ደቂቀ ናቡቴ

Thursday, September 27, 2012

በዋልድባ አምላከ ቅዱሳን ተዓምራቱን እያሳየ ነው

የገዳማውያኑ የጸሎታቸው በረከት ይደርብን
  • ቅዱስ ሩፋኤል በእለተ ቀኑ በዋልድባ ዛሬማ ወንዝ ላይ የተሰራውን ድልድይ በመብረቅ ተመቶ ጠራርጎ ወስዶታል
  • በአቲካ ወንዝ ላይ የተሰራው የሸንኮራ ማልማያ ግድብ እንዲሁ በዚሁ ቀን ፈራርሷል
  • የገዳማውያኑ እንግልት እንደቀጠለ ነው
  • ቤተክህነት በዋልድባ ገዳም ለሚፈርሱት ቤተክርስቲያኖች ካሳ ጠይቋል ይባላል (የተረጋገጠ መልስ ማግኘት አልቻልንም)
(PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ )
ባለፉት ጥቂት ሳምትታት ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ በሚሰራው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሥራውን ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ እንደነበረ ከአካባቢው በደረሱን መረጃዎች ለመገንዘብ ችለናል። እንደሚታወቀው ከጥቂት ወራት በፊት በዋልድባ ገዳም አካባቢ ሊሰራ የታሰበውን ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱን ወስዶ ሥራዎቹን ጀምሮ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን በተለያየ ጊዜ በአካባቢው በደረሰው ተአምራት ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የዲይን ኢንጂነሩ በአጋጣሚ በመሞቱ፣ ጥቂት ሰራተኞች በአውሬ በመበላታቸው፣ የግድቡ ሥራ በጣም አዳጋች በሆነ መልኩ መስራት ባለመቻላቸው (ለግድብ ሥራ ጉድጓድ ቆፍረው በነጋታው ሲመለሱ ውሃ ሞልቶት ወይንም አፈር ተንዶ በመሞላቱ) ተደጋጋሚ ክስተቶች በመፈጸማቸው የሱር ኮንስትራክሽን ኮንትራቱን አፍርሶ መውጣቱ ይታወሳል። ኮንትራት አፍርሶ መውጣት (breach of contract) በብዙ ሚሊዮን ብር ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም ሱር ኮንስትራክሽን ባለቤቶቹም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት በዓይናቸው በማየታቸው ቅጣቱን ተቀጥተው ትተው ወጥተው ነበር።
ሱር ኮንስትራክሽን ጥሎ እንደወጣ ኢ-አማናውናኑን ጣዖት አምላኪዎቹን የቻይና ኮንስትራክሽን ካምፖኒዎችን በማስመጣት ሥራዎቹን እንዲቀጥሉ ማድረግ ተችሎ ነበር፤ በመጀመሪያው አካባቢ የአካባቢው ሰው በማንኛውም የቀን ሥራ ተቀጥሮ ለመስራት ፈቃደኛ ባለመገኘቱ፣ የአካባቢውም ነዋሪዎች በገዳሙ ላይ እንዲህ አይነት ሥራዎችን ሲሰሩ ከማየት ሞታችንን እንመርጣለን በማለት ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ፍጥጫ መፈጠሩ የሚታወስ ነው፤ የመንግሥትም አካላት ምንም ዓይነት ግብግብ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር እንዲፈጠር ባለመፈለግ፣ ቢፈጠር ሊመጣ የሚችለውን የከፋ አደጋ አስቀድሞ በመገመት በወቅቱ ሥራው ትንሽ ጋብ ለማድረግ ተችሎ ነበር። የአካባቢው ገበሬ መሐበራት ሥራቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ወጥተው ስለነበር ለብዙ ጊዜ ያለሥራ መቆየት ባለመቻላቸው በመቀጠል የቻይናው ኮንስትራክሽን ሥራውን ላለፉት ጥቂት ወራት ሲሰራ ቆይቷል በዚህም በዛሬማ ወንዝ ላይ ትልቅ ድልድይ ወደ ገዳሙ ውስጥ logistics ሊያስገቡበት የሚችሉበት ድልድይ ተሰርቶ ነበር ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአቲካ ወንዝ አካባቢ መጠነኛ ግድብ ገድበው ለሸንኮራ ልማት ችግኝ ማፍያ የሚሆን ግድብ ተገድቦ ነበር በነዚህ ጥቂት ወራቶች ውስጥ ነገር ግን የፈጣሪ የአለም መድኃኒት ውጊያው ከባድ ነው ከፍጡራን ጋር ሰዎች ወይም መንግሥታት ጦርነት ገጥመው ወይንም ጎበዛዝት እርስ በርስ በጦር ገጎራዴ ሊጋጠሙ ይችላሉ በዚህም ጎበዝ የሆነው መንግሥት ወይም የጎበዝ አለቃ ያሸንፋል ተሸናፊውም መሸነፉን በጸጋ ተቀብሎ ይሄዳል። ነገር ግን የሀገራችን የኢትዮጵያ መንግሥት ወይንም የስኳር ልማት ሚኒስቴር በጉልበት ሰውን እንደሚያሸንፉ፣ በመሳሪያ ሃይል ሰውን እንደሚያስገድዱ፣ በወገናቸው ብዛት ወይም የስልጣናቸው መጠን እንደሚያሸንፉበት ሳይሆን ተግዳሮቱ ሰማይና ምድርን ከዘረጋው ከፈጣሪ ጋር መሆኑ እጅግ ከባድ ሊያደርገው እንደሚችል የተገነዘቡት አይመስለንም። በመጽሐፍ እንደተገለጸው ፈርዖን ልቡ ደንድኖ የፈጣሪን ትዕዛዝ ባለመቀበሉ 10 ተዓመራትን በግብጽ ምድር ላይ ሊታይ ችሏል ጓጉንቸር ከሰማይ ዘንቧል፣ ቅማል ምድሪቱን ወርሷታል፣ የደም ዶፍ ወርዶባቸዋል ያም አልበቃ ብሎ የግብጽን የበኩር ልጆች በመቅሰፍት ተመተዋል በመጨረሻ ግን የእግዚአብሔር ሃይል በልጦ እስራኤላውያን ወደ ተሰፋይቱ ምድር ለመሄድ በመሪያቸው በሙሴ አማካኝነት ከግብጽ 400 ዘመን ባርነት ወጥተው ነበር። ዛሬ በኛ ሀገር እንዴት እነዚህ በቅዱሳን መጽሐፍት የተጻፉ ታሪኮች እና የእግዚአብሔርን ሃያልነት የሚያስገነዝቡ ትምህርቶች ለመማር አለመቻላችን እስከ አሁን የሀገር መዋዕለ ንዋያት እና ሃብት ዝም ተብሎ ለጎርፍ እና ለመቅሰፍት መዳረጋቸው ያሳዝነናል።
ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው በጳጉሜ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ. ም. መብረቅ ቀላቅሎ የወረደው ዝና በዋልድባ ገዳም በቻይና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ላለፉት ወራት ሲገነቡ የነበሩ ግንባታዎች በሙሉ ለታሪክ እንኳን ምንም ሳይቀር በመብረቅ እና የዝናም መዓት ተመተው ድራሻቸው መጥፋታቸው ለአምላከ ቅዱሳን መድኅኒዓለም ክርስቶስ ምን ይሳንሃል ያሰኘ ክስተት ነበር፤ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ እንደተናገረው ” . . .ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን የሰጣል ይላል . . .” ስለዚህ ዛሬም እግዚአብሔር ለተገፉት፣ ለተገረፉት፣ ለተደበደቡት ገዳማውያን አባቶቻችን ሃይሉን ሰጥቷቸው በጸሎታቸው ሃይል እንሁም በአምላካችን ቸርነት በዛሬማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በመብረቅ ለወሬ እንዳይመች ሆኖ በጥፋቱ በአቲካ ወንዝ ለሸንኮራ ማፍያ የተገደበው ግድብ እንዲሁ በጎርፍ ሙላት ሙሉ ለሙሉ ከነሸንኮራ ችግኝ ማፍሊያ እና የተለያዩ ከባድ እና ቀላል machinery በአንድነት በአንድ ጀምበር ድምጥማቱ መጥፋቱ “የአምላክ ሥራ መርቀቁ” የሚያስብል ሆኖ አልፏል ከዚህም ጊዜ ጀምሮ በምንም መልኩ የቻይናው የኢ-አማናውያኑ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሊያንሰራራ ባለመቻሉ እስከ አሁኗ ቀን ድረስ ሥራው ሊጀመር አልቻለም ቢጀምሩም እንደገና ከዜሮ መጀመራቸው የማይቀር በመሆኑ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ይልቁንም አቶ አባይ ጸሐዬ በሚመሩት የሥኳር ልማት መስሪያ ቤት ውስጥ የተለያዩ ሃሳቦች እየተነሱና በዚህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችም ሃሳባቸው እየተከፋፈለ መምጣኑን ሰምተናል።
የዚህ ዝግጅት ክፍል እንደሚያምነው “ተግዳሮቱ ከፈጣሪ ጋር በመሆኑ ይቅር ባይ ነን፤ የፈርዖንን ልብ የያዘ ደግሞ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል በዓይናችን የምናየውን ማየት ከተሳነን” ምከረው ምከረው፤ አልመለስ ካለ መከራ ይምከረው የሚለውን የአባቶቻችንን አባባል እኛም ለመድገም እንገደዳለን።
ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ በዚሁ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እግዚአብሔር መዓቱን አውርዶ እነዚህ ግድብ እና ድልድይ ከፈረሱ በኃላ የአካባቢው ጸጥታ ሰዎች በገዳሙ ውስጥ በመግባት አባቶችን ማወክ እና መደብደብ ጀምረው “የእናንተ መተት ነው” በማለት ሲያውኩ አንድ ስሙ ክንፈ ገብርኤል የተባለ መናኝ “የግድቡ እና የድልድዩ አይግረማችሁ፣ ይህንን ገዳም ለማፍረስ የተነሳ ሥራው ብቻ ሳይሆን እራሱ ይፈርሳል” በማለት በሃለቃል ለታጣቂዎቹ ነግሯቸው፣ ታጣቂዎቹም በአጸፋው መናኙን ክፉኛ ደብድበውት ክፉኛ በመቁሰሉ ማይገባ በሚባል ከገዳሙ የሰባት ሰዓት መንገድ የሆነ ጤና ጣቢያ ተወስዶ በህክምና ሲረዳ መቆየቱን እና በአሁን ሰዓት በማገገም ላይ እንደሚገኝ ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።
ዋልድባ ገዳም በመድኅኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የድንጋይ ቆብ ቀርጾ ባመነኮሳቸው መነኮሳት የተገደመ ገዳም እንደመሆኑ መጠን ችግሩ ምን ቢጸና፣ ምን ያህል አባቶቻችን መነኮሳት እና እናቶቻችን መነኮሳይት ቢንገላቱ እና ቢሰደዱ፣ በገዳሙ ውስጥ የሰው ዘር እንኳ ቢጠፋ በፍጹም ልንገነዘበው የሚገባን የገዳሙ መስራች እና የቤተክርስቲያናችን ጉልላቷ ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ሊተዋት አይችልም መንግሥታት፣ ጎበዛዝት፣ ሃይለኞች ፣ በለጊዜዎች እና ባለመሣሪዎች በሙሉ ሰማይና ምድርም ሳይቀሩ ያልፋሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እና የፈጣሪያችን ቃሉ ለዘዓለም ህያው ሆነው እስከ ዓለም ይኖራሉ። ዋልድባም ከነሙሉ ክብሩ በመድኅኒታችን ጠባቂነት እና ረደኤት ከትውልድ ትውልድ መተላለፉ ጥርጥር የሌለው እውነታ ነው።
መድኅኒዓለም ክርስቶስ ዘወትር በተዓምራቱ እና በቸርነቱ ያልተለየን የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን
ቸር እንሰንብት
 
ምንጭ፡- ዋልድባ ገዳምን እንታደግ!

27 comments:

  1. girum dink newu gena bizu meat yiwerdal

    ReplyDelete
  2. very amazing events. thanks to God we can what ever we like

    ReplyDelete
  3. "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው" ዘጸ.15:3፤

    ReplyDelete
  4. Abetu yeker belen geta hoy!

    ReplyDelete
  5. Abetu yekir belen geta hoy!

    ReplyDelete
  6. ናፍቆት እስክንድርSeptember 28, 2012 at 6:34 AM

    እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ይቺን ትንሿን ነገር ዓለምንም በአንድ ቀን አፍርሶ መስራት እንደሚችል አምናለሁ። ነገር ግን የናንተ ዘገባ ምን ያክል እውነት ነው? …. በአካባቢው ነዋሪ ከሆኑ ሰዎች፣ ወይንም ከመነኮሳቱ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋችሁ፣ ከተቻለም በመብረቅ የተመታውን ድልድይ ፎቶ አያይዛችሁ ብታቀርቡልን፣ በገዳሙ ይዞታ ላይ በድፍረት እየተከናወነ ያለውን ግንባታ ለምንቃወም ሰዎች ብርታት፣ ይህንን ለማድረግ ቆርጠው ለተነሱትን ለህወሃት ጀሌዎች ደግሞ ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

    ReplyDelete
  7. የአባቶቻችን አምላክ ህያው እግዚአብሄር ስሙ ዛሬም ዘወትርም የተመሰገነ ይሁን።

    ReplyDelete
  8. KIBIR LEHAYALU EGZIABHER YIHUN!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  9. Amlak Yetemesegene yihun! Egziabiher yezegeye bimeslim ayzegeyim sirawin yiseral any way Pls pray.







    ReplyDelete
  10. mekari yata nigus yale ande ken ayenegis!!! ayen eyalachew honual negeru!

    ReplyDelete
  11. "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው"
    "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው"
    "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው"
    አሜን::

    ReplyDelete
  12. Yemewgiawn beret lemikawem lersu yibesebetal.please correct pagume 3 is yerufael beal.not yeraguel.Ye kidus raguel beal meskerem 1 new.

    ReplyDelete
  13. እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን እኛ ብናቀላፋም የማይተኛ አባት አለን ለቤቱ የሚቀና
    እኛስ የቤተክርስቲያን ልጆቿ የሆንን ምን ማድረግ እንዳለብን እስቲ ሁላችንም እናስብ አብዛኛው ምዕመን በቤተክርስቲያናችን፣ በገዳማቱና በገዳማቱ አባቶች ላይ እየደረሰ ስላለው ጉዳት የማያውቅ ነው፡፡ ይህንን ጉዳት የሚያውቀው በጣም ጥቂት ምዕመን ነው፤ ጥቃቱ ግን በጣም የከፋ ነው ዛሬ ሩቅ አድርገን ያየነው ነገ አጠገባችን ሆኖ ብናገኘው ምን የምንይ ይመስለናል ቤተክርስቲያናችን መጠጊያችን ናት ቤተክርስቲያናችንን እኛ ልጆቿ ልንታደጋት አልቻልንም ለምን? እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ በሀይማኖት ደካማ ስለሆን? እምነት ስለሌለን? የኛ ጸሎት አይሰማም ብለን አስበን? ወይስ ባለቤቱ ይዋጋ ብለን ትተናል፡፡ መቼም ፀሎት ሳያደርግ ከቤቱ የሚወጣ ምዕመን አለ ብዬ አላምንም የአባቶችን ትዕዛዝ አንጠብቅ እኛ ስለራሳችን በሰላም አውለን ብለን ስንወጣ ቤተክርስቲያናችንን፣ ሀይማኖታችንን፣ ገዳማቱን ጠብቅልን ብለን አምላካችንን እንማፀን እኛ በዕምነታችን ደካሞች አንሁን የማንንም አንመልከት እኛ እንትጋ እግዚአብሔርም አይረሳንም፡፡
    እግዚአብሔር ለሀይማኖቱ የሚቀና በጐቹን ከስህተት የሚጠብቅ ለቤተክርስቲያን አለሁ የሚል አባትን ያምጣልን አሜን፡፡

    ReplyDelete
  14. egzihabeher lib yisten

    ReplyDelete
  15. egzabher lib yistachu

    ReplyDelete
  16. Amilak Egziabher simu yetemesegene yihun gena bizu teamirat enayalen abatochinm betsinat yaqoyiln egna be Egziabher chernet ena benesu tselot newu yalenenewu bicha geta lehulum neger mikiniyat alewu geta awaqinewu geta bewusanewu ayisasatim.....!!!

    ReplyDelete
  17. የዋልድባ ነገር የሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ሁሉ አይን ነው እባካችሁን ያለውን ነገር ሁሉ ተከታትላችሁ አሳውቁን መቼም ካልጠፋ መሬት እንዴት ዋልድባ ለመንግስት ታየው ዓላማው ቤተክርስቲያንና ልጆቿን ለማጥፋት የታለመ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ዛሬ ወጣቱ ለሀይማኖቱ ያለውን ጥንካሬ ያሳየበት ወቅት ነው እግዚአብሔር ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን እናንተንም ያበርታችሁ በሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ያለውን ነገር በግልጽ እንዲያውቁ ብትጥሩልን አንዳንድ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ አባቶችን ብታነጋግሩና ኃሳባቸውን ብትገልፁልን ያለውን ነገር ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ ሊያግዝ ይችላል፡፡
    የበላይሰብ እመቤት ወላዲተአምላክ እሷ ትታደገን

    ReplyDelete
  18. Egezihaber Yimesegen

    ReplyDelete
  19. Egzabher Lebona yestachew yefetare sera denke new. Bezo neger yasayenal "Ega zem benele Egziabher yenageral"

    ReplyDelete
  20. Le Fetari mean yesanawale gena temaratune yegeltsale eandawe kaltefa lemeleme meder mean asemlektachawe Abaitu be cherenethe asebachawe mechime lebe yalawe mastawale yemichele eandi bale yetefate godana ayegozem ena mastewalen adelachawe.

    Amelake hoye kebare temesgane Ethiopian tebekate!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  21. A leader who dose not believe in God never succeed.what we are looking at is not success.God can anhilate everything and everyone in a second.
    we will see a lot if HE ALLOWS US TO LIVE.bELIEVE IT OR NOT WE SEE AMIRACLE IN THE NEAR FUTURE.WAIT AND SEE.

    ReplyDelete
  22. They are giving our vast fertile land for fake Indian investors and Jihadists from saud arabia and they are destroying our church and Monestry and our heritage.
    These people they do not like Ethiopian history (because most of them are from "Banda' Family) they hate the Ethiopian Orthodox Tewahido Church because they know they will be vanished by them.

    ReplyDelete
  23. I do not even know the way I ended up here, however I assumed this publish was good.
    I do not recognise who you're but certainly you're going to a well-known blogger should you aren't already.
    Cheers!

    Also visit my web site: Christian Louboutin Outlet

    ReplyDelete
  24. Hello everyone, it's my first pay a quick visit at this
    web page, and post is genuinely fruitful for me, keep up posting these types of
    posts.

    Also visit my homepage ... cheap louis vuitton bags

    ReplyDelete