Friday, April 15, 2022

†ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ቅዱስ አቡነ ሲኖዳ†



በስመ ሥላሴ
ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ቅዱስ አቡነ ሲኖዳ መርህ ለመንግስተ ሰማያት”
“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅመ እግዚአብሔር” (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።) መዝ.፻፲፭፡፲፭ (115፡15)
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡ (እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አቡነ ሲኖዳ የተባሉት አንዳንድ ፀሒፍያን ሀገራቸው ሸዋ ነው ይላል። ሀገራቸው ግን ጎጀም ደብረ ጽሞና ምስራቅ ከተባለው አሁን ገዳማቸው ከሚገኝበት ቦታ ተወለዱ። በ፲፬ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በአፄ ይስሐቅ ጊዜ የነበሩ ጻድቅ ናቸው። በዚህ በጎጀም በደብረ ጽሞና የነበሩት ሕዝቦች በዘንዶ ያመልኩ ነበርና ያንን የሚያመልኩትን ዘንዶ በመስቀላቸው ሲባርኩ ከሁለት ተሰንጥቆ ሞቷል። የሀገሩንም ሕዝብ አስተምረው አጥምቀው ቤተ ክርስቲያን በእመቤታችን ስም ሰርተው ሰጥተዋቸዋል። እነሱም “ሲኖዳ ቅዱስ አቡነ መርህ ለመንግስተ ሰማያት” ብለዋቸዋል። በዚህም ጌታችን አስደናቂ ቃል ኪዳን ሰጥቶአቸዋል።
ቃል ኪዳናቸውም እንደ አባ ኪሮስ ቃል ኪዳን የማይወልዱ መካናት በመቃብራቸው ዙርያ እየተንከባለሉ እምነታቸውን እየታሹ እየተሳሉ ሲሄዱ መካናት በሙሉ ይወልዳሉ አያፍሩም። በዚህም በመዋእለ ዘመናቸው በዘጌው የነበረው ጨካኙ ህዝብ ናኝ የተባለው ሰይጣን በልቡ አድሮ እሳቸውን አስወስዶ እጃቸውንና እግራቸውን አስቆርጦአቸዋል። ለጣኦት ስገዱ ብሎ ከዚህም በኋላ መላእክት መጥቶ ጊዜ ሞትህ ደርሷል፤ አትዘን ብሎአቸው ተሰውሯል። ወዲየው ደቀ መዛሙርታቸውን ጠርተው ተሰናብተው በዚህ ዕለት ማለትም ኀዳር ፲፯ ቀን አርፈው በደቅ እስጢፋኖስ ተቀብረዋል። ኋላ ግን ልጃቸው ደቀ መዝሙራቸው የሆኑት አባ መቃርስ የተባሉት አፅማቸውን አፍልሰው አምጥተው አሁን በስማቸው በተሠራው ገዳም ጎጀም በደብረ ፅሞና አስቀምጠውታል። በአሁኑ ሰዓት አጽማቸው በዚህ ይገኛል። ዛሬ በዚህ ገዳም አከባቢ እህል በቅሎ የሚበረከትበት ልጅ የሚወለድበትና የሚያድግበትቦታ የጤና ሀገር ሆናለች። የአባታችን በረከታቸው ረድኤታቸው በሁላችን ላይ ጸንቶ ለዘላለሙ ይኑር። አሜን ይቆየን። ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ!      
ምንጭ፡- የኢትዮጵያውያን ተወላጆች ቅዱሳን ታሪክ  በሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ፣ የዛሬው መጽሐፈ ስ/ሳር፣ ነገረ ቅዱሳን 

No comments:

Post a Comment