ኢየሱስ
ክርስቶስ ምስጢረ ሥላሴን አላስተማረም፣ የአምላክ ልጅም አይደለም፣ የአምላክ ልጅ ነኝም አላለም እያሉ ዓለምን ለሚያወናብዱት ለነአሕመድ
ዲዳት ማብራሪያ
ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በአካል አንድ ብቻ አልነበረም፡፡ በአካል በስም፣ በግብር ሦስት፣ በመለኮት፣ በባሕርይ በህልውና አንድ ሁኖ አንድ አምላክ እየተባለ ዘለዓለም ሲቀደስ ኑሯል፤ይኖራል፡፡
ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በአካል አንድ ብቻ አልነበረም፡፡ በአካል በስም፣ በግብር ሦስት፣ በመለኮት፣ በባሕርይ በህልውና አንድ ሁኖ አንድ አምላክ እየተባለ ዘለዓለም ሲቀደስ ኑሯል፤ይኖራል፡፡
ሥላሴ
በስም:- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡ በግብር አብ ይወልዳል፤ ያሠርጻል፤ ወልድ፤ ይወለዳል፤ መንፈስ ቅዱስ ይሠርጻል፡፡ በአካል አብም፤ ፍጹም አካል (ህልውና፤
ገጽ) አለው፤ እንደዚሁም ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ የተለየ ፍፁም አካላት አሏቸው። አካልና ሰውነትን ያልተማሩ ሰዎች ያደባልቋቸዋል፤ አካል ሦስቱም፣አብ ወልድ ፡ መንፈስ ቅዱስ ለእየራሳቸው
አሏቸው ሰውነት ግን የሚጨበጥ የሚዳሰስ ያለው ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይኽውም ሥጋ በመልበሱ፡፡ በምስጢረ ሥላሴ አካል ለቀዋሚ ነገር ለመንፈስ
ነው የሚነገረው፤ አይታይም አይዳሰስም፤ መንፈስ ነው፡፡ አካል በምናውቃቸው በሌሎቹ ቋንቋዎች (ፕሮሶፓን ግሪክ፤ ፔርሶና ላቲን፤
ፔርሶን እንግሊዝ፣ ጣልያን ፈረንሳይ ነው፡፡ ሰውነት (በአልካ በሚዳሰስ ትርጉሙ)ሶማ ግሪክ፣ ቦዲእንገሊዘ፡ ኮርም ጣልያን፡ በፈረንሳይ
በንባብ ኮር በአፃፃፍ ኮርጥስ፡ ላቲን ኮርፑስ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ ረቂቅ አካሉ ሥጋ ስለለበሰ።
ሰውነት(የሚዳሰስ አካል) አለው የሚባለው፡፡ ባሕሪያቸው መለኮታቸው፣ መንግሥታቸው፣ ሥልጣናቸው ግን አንድ ነው፡፡ በአካል ሦስት
ስለሆኑና በመለኮት፣ በባሕርይ አንድ ስለሆኑ፣ እኔ እያለ በነቢያት በክርስቶስ፣ በሐዋርያት፣ እግዚአብሔር ሲያናግር ኑሯል፡፡
- (ዮሐ. 1፡1-3) በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ይህ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ሁሉም በእሱ ሆነ፡፡ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም። ከዚህ ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ ጋራ ሌላ እግዚአብሔር ወልድ እንዳለ እና ያለእሱም ምንም እንዳልሆነ ይናገራል፤ በአካል የተለያዩ በመለኮት ግን አንድ የሆኑ፤ ሁለት አካላት፤ አንድ እግዚአብሔር እንድ እግዚአብሔር እንዳለ ወንጌላዊው ቁልጭ አድርጎ ገልጧል፤ ከዚህ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ አካላት አብና ወልድ ናቸው፣ ዝቅ ስንል ደግሞ ሦስት አካላት መሆናቸውን እናያለን፡፡
- (ማቴ.3፡16-17) ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኋ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ወርዶ ከእሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም ድምፅ ከሰማይት ወጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡ በዚህም በአምሰላ ርግብ የወረደው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፤ የምወደው ልጄ ያለ እግዚአብሔር አብ ፤ ተጠማቂው ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በትስብእቱ ዐማኑኤል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው፣በኋላ የቤተክርስቲያ ሊቃውንት ሥላሴ ብለው የሰየሟቸው አካላት፣ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡(ማር.1፡911፤ ሉቃ.3፡21-22)
- ይኽው ታሪክ በድብረ ታቦርም ተደግሟል፣ ያውም ከትእዛዝ ጋራ፣ (ማቴ.17፡1-6፤ማር.9፡2-13 ሉቃ.9.28-36)"እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት፡፡"፥
- (ዮሐ.11፡4) ኢየሱስም ሰምቶ፣ ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ፡፡
- (ዮሐ.11፡-፡27) አዎ!ጌታ ሆይ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ቁርአንና እስላሞች እንደሚሉት አምላክ ባይሆን ኑሮ፣ አይደለሁም ተሳስተሸል፣ እኔ አምላክ አይደለሁም ይላት ነበር፡፡