑ ከዕርቀ ሰላሙ ንግግር በኋላ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ከሊቀ ጳጳሱ አቡነ ፋኑኤል ጋራ ለተፈጠሩት አስተዳደራዊ ችግሮች መፍትሔ ለማበጀትና ሊቀ ጳጳሱ በሀ/ስብከቱ ጸሐፊ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት እንዲያነሡ በመሥራት ላይ መኾኑ ተዘግቧል፡፡
ብፁዕ አቡነ ገሪማን (በሰብሳቢነት)፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስንና ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን በልኡካን ቡድኑ አባልነትና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን በጸሐፊነት የያዘው የልኡካን ቡድኑ÷ ለቅዱስ ሲኖዶሱ በጻፈውና በስብሰባው ላይ በንባብ በተሰማው ባለሁለት ገጽ ደብዳቤው÷ አራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱበት ኹኔታ በስደት በሚገኙት አባቶች የተሰጡትን ምክንያቶች መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ምልአተ ጉባኤው የሚያካሂደው ምክክር አስፈላጊ መኾኑን አመልክቷል፡፡
ደብዳቤው አያይዞም÷ የዕርቀ ሰላሙ ቀጣይ ንግግር ከጥር 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም በካሊፎርኒያ – ሎሳንጀለስ እንደሚካሄድ መወሰኑን፣ ሂደቱ ከመልካም ፍጻሜ እንዲደርስ ሁሉም ወገን ለሰላሙ መሰናክል የኾኑ ማናቸውንም ሥራዎች ከመሥራት ትዕግሥት እንዲያደርግ ስምምነት ላይ መደረሱን ለዚህም መፈረማቸውን፣ የሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ወደ ሁለቱም ወገኖች ተጉዞ የማግባባት ሥራ እንዲሠራ የሚጠበቅ መኾኑን በማስታወስ፣ ምልአተ ጉባኤው እኒህን የሚያደናቅፉ ውሳኔዎች ከማሳለፍ እንዲታገሥ ተማፅኗል፡፡
በደብዳቤው ላይ ከምልአተ ጉባኤው አባላት የተለያዩ ሐሳቦች ተደምጠዋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ ሦስት አባላት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንደመኾናቸው በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ተገኝተው በሕጉ ረቂቅ ይኹን በአስመራጭ ኮሚቴው አባላት አደረጃጀት ላይ ሐሳብ የመስጠት መብታቸው እንዲጠበቅ የተናገሩ ብፁዓን አባቶች÷ የዕርቅና ሰላም ቀን እንደማይመሽ በማጠየቅ የልኡካኑን ደብዳቤ ሐሳብ ደግፈዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የልኡካን ቡድኑ አባላት በውግዘት ከተለያዩ አባቶች ጋራ አብረው ስለመቀደሳቸውና ስለመጸለያቸው (በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል) ትኩረት በመስጠት፣ የመጨረሻ ነው በተባለ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ‹‹ቀን ቀጥረው ለመምጣትም ሥልጣኑ አልነበራቸውም›› በሚል የልኡካን ቡድኑን በአቋም ለመቃወም መዘጋጀታቸው ተገልጧል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብሳቢዎች ከኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል 32 አባቶች ብቻ በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ÷ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ 16 ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አለመሳተፋቸው ታውቋል፡፡ ከሕመም ጋራ በተያያዘ በስብሰባው ለመሳተፍ አልቻሉም የተባሉትን ብፁዓን አባቶች ትተን በተለይም በሀገር ውስጥ እያሉ በምልአተ ጉባኤው ላይ ያልተገኙት አባቶች (እንደ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ)÷ ዕርቀ ሰላሙን ከማስቀደም አንጻር ባላቸው አቋም ከስብሰባው መታጎላቸው ‹‹ከምርጫው ይልቅ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖችንትኩረት ስቧል፡፡

ለዕርቀ ሰላሙ ብዙዎች ያሳደሩት ተስፋ ለምልሞ ከመልካም ፍጻሜ የሚደርስ ከኾነ ለሳምንት ያህል የተደከመበት የምርጫ ሕግ ማጽደቅና የአስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም ድካምና ውሳኔን ጥቅም አልባ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡ ‹‹ከምርጫው ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖች አራተኛው ፓትርያሪክ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ በሚለው አቋም ላይ ጥንቃቄ በማድረግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እስካሉ ድረስ መንበሩ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ወይም በእንደራሴ እንዲመራ ይሟገታሉ፡፡
ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ÷ ‹‹የላክናቸው ሳይመለሱ  በመልእክቱ (በላክንበት ጉዳይ ላይ) ውሳኔ አናሳልፍ›› እያሉ ቢሟገቱም ተንኮል በተሞላበት ስሌት የአስመራጭ ኮሚቴው አባል ተደርገው መመረጣቸው አስገራሚ ነበር፡፡ በዛሬው ዕለት እኚህ አንጋፋ ብፁዕ አባት÷ ‹‹በሂደቱ አላምንበትም፤ በኮሚቴውም አልሠራም›› በማለት ግልጽ አቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡ የኮሚቴው መቋቋም ውሳኔ በተላለፈበት የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ፣ ‹‹የልዩነት ሐሳቤ በቃለ ጉባኤ ይስፈር›› ያሉት ብፁዕነታቸው የኮሚቴው አባል ኾነው የተመረጡበትን ደብዳቤም ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልኾኑና እንዳልተቀበሉም ተዘግቧል፡፡ 
የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል  ቅዱስ ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴ በማቋቋም ያስተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ለብዙኀን መገናኛ መግለጫ እንዲሰጡ የተላለፈላቸውን ትእዛዝ አልቀበልም ብለዋል፡፡ መንግሥት በይፋ በመደበው አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ጭምር ቢታዘዙም፣ ከማዘዝም አልፎ ቢያስፈራሯቸውም ብፁዕነታቸው÷ ‹‹ምልአተ ጉባኤው ተሰብስቦ መግለጫ ስጥ ሲለኝ እንጂ አንተ ስላልኸኝ አልሰጥም›› በማለት የጽናታቸውን ልክና ዳርቻ አሳይተዋል፡፡
በሲኖዶሱ እየታየ ያለው ውጥረት ተባብሶ የቀጠለ  ሲሆን አቡነ ማቴዎስም ከሲኖዶሱ እራሳቸውን ማግለላቸው እየተነገረ ነው:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ከየአቅጣጫው ያሉ ምዕመናን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመቃወም የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ የእኔም ጉዳይ ነው በሚል በከፍተኛ ንቅናቄ ለመንቀሳቀስ እየተነሳ ሲሆን አባቶች ጉዳዩን በማጤን ዕርቀ ሰላሙን የሚያሰቀድሙበትን ሁኔታ እንዲፈጠር መንገድ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል ፡፡

እግዚአብሔር አንድነታችንን ያጠንክርልን፡፡ 

 

15 comments:

  1. የአቡነ ቄርሎስ ጀግንነት ተስፋ በአባቶቻችን ተስፋ እንዳንቆርጥ እኮ ነው:: እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን እድሜ ቀንሶ ለሳቸው በሰጠልንና ጤናቸውን በሰጠልን እያልኩ አስባለሁ እርሱ ግን የኛንም ሳይቀንስ ለሳቸው ከሙሉ ጤንነታቸው ሊሰጥልን ይችላል::

    ReplyDelete
  2. Yemnegest Taleka gebenet ekawemalehu. Behege menegestu Yetesafewe teresa endey?

    ReplyDelete
  3. mengest megebat alebet,mekneyatum bezu halafinet yemaysemachewe sewoch selalu.............ke zer astesaseb yaltelakeku, ke 21we keflzemen yetetalu bezu hewalaker sewoch selalu.........i support what the government is doing because he is responsible.

    ReplyDelete
    Replies
    1. sorry this is not what we expect from an orthodox christian. we stand with only gods will we need no any government interference. we are GOD"s and will be only his subject for ever. midrawi nigus ayashanem!

      Delete
  4. Please change the back ground of the board to white because I can't able to read.

    ReplyDelete
  5. Talka Gebinetun ekawomalehu! Man leman talka yigebal. Bete christian lerasua yerasuan guday ticheris.

    ReplyDelete
  6. አረ ነገሩ እንደዚህ ተካሯል እንዴ. እኔ በበኩሌ፣ ለሁሉም ነገር ባንቸኩል እላለሁ፡፡

    ReplyDelete
  7. we children of God shall pray to God because we are highly supported only by him.A handful of faithful children of God are struggling with the selfish guys.
    Everyone is marching towards power and money.God is looking at all of us.we will see what will happen in near future.Becareful,God has seen our acts.He will do His part soon. May God bless us to do our part.

    ReplyDelete
  8. I dont know why we are rushing to criticize the govenment while some of our church members( abatoch) are becoming the main opponent for the peace process. Ofcourse the government is trying to do what it used to but I dont see from many blogs criticizing those abatoch who works against the will of our church...let the church followers know who they are so that they wiil be held accountable for all the damge to our church if this peace process falls coz of them... May God help our church and its followers. Amen

    ReplyDelete
  9. መረጃውን በየአለንበት ሁሉ እንዲድረ በእግዚአብሔር ፈቃድ ለምትጥሩ ሁሉ እግዚአብሔር ብርታትና ጽናት ሰጥቶ ፍጻሜያችሁ ያሳምረው እያልክ ሁሌ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር፤ እንዴት ነው አንድ የመንግስት ባለስልጣን የሐዋርያት ምሳሌ የሆኑትን አባቶቻችን አስታራቂ የሚሆነው? እንዴት ነው ይቅርታንና ሰላምን በመስበክ እግዚአብሔር ይፍታህ እያሉ የሚባርኩን አባቶቻችን በአለማዊ ሰው ጣልቃ ገብነት የሚሸመገሉት? ታዲያ የት ላይ ነው አባትነቱ፣ የት ላይ ነው የሐዋሪያት ተምሳሌነቱ፣ ምናልባት እረኛው ባይፈቅዳቸውም ቤታችውን ፈልገው እንደሚመጡ እንስሳት እኛ ምዕመኖችም እንሆን ይሆን?
    እግዚአብሔር በቱን ይጠብቅ።

    ReplyDelete
  10. የአቡነ ቄርሎስ ጀግንነት ተስፋ በአባቶቻችን ተስፋ እንዳንቆርጥ እኮ ነው:: እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን እድሜ ቀንሶ ለሳቸው በሰጠልንና ጤናቸውን በሰጠልን እያልኩ አስባለሁ እርሱ ግን የኛንም ሳይቀንስ ለሳቸው ከሙሉ ጤንነታቸው ሊሰጥልን ይችላል::

    ReplyDelete
  11. Loѕ Secгetos ԁel tantra Con la ρг?
    Τhe Nokіa E7 iѕ the lаtеst tгacκ to fly the Richard Mille colouгs for thiѕ unmіssablе motorsportѕ event.



    Ϲhеck out my web-site - massages

    ReplyDelete
  12. This is the perfect site for anybody who would like
    to understand this topic. You understand so much its almost hard to argue
    with you (not that I personally would want to…HaHa). You
    certainly put a brand new spin on a subject that has
    been discussed for years. Excellent stuff, just great!


    Feel free to visit my web page; http://my-maleedge-Review.blogspot.com

    ReplyDelete
  13. Hey this is kind of of off topic but I was wondering if blogs use WYSIWYG
    editors or if you have to manually code with HTML. I'm starting a blog soon but have
    no coding expertise so I wanted to get advice from someone with experience.
    Any help would be greatly appreciated!

    Check out my web page - Dr Dre Beats

    ReplyDelete
  14. Hey there fantastic blog! Does running a blog
    similar to this take a lot of work? I have very little
    knowledge of computer programming but I had been hoping to start my own blog soon. Anyway,
    if you have any recommendations or techniques for new blog owners please share.
    I understand this is off topic however I just had
    to ask. Many thanks!

    Also visit my blog Louboutin Shoes

    ReplyDelete