![]() |
በጠቅላይ ቤተ ክህነት አካባቢ ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” ብሎ የሰየመውን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የእገዳ ደብዳቤ ጣለበት፡፡ የጉባኤው
መስራቾች ነን ባዮች እነ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ፡ ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል ፡ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ
ጥላሁን እና ሌሎች 27 የሚሆኑ ሲሆን ጉባኤውን እያደራጁ የሚገኙ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት እያጡ የመጡ ግለሰቦች እንደሆኑ ለመረዳት ችለናል::