- ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል
ቅዱስ አትናቴዎስ
- ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል
ቅዱስ ሚናስ
- በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና
ታላቁ አባ መቃርስ
- አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡
- ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡
ማር
ይስሐቅ
- ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡
አረጋዊ መንፈሳዊ
- ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
- ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር››
ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
- ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
ቅዱስ አርሳንዮስ
- ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››
ቅዱስ እንድርያስ
- ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››
አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
- ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ