ደቂቀ ናቡቴ

Wednesday, September 26, 2012

“አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረን፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፋችንን ደምስስ። ከበደላችንም ፈጽሞ እጠበን፥ ከኃጢአታችንንም አንጻን፤ እኛ መተላለፋችንን አናውቃለንና፥ ኃጢአታችንም ሁልጊዜ በፊታችን ነውና። አንተን ብቻ በደልን፥ በፊትህም ክፋትን አደረግን፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።” መዝ.50/51፡1-4'


ፀሎተ ምህላ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
“አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረን፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፋችንን ደምስስ። ከበደላችንም ፈጽሞ እጠበን፥ ከኃጢአታችንንም አንጻን፤ እኛ መተላለፋችንን አናውቃለንና፥ ኃጢአታችንም ሁልጊዜ በፊታችን ነውና። አንተን ብቻ በደልን፥ በፊትህም ክፋትን አደረግን፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።” መዝ.50/51፡1-4

♥♥♥የይቅርታ አምልክ አቤቱ ማረን የቸርነት አምላክ አቤቱ ይቅር በለን፤ ልጅህን ልከህ ያዳንከን አቤቱ ተመልከተን ጨለማ ሕይወታችንን ወደ ብርሃን የለወጥክ  አቤቱ ታደገን።
♥♥♥በዚህ ክፉ ዘመን የገጠመንን መከራና ችግር ታርቅልን ዘንድ በአማኑኤል ስምህ በድንግል እናትህ እንለምንሃለን።
♥♥♥† በጨለማ ለነበሩት አህዛብ እንደ ነጋሪት ጮኸውመወለድህንና መምጣትህን ስላስተማሩ ነብያትህ ብለህ ከመዓት ሰውረን።
♥♥♥† የአህዛብን ምድር በመስቅልህ እርፍ አርሰው የቃልህን መዝገብ በዓለም ዳርቻ ሁሉ ስለ ዘሩ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ብለህ ከክፉ መከራ አድነን።
♥♥♥† ድል ስለነሱ፣ አምነው ንጹህ ስለሆኑ ስለ ሰማዕታት ተኩላዎች ስለበሏቸው ስለመንጋህ ብለህ ይቅር በለን።
 ♥♥♥† የጽድቃቸውን ዋጋ ትሰጣቸው ዘንድ በንጽህና ሹመታቸውን ስላበረከቱ ፍጻሜያቸውንም ስለተቀበልከው ስለአባቶቻችን ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ስለወንድሞቻችን ዲያቆናት፣ ደናግልና መነኮሳት ብለህ ይቅር በለን።
♥♥♥† ይህንን አላፊ ዓለም ጠልተው በሰማይ ያለውን ሰርግና ክቡር የማያልፈውንም ተድላ ስለወደዱና ዓለምን ስለናቁ ልጆችህ ስትል ይቅር በለን።
♥♥♥† የሁላችን እምቤት የእምነታችን ምልክት የመዳናችን ምክንያት እውነተኛ መብልን የሰጠችን መሶበ ወርቅ የሕይወት ውሃን ያጣፈጠችልን ንጹህ ማሰሮ በሆነች በድንግል ማርያም ስም ብለህ ይቅር በለን።
♥♥♥† ጌታ ሆይ ስለማያልቀው ቸርነትህ ስትል ምህረትህን አድርግልን። በዚህ ቦታ በዚህም የምህላና በዚህም ሥፍራ በሀገራችንና በዓለም ሁሉ ምህረትህንና ቸርነትህን አድርግልን።
♥♥♥† ቸር አምላክ ሆይ የደከሙት ይዳኑ፣ ኸጥአን ይጽደቁ፣ ንሰሐ የገቡት ይንጹ፣ ፃስቃንም ይጠበቁ  የተቸገሩት ይፈቱ፣ የተጠጨነቁት ይረፉ፣ ተክዘው የነበሩ ሁሉ መጸናናትን ያግኙ፣ ያዘኑትም ባንተ ደስ ይበላቸው፤ ተስፋ የቆረጡት ተስፋቸው ይመለስ። በአስከፊ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በምህረት ዓይንህን ይጎብኙ።
♥♥♥† ጌታ ሆይ እየሰተሰማ እየታየ እየተፈራና እየተጠበቀ ካለው ክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን፤ ሕዝቦችህን ጎብኝ።  
   
  ♥♥♥† በቸነፈር፣ በዋግ፣ በአንበጣ በአረማሞ፣ በተምችና በኩብኩባ፣ በወባ ንዳድ በኤድስና በረሃብ ከመሞት ሰውረን።
♥♥♥† ቸር አምላክ ሆይ በእስር ቤት ያለ ፍርድ  የሚማቅቁትን ፍትህ በማጣት በገዥዎች ቀንበር ሥር ወድቀው የሚሰቃዩትን ሁሉ ተመልክተህ ነፃ አውጣ።
♥♥♥† ምድራችንን እያናወጠ ካለው የዲያብሎስ አሰራር፤ እርሱም ዘረኝነት፣ ደም እፍሳሽነት፣ ሽብርተኝነት፣ መናፍቅነት ታደገን። በመከራችን ጊዜ ካንተ በቀር የሚረዳን፤ በሀዘናችንና በችግራችን ጊዜ የሚታደገን የለምና ይቅር በለን። በአንድ ልጅህ በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከነርሱም ጋር ትክክል በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
   
የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment