ደቂቀ ናቡቴ

Wednesday, September 26, 2012

“መስቀል መልእልተ ኩሉ ነገር ያድኅነነ እም ጸር - ከሁሉ በላይ የሆነ መስቀል ከጠላታችን ያድነናል!“ ቅዱስ ያሬድ



 “ሩቤል ላይ የምትኖር የቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) ጥልቀት የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ አቤቱ ምስጢርን ግለጽልን፤ ቃልህንም እንናገር፣ እናስተላልፍም ዘንድ ሁኔታዎችን ሁሉ አመቻችልን።
+++ ዝንቱ መስቀል ረድኤት ወኃይል +++ ለእለ ነአምን መራሔ ሕይወትነ +++
+++
ይህ መስቀል ለምናምን ለኛ ሕይወትን የሚመራ ረድኤትና ኃይላችን ነው +++
ቅዱስ መስቀል
መስቀል በመጽሐፍ ቅዱስ በሦስት ይከፈላል። . መከራ መስቀለ ክርስቶስ
                                      . መከራ መስቀለ ክርስቲያን
                                      . ዕፀ መስቀል
. መከራ መስቀለ ክርስቶስ ማለት፡-  
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ከጎልጎታ እስከ ቀራንዮ አደባባይ፣ ከዚያም እስከ ርደተ መቃብር የደረሰበት ጽኑ መከራ መስቀል ይባላል። የመስቀል ትርጉም ቅሉ መከራ ማለት ነው።
 ጌታችን በበረት መወለዱ፣ በጨርቅ መጠቅለሉ፣ በብርድ መንከራተቱ መስቀል ነው።
ወደ ግብጽ ተሰዶ እኛን ከስደት ነፍስ መመለሱ፣ሰይጣንን ከሰዎች ልቦና ማሳደዱ መስቀል ነው።
በአጠቃላይ ስለኛ የተቀበለው መከራ ሁሉ መከራ መስቀል ይባላል። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። ፩ቆሮ.፩፡፲፰ (1ቆሮ.118) በማለት የገለጸው። በተጨማሪም እንዲህ አለ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። ገላ.፮፡፲፬ (614) 
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በማከልም ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። ስለዚህ  ከዚህ በላይ የጠቀስኩት ሁሉ በክርስቶስ መከራ የሚተረጎሙ ናቸው። ለዚህም ነው ቅድስት /ክርስቲያናችን በዘወትር ጸሎቷ መስቀል ሃይላችን ነው፣ መስቀል ጽንአ ነፍሳችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን፣  መስቀል የነፍሳችን መድኃኒት ነው። አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምናለን፤ ያመነው በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም በማለት የምትጸልየው። መጽሐፈ ኪዳንም አኮ ከመይትርአይ ዝንቱ መስቀል አላ ከመ ይትሃለይ ይህ መስቀል (መከራ ክርስቶስ) በዐይን የሚታይ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ ነውበማለት ገልጿል።
ስለዚህ ሕማሙን ሞቱን እያሰብን እንደ ዮሐንስ ልንጸልይ ይገባናል። ቅዱስ ያሬድም መድሃኒት ስለሆነችው ስለሞቱ እና ስለ መስቀሉ ሲናገር ዝንቱ ውእቱ መስቀል በአማን እጸበ ያቀልል ሃይልነ ወጸወንነ ወሞገስነ ይላል። በዚያው ክፍል  “በሃይለ መስቀሉ ገብረ መድሃኒተ ሰደደ አጋንንተ አንሥአ ሙታን በሃይለ መስቀሉ ፈትህ ሙቁሐነ ትርጉሙም === መስቀሉ ሃይል መድሃኒትን አደረገ፤ አጋንንትን አሳደደ፣ ሙታንን አስነሳ፣ እስረኞችን ፈታ ይላል።
ይቀጥላል ፪ኛው መከራ መስቀለ ክርስቲያን እና ፫ኛው ዕፀ መስቀል የሚሉ ርዕሶችን ትርጉም እግዚአብሔር እንደፈቀደ በሚቀጥለው ጽሑፌ ይቀጥላል። አምላክ የነገ ሰው ይበለን ከመስቀል በረከተና ረድኤትን ያድለን። መልካም የመስቀል በዓል ይሁንላችሁ አሜን
ስብሐት ወክብር ለእግዚአብሔር
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር  በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ እድሜ ለንሰሐ ዘመን ለፍሰሃ ሰጥቶኝ ይህችን ታህል ስለ አባታችን እንድመሰክር የረደኝ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
አመስግኛት የማልሰለች፣ ስለሷ ተናግሬ የማይደክመኝ፣ በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

3 comments:

  1. No comment, THANKS TO GOD

    ReplyDelete
  2. Kale Hiwot Yasemalen

    ReplyDelete
  3. webwinkel beginnen post.nl webwinkel beginnen kosten

    Also visit my weblog ... webwinkel beginnen rabobank

    ReplyDelete