ደቂቀ ናቡቴ

Friday, September 28, 2012

ስለ መስቀል ክፍል ሁለት


በስመ ሥላሴ 
ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና፣ አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፤ በኪሩቤል ላይ የምትኖር የቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) ጥልቀት የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ፤ አቤቱ ምስጢርን ግለጽልኝ፤ ቃልህንም እናገር ዘንድ፣ ያለመሰልቸት ስለ አንተ እንድመሰክር አንተ አንደበት ሁነኝ አሜን።
“በምድር ላይ ኃጢአትን አሰረ፤ በሲዖል ሞትን አሸነፈ፣ በመስቀል ሳለ መርገምን ሻረ፣ በመቃብር ውስጥ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አስቀረ። (ቅዱስ አትናቴዎስ)
“መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር” (መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው)” (ሊቃውንተ ቤ/ክ)
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ በሚበልጥ ዓለምን ሁሉ ያዳነበት ከጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ ጥበብ ይህ ቅዱስ መስቀል ነው!”
    
በቀደም በክፍል ፩ (አንድ) ጽሑፌ መስቀል በመጽሐፍ ቅዱስ በሦስት ከፍዬ ማሳየቴ ይታወሳል፤ ይህም  ፩. መከራ መስቀለ ክርስቶስ
                 ፪. መከራ መስቀለ ክርስቲያንና
                 ፫. ዕፀ መስቀል
የመጀመሪያውን መስቀል ማለት መከራ መስቀለ ክርስቶስን መሆኑን  በቀደም በጻፍኩት ጽሑፌ በሰፊው የገለጽኩት ሲሆን፤ በክፍል ሁለቱ (፪)ቱ ደግሞ የቀሩትን ማለትም፡- መስቀል ማለት “መከራ መስቀለ ክርስቲያንና”፣ “ዕፀ መስቀል” በሚሉት ትርጉሞች ላይ ዳግም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘን መለያየታችን ይታወሳል።
ክፍል ሁለት ደግሞ እነሆ እንደሚከተለው ቀርቧል።  መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።
፪. “መከራ መስቀለ ክርስቲያን”፡- ማለት አንድ ክርስቲያን ወይም ሐዋርያ ስለ ክርስቶስ ስም፣ ስለ ወንጌል፣ ስለ ቤተክርስቲያን እድገት፣ ስለ ማህበረ ምዕመናን፣ የሚደርስበት መከራ፣ ስድብ፣ ሐሜት፣ መስቀል ይባላል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር “መስቀሌን የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለኔ ሊሆን አይገባውም።” ማቴ.፲፡፴፰/10፡38/ በማለት የተናገረው ለዚህ ነው። በተጨማሪም “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። አለ (ማቴ.፲፮፡፳፬/16፡24/፣ ማር.፰፡፴፬-፴፮/8፡34-36/ ጌታ መስቀሉን ተሸክሞ እንዳለ ቅዱሳን ሰዎች የሚቀበሉት የክርስቶስ ሳይሆን የራሳቸውን ነው። በመሆኑም ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል መሰቀሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በሰይፍ መመታት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ኢሳያስ በመጋዝ መተርተራቸው የቅዱሳን ሁሉ ልዩ ልዩ ጸዋተወ መከራ መስቀል ይባላል።
፫. “ዕፀ መስቀል”፡- በእንጨት የተሰራ መስቀል ማለት ነው። የውርደት ምልክት የነበረው መስቀል የድል አርማ ሆኗል። እንዴት ቢሉ፡-
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰ ደሙ ሰላምን ስላደረግ (ቆላ. ፩፡፳/1፡20/
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ይውርደት ሞት ያም በመስቀል ላይ ሞቶ ሞትን ድል የነሳበት የድል አደባባይ ስለሆነ (ፊሊ.፬፡፰/4፡8/ ስለ መስቀል ተጫማሪ ጥቅስ ካስፈለገ ማቴ.፳፯፡፴፪/27፡32/፣ ዮሐ.፲፱፡፳፩/19፡21)ን ይመልከቱ።
ማጠቃለያ፡-
ሁሌም መስቀል ሲዘከረ፤ መስቀል የሚል ቃል ሲነገርም ሆነ፤ ሲሰማ በክርስቲያኖች ልብ ውስጥ ልዩ መንፈስን ይፈጥራል። መስቀል በእርሱ ላይ የተሰቀለውን እግዚአ ኃይላት ክርስቶስን ያሳስበናል፡፡ የእሾህ አክሊል ደፍቶ፣ ጎኑ በጦር ተወግቶ፣ በብዙ መከራ ስቃይ በቀራንዎ የዋለውን ጌታ በውስጣችን ይስላል። የሲዖል መሠረት የተናወጠበት፣ ሰውና እግዚአብሔር ለዘማናት ለያይቷቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበት፣ ሞት ድል የሆነበት፣ የትንሳኤ መንገድ የተከፈተበት ልዩ መንፈሳዊ መሣሪያ መስቀል ነው።
ስለዚህ መስቀል ለምዕመናን የነፃነትታቸው፣ የዕርቃቸውና የሰላማቸው ምልክት በመሆኑ ለመስቀል ልዩ ክብር ይሰጣሉ፤ ይሰግዱለታልም። ማንኛውም ተግባር፤ ጸሎትን፣ ምግብን፣ ጉዞን፣ከመጀመራችን በፊትና ከጨረሱም በኋላ በትእምርተ መስቀል ያማትባሉ፤ በፈተና፣ በሐዘን፣ ክፉ ሐሳብ በሕሊናቸው በተፈጠረ ጊዜ ሁሉ ያማትባሉ። በከበረ ደሙ መስቀልን የቀደሰ ጌታቸው በኃይለ መስቀሉ ሁሉን ሊያደርግላቸው እንደሚችል በመታመን ይህን ያደርጋሉ፡፡ “እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ በሚበልጥ ዓለምን ሁሉ ያዳነበት ከጥበብ ሁሉ በላይ የሆነ ጥበብ ይህ ቅዱስ መስቀል ነውና!”  ለዚህ ነው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር” (መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው)” ያሉት። ይህ የመስቀሉ ነገር አምላክን ሰው የመሆንና እስከ መሪር ሞት ያደረሰውን ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ከማንከር በስተቀር ሊመረመርና ድርሰ-ነገሩ ሊስተዋል የማይቻል ረቂቅ ነው። በመሆኑም ነገረ መስቀሉ ለአንዳንዶች ፈተና ለሌሎችም ስንፍን ሆኖባቸዋል። ለሚያምኑ ምዕመናን ግን ከተና እንደወርቅ ነጥረው የሚወጡበት ነው።
በእውነት ጠላቶች እውነትን ለማጥፋተ ቢዘጋጁም በእርሱ ለዓለም እውነት ተሰብኳል። አይሁድ ሰዎችንና ክርስቶስን ለማራራቅ በመስቀል ቢሰቅሉትም በመስቀል ያፈሰሰው ክቡር የሚሆን ደሙ  ዓለሙን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቧል።
ለዚህ ነው የነቢያት የሐዋርያት፣ የቅዱሳን ሁሉ ትምህርታቸው፣ ስብከታቸው
“ንህነሰ ንስብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ”  /እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥/ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።  ፩ቆሮ.፩፡፳፫-፳፬/1ቆሮ.1፡23-24/ በማለት የተናገሩት።
በአጠቃላይ “መስቀል”+++
የክርስቲያኖች ተስፋ ነው፤ የሙታን ትንሳኤ ነው፤ የእውራን መሪ ነው፤ተስፋ ቅቡጻን ነው፤ካለ በኋላ መስቀል ትንቢተ ነቢያት ነው፤ ስብከተ ሐዋርያት ነው፤ ክብረ ሰማዕታት ነው፤ የጻድቃን ሞገስ ነው፤ የመነኮሳት ጽሙና ነው፤ የደናግል ንጽህና ነው፤ የቤተ ክርስቲያን መሠረት ነው፤ የዓለም መረጋጋት ሰላምም ነው። (ግብር ዮሐንስ አፈወርቅ ቅፅ 2) ይኸው ሊቅ በሌላ ክፍል “ክፉ ምንፈስ የተመታበትንና የቆሰለበትን ሰይፍ ካየ ወደ ሰይፉ ሊቀርብ አይችልም …… ስለዚህ በቤታችን፣ በግድግዳችን፣ በበራችን፣ በግንባራችን፣ በደረታችን፣ በጣታችንና በክንዳችን የመስቀሉ ምልክት ይኑራን፤ ምክንያቱም መስቀል ድላችን ነው። ከተሰጡን በረከቶች ሁሉ ታላቁ በረከት ነው…. የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ነው፤ በመሆኑም መስቀሉን በአእምሯችሁ እንደ ማህታም አትሙት።” (ግብር ዮሐንስ አፈወርቅ ቅፅ 7) በማለት ይመክራል። በቀላል አማርኛ በመስቀሉ የሰው ልጅ የበደል ካሳ ያገኘበት ነውና  የመስቀሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደር አሜን ይቆየን!።
 ስብሐት ወክብር ለእግዚአብሔር
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር  በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ እድሜ ለንሰሐ ዘመን ለፍሰሃ ሰጥቶኝ ይህችን ታህል ስለ አባታችን እንድመሰክር የረደኝ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
አመስግኛት የማልሰለች፣ ስለሷ ተናግሬ የማይደክመኝ፣ በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

5 comments:

  1. Also I much like the pretty purple colors with the Cruisers but if my son had an impression
    he might not. These foods rich in vitamin C contain tomatoes, grapes, oranges, cauliflower, melon, onion, garlic, apple, prickly pear, jujube as well as other
    fruits and vegetables, especially apple.

    Take a look at my homepage ... Evaluating Uncomplicated Methods For baby swing

    ReplyDelete
  2. It is recommended being applied to damp skin as a way to reduce greasiness.
    Diaper changes could be especially disturbing to sleep inside middle of the night, especially if the baby is wearing a great
    deal of clothes and blankets, in order that it's a fantastic idea to work with blankets and clothes that allow easy access inside the middle in the night so diaper changes will likely be as little disturbance as is possible.

    Also visit my site ... best rated baby swings

    ReplyDelete
  3. Thanks for sharing your thoughts on delaware incorporation services.
    Regards

    Review my web-site best stand mixer reviews ()

    ReplyDelete
  4. That may be very obviously, in the event that you utilize the actual coupon
    when you can make it and so it will save you undoubtedly the a many revenue through applying the actual idea with
    a specific time. The safety standards in China
    are not as rigorous because the United States and other countries, so kids' items are created with harmful substances.

    Here is my webpage :: best portable baby swing - http://matchsouls.com/tweet/?module=IonaMcnutt&params=1187 -

    ReplyDelete
  5. I like the valuable info you provide in your articles.
    I will bookmark your weblog and check again here regularly.
    I am quite sure I will learn plenty of new stuff right here!
    Good luck for the next!

    my page: cuisinart stand mixer reviews ()

    ReplyDelete