Friday, May 18, 2012

ቅ/ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳመጠ

  • ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል።
  • “ሃይማኖቴ እንደ አባቶቼ ነው” ያሉት የአባ ሰረቀ እና “የቅን ልቦና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎትን ያቋቋምኹት ልጆቼን የማበላቸው ስለተቸገርኹ ነው” ያሉት የ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ጉዳይ ያለውሳኔ ሐሳብ ለምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀርቧል።
  • አባ ጳውሎስ ከጥንተ አብሶ ጋራ በተያያዘ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና እንዲመሰክሩ ሊጠየቁ ይችላሉ።
  • ሊቃውንት ጉባኤው ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጎለት ያልቀረበው በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት የሊቃውንት ጉባኤውን ሰብሳቢ በእጅጋየሁ በየነ አማላጅነት ሲለማመጥ ታይቷል፤ ሊቃውንት ጉባኤው “በአንድ ወቅት በራስ ቅል ኮረብታ ላይ ኢየሱስና ዲያቢሎስ ቁማር ተጫወቱ . . . ዲያቢሎስም በጨበጣ ገባ” የሚለውና ሌሎቹም ጥንቃቄ የጎደላቸው ንግግሮቹ ፍጹም ውግዘት የሚገባቸው እንደኾኑ አመልክቷል።
  • የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አመራርና መዋቅር ይሻሻላል፤ በጠቅላላ ጉባኤና በቦርድ ይመራል፤ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እንደሚኾኑ ተጠቁሟል።
  • የማኅበራት መመሪያ ረቂቅ ለውይይት ቀርቧል፤ አሁን ባሉበት አኳኋን ከቀጠሉ “ሌላ ሲኖዶስ ይኾናሉ፤ የፖሊቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ይኾናሉ፤ በቀኝ ዘመምና ግራ ዘመም አቋም ቤተ ክርስቲያኒቷን ይውጣሉ/ይከፍላሉ” የሚል ስጋት የቀረበባቸው ማኅበራት ንብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተጠቃልሎ እንዲተዳደር ሐሳብ ቀርቧል፤ የመመሪያውን ረቂቅ በጥንቃቄ የተመለከቱት የምልአተ ጉባኤው አባላት ጉዳዩ በይደር እንዲታይ አድርገዋል።

 የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በግንቦት 8 ቀን 2004 ዓ.ም ስድስተኛ ቀን ውሎው በፕሮቴስታንት ድርጅቶች ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገላቸው የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት ለማፋለስ፣ ሥርዐተ እምነቷን ለመለወጥ፣ አገልጋዩንና ምእመኑን ለመከፋፈል በቡድንና በድርጅት ኾነው በመንቀሳቀስ ላይ ስለሚገኙት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳምጧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ በአጀንዳ ተ.ቁ (13) ላይ ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ በተመለከተው ርእሰ ጉዳይ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ከሊቃውንት ጉባኤ ጋራ በመኾን የቀረቡ ማስረጃዎችን መርምረው የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርቡ ሰባት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት ኮሚቴ ሠይሞ ነበር፡፡

በወቅቱ የኮሚቴው አባላት እንዲኾኑ ተመርጠው የነበሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ነበሩ፡፡ ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም ከተሠየመው ከእኒህ የኮሚቴው አባላት መካከል ሦስቱ (አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ቄርሎስ እና አቡነ እንድርያስ) በተለያየ ምክንያት መቀጠል ስላልቻሉ ቋሚ ሲኖዶሱ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስንና ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስን ተክቷል፡፡

ኮሚቴው ከሊቃውንት ጉባኤው የቀረበለትና መርምሮ በትናንትናው ዕለት ከቀትር በኋላ በጸሐፊው በኩል ለቅዱስ ሲኖዶስ በንባብ ያሰማው ሪፖርት ባለ60 ገጽ ሲኾን በዛሬው ዕለት ምልአተ ጉባኤው በሪፖርቱ ላይ በመወያየት የውሳኔ ሐሳቡን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሪፖርቱ በፕሮቴስንታንት ድርጅቶች ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገላቸው ኦርቶዶክሳውያን መስለው በሁሉም የቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ እና የአስተዳደር መዋቅሮች ውስጥ በመሰግሰግ ፕሮቴስታንታዊ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም ከሚንቀሳቀሱት ማኅበራት መካከል በስምንቱ ላይ ያተኮሩ የኅትመት ውጤቶችን፣ የድምፅ እና ምስል ማስረጃዎችን መርምሯል፡፡

የፕሮቴስታንት እምነት ተቋማት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋራ ያላቸውን የመሠረተ እምነት /ዶግማ/ ልዩነት /ድንበር/ አጥፍተው ቤተ ክርስቲያናችንን በቁጥጥር ሥር አውለው ባለችበት ፕሮቴስታንታዊ ማድረግ ወይም ቤተ ክርስቲያናችንን  የጦርነት ቀጣና በማድረግ እንደ ሕንድ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት መክፈል ዓላማ ያላቸው ማኅበራቱ በአሁኑ ሰዓት በሚያወጧቸው መጻሕፍትና መጽሔቶች እንዲሁም በራሪ ወረቀቶች የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በግልጽ ይቃወማሉ፤ አገልጋዩና ምእመኑ በማይመች አካሄድ እንዲጠመድ እና በዘረኝነት እንዲከፋፈል ጭምር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህም በማስረጃ ተደግፎ የቀረበ በመኾኑ ፍጹም መወገዝ ያለባቸው ማኅበራት ተለይተው ቀርበዋል፡፡

ከእኒህም ውስጥ ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት እንዲተላለፍባቸው የውሳኔ ሐሳብ ከቀረበባቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራት መካከል፡-
1.   ማኅበረ ሰላማ - በክልል ትግራይ ፍትሕ ቢሮ ተመዝግቦ ፈቃድ ባወጣበት ስሙ ማኅበረ ሰላማ ምትሕግጋዝ ማኅበር (Abune Selama Self Help Association) እየተባለ የሚጠራና ዋና ጽ/ቤቱ መቐለ የሚገኝ ነው፡፡ ባወጣው ፈቃድ መሠረት በልማት ሥራ ላይ መሳተፍ ሲገባው ከሕገ ወጥ ባሕታውያንና ሌሎች የተሐድሶ ማኅበራት ጋራ በመቀናጀት ‹‹በገዳማት ላይ ጥናት ማድረግ›› በሚል ሰበብ በቅርሶች ላይ ከፍተኛ ዘመቻ በማካሄድ ማንነትን ለማጥፋትና በአቋራጭ ለመክበር ይንቀሳቀሳል፤ ዘረኝነትን ያስፋፋል፡፡ የአሲራ መቲራው ገዳም አበምኔት ነኝ ባዩ አባ ገብረ መድኅን ገብረ ጊዮርጊስ ከማኅበሩ መሪዎች ጋራ በድብቅ በመገናኘት ዕቅዱን ለማስፈጸም ይንቀሳቀሳል፡፡
2.   ማኅበረ በኵር - በ1983 ዓ.ም የተመሠረተ ሲኾን መሥራቹ በ1953 ዓ.ም ከቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተባረረው መሠረት ስብሐት ለአብ ነው፡፡ ከምሥረታው ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በፕሮቴስታንቶች ድጋፍ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሌሎች የተሐድሶ ኑፋቄ ማኅበራት ‹‹አርኣያችን ነው›› ይሉታል፡፡ ጮራየተሰኘ መጽሔት ያሳትማል፡፡ መጽሔቱን በሕገ ወጥ መንገድ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለሰንበት ት/ቤቶችና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ግባኤያት ይልካሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት  አግዛቸው ተፈራ የተባለው በዋና አዘጋጅነት በሚሠራበት መጽሔት የጸሎት መጻሕፍትን ይቃወማሉ፤ አባቶችን ይዘልፋሉ፤ አዋልድ መጻሕፍትን አይቀበሉም፤ ‹‹ቅዱሳት ሥዕላት አያስፈልጉም›› ይላሉ፤ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም አማላጅ ነው››፤ ሥልጣነ ክህነትን አይቀበሉም፤ የእምነት ልዩነት ድንበርን ያፈርሳሉ፤ ‹‹ቅዱስ ቍርባን መታሰቢያ ነው፤ ውላጤ ኅብስት የለም›› ይላሉ፤ ምስጢረ ሜሮንን ይቃወማሉ፤ ‹‹ሥጋ በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ አልኾነም›› ይላሉ፡፡
3.   የምሥራች አገልግሎት - በ1990 ዓ.ም የተመሠረተና አሸናፊ ሲሳይ በተባለ ግለሰብ የሚመራ ሲኾን ‹‹ቤተ ክርስቲያን የውጊያ ቀጣና ናት›› በማለት ለእንቅስቃሴው የሚረዱ 34,000 ‹‹እርሾዎችን›› በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመሰግሰግ ከፍተኛ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ የሚደረግለት፣ እያንዳንዳቸው ከ100 - 160 አባላት ባሉት ኅቡእ ቡድን (Cell based) የሚንቀሳቀስ አካል ነው፡፡ ‹‹ፕሮቴስታንት እና ኦርቶዶክሳውያን በመሠረተ እምነት አንድ ናቸው›› ከሣቴ ብርሃን ከተባለው ድርጅት ጋራ አንድ ዐይነት ዓላማ ያራምዳል፤ የክርስቶስን አምላክነት በአግባቡ አያምንም፤ ምንኵስናን ይቃወማል፤ አዋልድ መጻሕፍትን አይቀበልም፡፡
4.   አንቀጸ ብርሃን - ከሰበታ መካነ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ተለይቶ የወጣው አሸናፊ መኰንን የሚያሳትማቸውን የኑፋቄ መጻሕፍት ያስተዋውቃል፡፡ በሌላ ስያሜው ራሱን ‹‹ማኅበረ መንፈስ ቅዱስ›› እያለ ይጠራል፡፡ ‹‹የኢ////ያን እምነትና ሥርዐት የጠበቀ መንፈሳዊ ጽሑፍ›› በሚል በኅቡእ በሚያሰራጫቸው ጽሑፎቹ ምሥጢረ ሥላሴን አፋልሶ ያስተምራል፤ ምስጢረ ሥጋዌን በማፋለስ ቅብዐትን ይሰብካል፤ በካህን ፊት የሚደረግ ኑዛዜን ይቃወማል፡፡
5.   የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር - በኑፋቄያቸው ከማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት የተሰናበቱ ተወግዞ የተባረረው የሃይማኖተ አበው ማኅበር ሰለባዎች ነው፡፡ አቶ መስፍን በተባለ ግለሰብ ይመራል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ወደ ፕሮቴስታንትነት መቀየራቸውን ሳያውቁት ሃይማኖታቸውን የሚያስክዱ የርቀት ትምህርቶችን ይሰጣል፤ ኅትመቶችን ያሰራጫል፤ ቤተ ክርስቲያንን በግልጽ ይዘልፋል፤ የሥጋ ወደሙን አማናዊነት አያምንም፡፡
6.   የእውነት ቃል አገልግሎት - ድርጅቱ ይህን ስያሜ ከመያዙ በፊት በመጀመሪያ BGNLJ (Brothers Gathered Unto Lord Jesus) በኋላም (Bible Truth Ministry) እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የድርጅቱ መሪ በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትና ማኅበረሰብ ብርታት የተባረረው ግርማ በቀለ ነው፡፡ ሌላው ተጠቃሽ ግለሰብ ሥዩም ያሚ የሚባለው ነው፡፡ ድርጅቱ ከእንግሊዝኛ በሚተረጉማቸው መጻሕፍት የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ክፉኛ ያብጠለጥላል፤ በየክልሉ በከፈታቸው ቅርንጫፍ ማከፋፈያዎች ጽሑፎችን በነጻ በማደል፣ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ ታሪክን በማዛባትና በአዋልድ መጻሕፍት ላይ የማይገባ ትችት በመሰንዘር አገልጋዮችን ያደናግራል፡፡



የድርጅቱ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ መቀየር እንደ ኾነ ከኅትመቶቹ መረዳት ይቻላል፡፡ ለዚህም ከፕሮቴስንታን ኮሌጅ የተመረቁ መናፍቃንን ቀጥሮ በደብረ ዘይት፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ጎባ፣ ወናጎ፣ ባሕር ዳር፣ ሐዋሳ፣. . .ወዘተ በከፈታቸው ቅርንጫፎች የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን ሥራ እንዲያቀላጥፉ ያደርጋል - በራሪ ጽሑፍ ማሰራጨት፣ የርቀት ትምህርት መስጠት፣ ወደ ገዳማት እና አድባራት ተመሳስሎ በመግባት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ተመሳስሎ በመስረግ በጎችን ለመንጠቅ እየተሯሯጠ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ የሚያስፋፋቸው ኑፋቄዎች ‹‹ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ ለአንድ ሺሕ ዓመት ይነግሣል›› ይላል፤ ‹‹ወልድም መንፈስ ቅዱስም አማላጆች ናቸው›› ይላል፤ አጽዋማትን ይቃወማሉ፤ ሥልጣነ ክህነትን አይቀበሉም፤ የቅዱሳንን አማላጅነት አይቀበሉም፡፡

‹‹የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት›› በሚል ስያሜ የሚጠራውና ነሐሴ 10 ቀን 1996 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስቴር ተመዝግቦ በአዲስ አበባ ገርጂ ጽ/ቤት ከፍቶ ኑፋቄ የሚያስፋፋ፤ በደሴ፣ ከላላ፣ ጎንደር፣ ጎጃም እና ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍቶ በሚንቀሳቀሰው ማኅበር ላይ (የቦርድ ሰብሳቢው መ/ር ሙሉጌታ ደምሴ ይባላል) የቀረቡት ማስረጃዎች ተጠናክረው ምርመራው እንዲቀጥል ኮሚቴው ሐሳብ አቅርቧል፡፡
በተለይም የዚህ ማኅበር አባል እንደ ኾነ የሚታወቀውና ‹‹በውኑ በማርያም ማመን ይገባሃልን?›› በሚል ርእስ የኑፋቄ መጽሐፍ የጻፈው ‹መጋቤ ጥበብ› ሰሎሞን ጥበቡ ፍጹም ውግዘት ከሚገባቸው ግለሰቦች መካከል እንደኾነ የኮሚቴው ሪፖርት ያስረዳል፡፡

በሪፖርቱ መሠረት በግለሰብ ደረጃ ከተዘረዘሩት መካከል፡-
1.   ጽጌ ስጦታው - ቅዱስ ሲኖዶስ በነገረ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ስሕተት መፈጸሙን አጣርቶ ጥያቄና መልስ ሲያካሂድበት ‹‹ተሳስቻለኹ፤ ልመለስ›› በማለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በቀን 29/11/2003 ዓ.ም በቁጥር 4560/136/90 በጻፈው ደብዳቤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም የሐዲሳት መምህር አባ ገብረ ኢየሱስ ዘንድ ልኮት ከጓደኛው ጋራ በፈጸመው ተመሳሳይ ጥፋት ከገዳሙ የተባረረ ነው፡፡

ግለሰቡ ከቀድሞው በባሰ እኵይ ተግባር ተጠምዶ ይገኛል፤ የራሱን ድርጅትና ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አቋቁሞ ንግዱን በሃይማኖት ስም እያጧጧፈ ‹‹ይቅርታ አድርጉልኝ›› ያላቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እያንቋቋሸና እየዘለፈ ይገኛል፡፡ ከብዙ ኑፋቄው መካከል ‹‹ይነጋል›› በተሰኘው መጽሐፉ ‹‹እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት፤ ተኣምረ ማርያምን የጻፉት ፀረ - ወንጌሎች ናቸው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ሁሉ ካህን ነው፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠው በጦርነት ነው፤ በቅዱሳን ስም መዘከር አግባብ አይደለም፤…›› እያለ ይወሸክታል፡፡

በሌሎችም ጽሑፎቹ የመነኰሳትን ክብር አቃሏል፤ ‹‹ደርግ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ቴዎፍሎስን በመግደሉ ሲኖዶሱ ተስማምቶበታል›› በማለት ምእመኑ በሲኖዶስ ላይ ያለው እምነት ለመሸርሸር ሞክሯል፡፡ ‹‹ለታቦት፣ ለመስቀል እና ለሥዕል መስገድ፤ የጾም መብዛት፣ በሕግ በኾነ ጋብቻ በተወሰኑ ቀናት ከሩካቤ ሥጋ መከልከል በሕዝቡ ላይ የተጫነ የአማራ ቀንበር ነው፤›› ይላል፡፡
2.   አሸናፊ መኰንን - አንቀጸ ብርሃን በሚል ስያሜ በሚያሳትመው መጽሔት ለአብነት ያህል ‹‹በእኛ ቤተ ክርስቲያን አምላክነቱን አጉልቶ የሰውነቱን ቅርበት መዘንጋት፣ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የሥጋውን ቅርበት አግንኖ የመለኮቱን ክብር መርሳት የተለመደ ነው፡፡ መጽሐፉ ግን ያቻችለዋል፤›› የሚሉና የመሰሉ በርካታ ክሕደቶችን ጽፏል፡፡
በመመሪያ ሓላፊ ደረጃ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና መዝገብ ቤት ሓላፊ ከኾነችውና የ‹ሙሉ ወንጌል› ቤተ እምነት ከምታዘወትረው ወ/ሮ ዐጸደ ግርማይ ጋራ ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው ይነገራል፡፡ በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አማካይነት በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት መሽጎ በበዓለ ሢመት፣ በዐበይት በዓላት፣ በደቀ መዛሙርት ምረቃ መርሐ ግብሮች ላይ በፓትርያሪኩ ስም የሚተላለፉ መልእክቶችን እስከ መጻፍ መድረሱ ይነገርለታል፡፡
3.   ደረጀ ገዙ - በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ ደረጃ ኑፋቄውን ሲያራምድ ከቆየ በኋላ ሲነቃበት ወደ አዲስ አበባ ተዛውሮ በከሣቴ ብርሃን የተሐድሶ ድርጅት ውስጥ በዋና ጽ/ቤት ተቀጥሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ በባሕር ዳር ከተማ በድብቅ ለካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ደባትራንና መዘምራን በተከራየው ቤትና ‹‹በሰሜን ምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት /ቤት›› ሥልጠና ሰጥቷል፤ ከኑፋቄዎቹ መካከል ‹‹ጽዮን የሚለው ስም ከእመቤታችን ጋራ ዝምድና የለውም፤ የተራራ ስም ነው፤ ለቅዱሳን ይኹን ለመላእክት ስግደት አይገባም፤ ለቤተ ክርስቲያን ስግደት ይገባል ማለት ክርስቲያን ለኾነው ሁሉ ይሰገድለት ማለት ነው፤ እንደ ኦሪታውያኖች የዕጣን ጭስ እንድንወዝውዝ አልታዘዝንም፤›› በሚል ግልጽ ድፍረት በዐውደ ምሕረት በድፍረት ተናግሯል፤ በመጽሐፍ ጽፏል፡፡ በውስጥ አጋፋሪዎቹ እየተረዳ እርሱም ባለቤቱም መናፍቅ መኾናቸው እየታወቀ በ27/09/98 ዓ.ም በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሥርዐተ ተክሊል›› ፈጽሟል፡፡
4.   በዛ ስፍርህ - ከቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጅ ተመርቆ በባሕር ዳር ከሣቴ ብርሃን  የኑፋቄ ተልእኮውን ሲወጣ ከቆየ በኋላ አሁን ወደ ሱዳን መሻገሩ ይነገርለታል፡፡ ደቀ መዝሙር በዛ በሚል ስም ‹‹መቅደስ የገቡ መናፍቃን›› በሚል ርእስ ከደረጀ ገዙ ጋራ በጻፈው የክሕደት መጽሐፍ ከላይ የተገለጹትን ኑፋቄዎች ከመናገሩም በላይ ‹‹የጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ›› በማለት የቤተ ክርስቲያንን መብት በመጋፋቱ በሕግም ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡
5.   ግርማ በቀለ - ከጽጌ ስጦታው ጋራ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመለወጥ ሲሯሯጥ ተደርሶበት የተባረረ ነው፡፡ ከኑፋቄው መካከል ‹‹ቤተ ክርስቲያን ማለት ክርስቲያኖች ተሰብስበው አምልኮ የሚፈጽሙበት ቦታ አይደለም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በእውነተኛዪቱ መቅደስ አገልጋይ ነው፤ አሁንም ይማልዳል፤ እንደ ሊቀ ካህንነቱ ከዚያ ኾኖ ቤተ ክርስቲያንን ያስተዳድራል፤ ኢየሱስ ሊቀ ካህን ከኾነ እኛ ሁላችን ካህናት ነን፤ እንደ ወረቀት ይቆጠር የነበረው ሰሌዳ ታቦት ተብሎ አሁን ወደሚገኝበት ደረጃ ተሸጋግሯል፤. . .›› የሚሉት ይገኙበታል፡፡
6.   አግዛቸው ተፈራ - በአሰላ ከተማ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት የነበረ፣ በነፋቄ መርዝ ከተነደፈ በኋላ በሰንበት ት/ቤቱ ትጋትና በሰበካ ጉባኤው ጥብቅ ክትትል ተጋልጦ አልመለስ በማለቱ የታገደ ነው፡፡ የክሕደት ትምህርቱን ‹‹የተቀበረ መክሊት›› ‹‹የለውጥ ያለህ›› ‹‹ጥላና አካል››. . .በተባሉ መጻሕፍቱ ያሰራጫል፡፡ ከጥር 2002 ዓ.ም ጀምሮ የመናፍቃኑ ማኅበረ በኵር መጽሔት የኾነው ጮራ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በመኾን ተቀጥሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ከኑፋቄው ጥቂቶቹ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉባኤ ኒቂያና ቁስጥንጥንያ ከረቀቀው የእምነቷ መሠረት ከኾነው ጸሎተ ሃይማኖት ውጭ ሌሎች ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች ስላሏት የአስተምህሮ ለውጥ ያስፈልጋታል፤ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀል ያልተገባ ክብር ሰጥታለች፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አምልኮተ ዕፀ መስቀልን በቤተ ክርስቲያን እንዳስፋፉ የእርሳቸውን ሥራ ዕውቅና ለመስጠት 2000 . ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳዘጋጀች ሲተች ይታያል፤ በዓለም ላይ በሐዲስ ኪዳን ዘመን ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታቦት እንደሌለ ይታወቃል፤ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ብቻ እንጂ ኦሪትንና ወንጌልን በአንድ ላይ እንድታስኬድ የታዘዘችበት ኹኔታ ፈጽሞ የለም፤. . .›› የሚሉት ይገኙበታል፡፡
7.   መጋቤ ጥበብሰሎሞን ጥበቡ - ‹‹በውኑ በማርያም ማመን ይገባሃልን?›› በሚል የኑፋቄ መጽሐፍ የጻፈ ሲኾን ‹‹የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት›› አባል ነው፡፡ በማኅበሩ ላይ የሚደረገው ተጨማሪ ክትትል እንደተጠበቀ ኾኖ ይህ ግለሰብ ግን ራሱን ችሎ ፍጹም ውግዘት እንዲተላለፍበት ኮሚቴው የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል ለሊቃውንት ጉባኤው በቀረበው የሰነድ ማስረጃ ተ.ቁ(8) ላይ የተመለከተው በጋሻው ደሳለኝ በሪፖርቱ እንደተመለከተው ሊቃውንት ጉባኤው ለጥያቄና መልስ ተደጋጋሚ ጥሪ በቃልና በጽሑፍ ቢያደርግለትም ጥሪውን አክብሮ ባለመቅረብ አጉራ ዘለልነቱን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለሠየመው አካል ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው በጋሻው ግን በሃይማኖቱ ሕጸጽ ዙሪያ የቀረበው ሪፖርት በትናንትናው ዕለት አጀንዳ ኾኖ እንደሚታይ ከውስጥ ተባባሪዎቹ ባገኘው መረጃ ይመስላል ገና በጠዋቱ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቅጽር ከተፍ ብሏል፡፡ በጋሻው በቅጽሩ በራፍ ላይ ደርሶ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ከኾኑት መጋቤ ምስጢር ዓምደ ብርሃን ቆሞ እንደተነጋገረ በአቅራቢያው የተከታተሉ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን  ተናግረዋል፡፡ የበጋሻው ንግግር የልምምጥ ቃና ያለው ‹‹በእንተ እጅጋየሁ›› ዐይነት ተማጥኖ ነበር፡-
በጋሻው ጠየቀ - ‹‹/ እጅጋየሁ ልከውኝ ነው፤ አልነገርዎትም?››
መጋቤ ምስጢር ዓምደ ብርሃን - ‹‹ከሌላ ነገር ጋራ አታገናኘው፤ ንጹሕ ሥራ ነው እየሠራን ያለነው››

ከቀትር በኋላ በቀረበው የኮሚቴው ሪፖርት ግን በጋሻው የተላከበት የወ/ሮ እጅጋየሁ ሞገስና በመጋቤ ምስጢር ዓምደ ብርሃን ምላሽ ውስጥ ግልጽ ኾኖ የወጣው የትእዛዝ መልእክት አልነበረም የተሰማው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልጅነት ጠባይ የሌለው በጋሻው በተለያዩ ጊዜያት እጅግ ጥንቃቄ በጎደለውና ድፍረት በተሞላበት ኹኔታ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ያስተምር ስለነበር ብዙ ሕዝብ አሳስቷል፡፡ አባቶችን ከመዝለፍ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ክብር በማዋረዱ ቀርቦ ሊጠየቅ ይገባው ነበር፡፡

በተለይም ‹‹ሳንጠነቀቅ መንፈስ እንዳቀበለን/እንዳዘዘን እናስተምራለን›› በሚለው የዘወትር መርሑ ‹‹በአንድ ወቅት በራስ ቅል ኮረብታ ላይ ክርስቶስና ዲያቢሎስ ቁማር ተጫወቱ፤ የቁማሩ አሸናፊ በሰው ልጆች ልብ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ለዘላለም ይነግሣል፤ ይህ ሲኾን ተስማምተው ጫዋታውን ለመጀመር ያላቸውን ሲያስይዙ ዲያብሎስ ብልጣብልጥ ቢጤ ነበርና በጨበጣ ገባ(የሚያስይዘው ሳይኖረው)፤ ክርስቶስ ግን የዋህ ነበርና የሚያስይዘው ቢያጣ ቅድስት ነፍሱን በአደባባይ አስያዘ፡፡ በመጨረሻ ግን በነፍሱ የተወራረደው ጌታ ጨዋታውን በርግጥ አሸነፈ፤›› እያለ ለተናገረው መልስ እንዲሰጥ ይፈለግ ነበር፡፡ የስብሰባው ምንጮች እንዳሉት ኤሽታኦል /2001 ዓ.ም/ በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 30 ላይ የሰፈረው ይኸው ቃሉ የሚያስጠይቀው እንደኾነና ተጠርቶ አለመቅረቡ ጭምር ከግምት ተወስዶ ውሳኔው በምልአተ ጉባኤው ደረጃ እንዲተላለፍ ሐሳብ ቀርቧል፡፡

በተመሳሳይ ኹኔታ 131 የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአባ ሰረቀ እና ጌታቸው ዶኒ ላይ ባቀረቧቸው ማስረጃዎች የግለሰቦቹ የሃይማኖት ሕጸጽ መመርመሩን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

አባ ሰረቀ በሰሜን አሜሪካ ሳሉ ‹‹እመቤታችን ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከኃልዮ፣ ከነቢብ ከገቢር የለያት፣ የጠበቃት ስትኾን የአዳም በመኾኗ /እንደመኾኗ/ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፍ ከነበረው የውርስ ኃጢአት ግን የተለየች እንዳልነበረች፤ ከዚህ የውርስ ኃጢአትም መንፈስ ቅዱስ አንጽቶና ቀድሶ የእግዚአብሔር ቃልን/ወልድን/ ለመቀበል ዝግጁ አደረጋት›› ከሚሉ ወገኖች ጋራ በመተባበር ‹‹እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት›› እንደሚሉ ነበር የሰነድ ማስረጃ የቀረበባቸው፡፡

በመስከረም ወር 1997 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ የደብረ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተነሣው የነገረ ሃይማኖት ውዝግብ የአጥቢያው ካህን ቀሲስ አስተርኣየ ጽጌ ‹‹እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአዳማዊ ዘር በኩል ከሚተላለፈው የውርስ ኀጢአት መንፈስ ቅዱስ አንጽቷታል›› ሲሉ የያዙትንና የቤተ ክርስቲያን ያልኾነውን እምነት በመቃወም ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ይህ መናፍቅነት መኾኑን ገልጸው ምላሽ ሰጥተዋል - ‹‹እመቤታችን ከአዳም የውርስ ኀጢአት የነጻችው ከመወለዷ በፊት ነው፤ ቤተ ክርስቲያናችን የምታምነውና የምታስተምረው፡- አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት፣ መርገመ ሥጋ፣ መርገመ ነፍስ የሌለባት፣ ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኅሊና ታስባ ትኖር የነበረች፣ በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ ሐሣብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች፣ ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስተ ቅዱሳን ናት፡፡››

ከጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ራሳቸው አባ ሰረቀ ይህንኑ ጉዳይ በታኅሣሥ ወር 2004 ዓ.ም ‹‹እውነትና ንጋት›› በሚል ርእስ ባሳተሙት መጽሐፍ መሰል ጥራዝ በቀሲስ አስተርኣየ ጽጌ እና በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ መካከል የተደረገውን ምልልስ ባስረዱበት ክፍል ነገሩን በንጽጽር በማቅረብ ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡

ይህ ልዩነት ወደ ሊቃውንት ጉባኤና ቅዱስ ሲኖዶስ ተልኮ ውሳኔ እንዲያገኝ በሰሜን አሜሪካ ከነበረው ማኅበረ ካህናት ጋራ በመኾን ኅዳር 16 ቀን 1997 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ መላካቸውን ለሊቃውንት ጉባኤ ማስረዳታቸው የተነገረው አባ ሰረቀ÷ ‹‹በአባቶቼ ሃይማኖት ነው የማምነው፤ ርእሰ መንበር የኾኑት አባት [አባ ጳውሎስ] እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤ እናንተ የምትሉት የእኔም እምነት ነው፤ በተላከው ደብዳቤ ይኹን በመጽሐፌ የገለጽሁት ያሉትን ሐሳቦች ነው፤ አስታርቃችኹ ንገሩኝ›› በማለት መግለጻቸው ተመልክቷል፡፡
ትላንት በተሰማው የኮሚቴው ሪፖርትም አባ ሰረቀ የእነ ቀሲስ አስተርኣየን አቋም በመቃወም እመቤታችን ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈባት መኾኗን እንደሚያምኑ በመመስከራቸው ‹‹ምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ይስጥበት›› ማለቱ ተዘግቧል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በጉዳዩ ላይ የሚያሳልፈው ውሳኔ የሚጠበቅ ኾኖ÷ አባ ሰረቀ የሰበሰቧቸውን ማስረጃዎች በመጽሐፍ መልክ ከማሳተምና በይፋ አስመርቀው የውይይት ርእሰ ጉዳይ ከማድረግ ይልቅ የተጠረጠሩበትን የሃይማኖት ሕጸጽ ለሚመረምረው ኮሚቴ ማቅረብን ለምን አልመረጡም? የሚለው ምላሽ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡

‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ከሦስት የእምነት ተቋማት ጋራ የተጻጻፏቸውንና ለአንዳንዶቹም አባል መኾናቸውን የገለጹባቸው ስማቸውንና ሙሉ ፊርማቸውን የያዙ ደብዳቤዎች የእርሳቸው አለመኾናቸውን በመካድ በፊርማና አሻራ ምርመራ እንዲረጋገጥላቸው ለሊቃውንት ጉባኤው ጥያቄ አቅርበዋል - ‹‹አሻራዬ በአባ ዲና ይታይ›› ብለዋል ጌታቸው ዶኒ፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ ባለአደራ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በቁጥር ቅ/ል/መ/ፈ/አ/8/2000 በቀን 14/01/2000 ዓ.ም ‹‹የቅን ልቡና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎት የእምነት ተቋም›› ተመዝግበው የተቋሙ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ በመኾን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ቀበሌ 02/04 በተከራዩት ግቢ ለኦርቶዶክሳዊ እምነትና ሥርዐት ተቃራኒ የኾነ ነገር ለማራማዳቸው ሲጠየቁም አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል - ‹‹ልጆቼን የማበላው ተቸግሬ ነው፡፡››
‹‹ከጊዜ በኋላ ለቅዱስ ፓትርያሪኩ የይቅርታ ደብዳቤ ጽፌ ሥራ ሰጥተውኛል›› ያሉት ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው እርሳቸው የጻፉትን የይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤና በምላሹ ፓትርያሪኩ የጻፉላቸውን ደብዳቤዎች በማስረጃነት ማቅረባቸው ተገልጧል፡፡

ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች በኩል 67 ግለሰቦች ከእኒህም ውስጥ በሕይወት ያሉና የሌሉ፣ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የሃይማኖት ሕጸጽ እንዳለባቸው የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ሥራዎች ማስረጃዎች መቅረቡን በሪፖርቱ ገልጧል፡፡ ሪፖርቱ አያይዞም የአንዳንዶቹ ስም ዝርዝር ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተልኮ በአድራሻ ተፈልገው እንዲጠሩ ተደጋጋሚ ጥያቄ የቀረበ ቢኾንም ሀገረ ስብከቱ አግኝቶ ሊያቀርባቸው እንዳልቻለ አስታውቋል፡፡ በመኾኑም ወደፊት ማስረጃው እየተጠናከረ ምርምራውን ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚደረግ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ከቀትር በፊት በነበረው የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አዲስ አመራርና አወቃቀር ማሻሻያ ላይ ተነጋግሯል፡፡ የአመራርና አወቃቀር ለውጡ ኮሚሽኑ በዐዋጅ ቁጥር 621/2001 እና ደንብ ቁጥር 168/2001 በሚደነግገው መሠረት በዳግም ምዝገባ በሰርቲፊኬት ቁጥር 1560 ‹‹ኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት›› ኾኖ መመዝገቡን ተከትሎ ከሃይማኖት አገልግሎት ጋራ ሳይቀላቀል ራሱን የቻለ የልማት ድርጅት ኾኖ ለመሥራት የሚያስችለው ነው፡፡

በዐዋጁ ላይ የማኅበራትና በጎ አድራጎት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄነራል በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዐዋጁና ደንቡ መሠረት እንደ ልማትና በጎ አድራጎት ተቋም ጠቅላላ ጉባኤና ቦርድ ያዋቅራል፤ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ብዛት 20 ሲኾን የቦርዱ አባላት ደግሞ ዘጠኝ ናቸው፡፡ ከኻያው የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ዐሥሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ሲኾን የተቀሩት ዐሥሩ ደግሞ ከምእመናን የሚመረጡ ባለሞያዎች ይኾናሉ፡፡

ለማኅበራትና በጎ አድራጎት ኤጀንሲ ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴና የኦዲት ሪፖርቶች፣ የንብረት ይዞታ፣ የዓመት ዕቅድና ሌሎችም ተዛማጅ ሰነዶች እያቀረበ ያስገመግማል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውና ቦርዱ ለኮሚሽኑ አመራር በመስጠትና ቁጥጥር በማድረግ ሙሉ ሥልጣን የሚኖራቸው በመኾኑ እንደ ችግር የሚጠቀሰውን የፓትርያሪኩን ጣልቃ ገብነት ለመከላከል እንደሚያስችል ተነግሯል፡፡ 

ኮሚሽኑ 90 በመቶና ከዚያም በላይ ገቢውን ከውጭ የሚያገኝ ሲኾን በአዲሱ አሠራር መሠረት 70 ከመቶ ወጪውን ለፕሮጀክት/ዓላማ ማስፈጸሚያ/ ብቻ፣ 30 ከመቶ ገቢውን ደግሞ ለአስተዳደር ወጪ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠሪ የኾነው ጠቕላላ ጉባኤው ከተሰበሰበ በኋላ የቦርዱ አባላቱን የሚመርጥ ሲኾን ‹‹የኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ›› የሚለው መዋቅር ቀርቶ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እንደሚኾኑ ተጠቁሟል፤ የሊቀ ጳጳሱ ምክትል በበጎ አድራጎት ድርጅት ባሕርይን በመገንዘብና በልማት አመራር ብቁ ልምድ ያካበተ ባለሞያ እንደሚኾን ተመልክቷል - ‹‹ስንት ምሁራን ያሏት ቤተ ክርስቲያን እንዴት የጡረታ መውጫ ትኾናለች?›› ብለዋል እርጅና የተጫጫናቸውን የወቅቱን ኮሚሽነር ድክመት የተቹት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፡፡

የአሁኑ ምልአተ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት የሚኾኑ 10 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን የመረጠ ሲኾን እነርሱም፤ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና አሁን የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ኾነው የሚመሩት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ናቸው፡፡

ፓትርያሪክ አባ ጳውሎስ በየጊዜው ከለጋሾች የሚሰጠውን የኮሚሽኑን የፕሮጀክት በጀት በየምክንያቱ በመጠየቅ ማባከናቸውን በመከላከላቸው የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ፊርማ ተሰርዞ የኮሚሽኑ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሒሳብ በኮሚሽነሩና በፋይናንስ መምሪያ ሓላፊው ጣምራ እንዲንቀሳቀስ ለአምስት ባንኮች የተለያዩ ቅርንጫፎች ያስተላለፏቸው ትእዛዞችም በዚህ የአመራርና አወቃቀር ለውጥ መሠረት ተቀባይነት እንደማይኖረው ተገልጧል፡፡

በሌላ በኩል ምልአተ ጉባኤው በቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ዙሪያ በመወያየት እስከ አሁን የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ኾነው ሳለ ያልተመለሱትን 283 ቤቶች በማስመለስ ረገድ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ጥረት በአግባቡ አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡፡ እስከ አሁን ድርጅቱ 16 ሕንፃዎችን፣ 271 ቤቶችንና 10 መጋዘኖችን ያስተዳድራል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎቻችንን ይከታተሉ፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤ 
አሜን፡፡ (ምንጭ: ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 9/2004 ዓ.ም፤ May 17/ 2012)

13 comments:

  1. When your kids gets somewhat older, their vision should be even
    better. The story from the virgin birth of Jesus holds a good
    looking truth of unconditional love and hope that transcends
    the boundaries of organized religion and speaks
    directly for the purity of our connection to Spirit.

    My web-site :: best rated baby swing

    ReplyDelete
  2. I have read a few excellent stuff here. Certainly value bookmarking for revisiting.
    I wonder how much effort you put to create this type of magnificent informative website.


    Feel free to visit my web-site - Quick Secrets and techniques For stand mixers In britain

    ReplyDelete
  3. Try a Jumper As an replacement for walkers, jumpers are first class,
    though they may be dangerous if your child is left unsupervised, so make
    sure you are right beside her when she's inside jumper. The best method to prevent acid reflux in the sleeping baby is permit baby sit up while sleeping or raise the head in the crib or sleeping area.

    Also visit my weblog :: Discovering Swift Procedures For baby swing

    ReplyDelete
  4. of course like your website but you have to test the spelling on several of
    your posts. Many of them are rife with spelling issues and I
    find it very bothersome to tell the truth nevertheless I'll certainly come again again.

    Also visit my web page; cuisinart stand mixer review *itisberenini.eu*

    ReplyDelete
  5. He then commences to demonstrate the Filter Queen Indoor
    Air High-quality Technique referred to as the Defender.
    00 and order the vacuum cleaner which is quiet, less difficult to implement, and greatest of all the far better cleaner.


    my website Vacuum Cleaner Characteristics Explained *http://intra.vasemmisto.org/*

    ReplyDelete
  6. Friends and families have been in attendance to lend support
    and love to the family and child. At five months, infants
    can spot small objects and be in a position to follow moving objects.


    my site; best portable baby swing [Bookmark.Linkmu.com]

    ReplyDelete
  7. There exists a substantial demand for that Hoover vacuum cleaners as they are between the ideal vacuum cleaners
    readily available while in the market place. When you have opted for the bagless model, you are able to rest assured that the dirt is collected into a
    cup that may be emptied at typical intervals.

    Also visit my web page; Realistic Merchandise In vacuum
    cleaner - An Analysis ()

    ReplyDelete
  8. A further benefit of lower affect aerobic exercising is the
    fact that patients tend to remain functional
    ''. With millions of individuals suffering from continual back pain,
    its no wander the 1st question mark has to become with our sleeping patterns.


    Look at my homepage benefits inversion table (recentarticless.info)

    ReplyDelete
  9. Husbands and wives should also refrain from sex 72 hours after ovulation.
    When your infant is first born it is likely you will produce colostrum, a sticky yellowish fluid, known by the
    well deserved nick name " liquid gold".

    my web blog: best portable baby swing (http://www.happydogdays.co.uk/community/blogs/20197/22019/successful-tricks-for-baby-swing)

    ReplyDelete
  10. Simply maintain the food mill in the plastic bag so it may be placed in the bag following a
    meal. ' Although these sharks aren't targeted directly
    by commercial fisherman, they're a bycatch (accidentally caught in the nets).

    Review my web site: best baby swings

    ReplyDelete
  11. This article demonstrates to you ideas for pallettes, graphics,
    decorating options, and also fun puzzles to generate planning
    baby shower a little easier. In 2007, "Talk" co-host Sara Gilbert gave her daughter the unisex name Sawyer.


    Also visit my web-site: best baby swing to buy **

    ReplyDelete
  12. Use them caution, and always make an effort to read online reviews before you decide
    to buy one. The long-term health risks of pesticides is currently becoming called
    wide-spread use of chemicals in farming started only in the middle with the 20th century.



    Feel free to surf to my web site ... best baby Swing reviews

    ReplyDelete
  13. Their effective cleansing abilities and innovative options may take
    within the most demanding cleaning tasks successfully. The air that's normally deflected out the back or another path is directed on the floor to allow the canister vacuum to glide along behind you.

    my web site: No-Fuss vacuum cleaner Programs - Insights

    ReplyDelete