Wednesday, October 3, 2012

†♥† ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ†♥† መዝ.111፡1-6



በሰመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
†እንኳን ለአባታችን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የበዓላቸው  መታሰቢያ  በሰላም አደረሰን።†
“ጻድቅ በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል እውነት እላችኋለሁ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። "  የማቴዎስ ወንጌል ፲፡፵­-፵፪ (1040­-42)
ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ የጸድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል መዝ.111፡1-6 ምሳሌ 10፡7 ማቴ. 10፡40-42
ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር አብ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር  ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ የአባቴ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ነገር እና መልክአ በማብዛት አይደለም በማሳነስ በማስረዘም አይደለም በማሳጠር እንድጽፍ ያነሳሳኝ ክብርና ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባዋል አሜን በእውነት፡፡


አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ . ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ ተክለ ሃይማኖት ማለት ደግሞ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡

ሶስቱ ምክሮች

(ደቂቀ ናቡቴ መስከረም 23,2005 ዓ.ም) ይህን ፅሁፍ የት እንዳነበብኩት በውል ትዝ አይለኝም እናንተ ግን ትማሩበት ዘንድ እንድታነቡት አቀረብኩላችሁ ታሪኩ እንዲህ ነው፡-  

ከወንድሞች አንደበት ከሰማሁት ብሎ ይጀምራል ፀሀፊው ቀጥሎም  ባንድ ወቅት አንድ ባል እና ሚስት በትዳር ሁለት ልጆችም ነበራቸው፡፡  አብረውሲኖሩ በመሃላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው፡፡ በቤታቸው ግን የሚላስ የሚቀመስ በመጥፋቱ ምክንያት  ይህንን ችግር ለዘለቄታው ለመፍታት ባል ራቅ ብሎ ሄዶ  ሊሰራ ተስማምተው  ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ መስራት ጀመረ፡፡ በተከታታይ 13 ዓመታት ሰራ ከዚያም ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ተነሳ፡፡ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ መጣ ምን? ደሞዝ፡ ደሞዙ ምን ሆነ? በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነውን 3000 (ሶስት ) ብር  ተሰጠው፡፡ ምን ያድርግው? ተመልሶ እዛው ስራውን ይቀጥል? ወደ ናፈቁት ቤተሰቦቹ ይሂድ? ይቻላል ግን ተመልሶ ቢሰራ ደሞዙ መቆራረጡ አይቀሬ ነው፣ ወደ ቤተሰቦቹ እንዳይሄድ 13 ዓመት ይህን ብቻ ሰራሁ ቢል ማን ያምነዋል? አወጣ አወረደ በመጨረሻም  ሌላ ቦታ ተቀጥሮ ለመስራት ወሰነ፡፡  ሌላ ጉዞ..፡፡ ብዙ ከተጓዘ ብኋላም አንድ አባት አገኘ፡፡
እኛም አባት ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ምንስ ትፈልጋለህ? አሉት፣ አሱም ሁሉንም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው፡፡
አኛም አባት አንዲህ አሉት እንግዲያውስ የምትፈልገውን ማግኘት ቀላል ነው፡፡
እሱም "እንዴት አባቴ?" ሲል ጠየቃቸው
እሳቸውም "በል አንድ ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ" አሉት የቸገረው ነውና ነገሩ አሱም አንስቶ አንድ ብሩን ሰጣቸው፡፡
እኝህ አባትም "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይሉታል፡፡

Monday, October 1, 2012

ቅዱስ ያሬድ ዜማውና 1500ኛ አመት መታሰቢያ ክፍል አራት


1500 ዓመት የቅዱስ ያሬድን በዓል ምክነያት በማድረግ ክፍል አንድ ክፍል ሶስት  "ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዜማውና 1500ኛ አመት መታሰቢያ"  በሚል ርእስ አስነብበናችኋል፡፡  ዛሬ ደግሞ በክፍል አራት የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች  በሚል ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶ ለዜማው መመሪያ እንዲሆኑ የፊደል ቅርጽ  የሌላቸው ስምንት ምልክቶ የፊደል ቅርጽ  ያላቸው  ሁለት የዜማ ምልክቶች አሉት፡፡ እነዚህ ምልክቶች በሙሉ ምሳሌነታቸው ስለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከልደት እስከ ዕርገት ላደረገው የመስቀል ጉዞ ነው፡፡

  •   ድፋት(  )ምሥጢሩ የክርስቶስን ከሰማየ ሰማያት መውረድ ያስረዳል፡፡

  •   ሂደት ( )ምሥጢሩ ጌታ በዚህ ዓለም እየተመላለሰ /እየተዘዋወረ/ ማስተማሩንና በተከሰሰም ጊዜ ከሐና ወደ ቀያፋ ወደ ሄሮድስና ወደ ጲላጦስ ምንም ሳይናገር መመላለሱን ያስረዳል፡፡