†♥†በስመ ሥላሴ†♥†
†♥† “ስምከ ሕያው ዘኢይመውት”†♥† /”ሰው የተመኘውን ከሰራ የሚጠብቀው
ሞቱን ነው” (አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ 1932-1982)
†♥† ወበዛቲ ዕለት
አዕረፈ አቡነ አላኒቆስ (ጥቅምት ፳፩) (በዚህ ቀን ትልቁ ጻድቅ
አቡነ አላኒቆስ አረፈ)።
†♥† “ከቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15
†♥† ሀገራቸው ሸዋ አንኮባር ሲሆን ወግዳ ወይም
ምግዳ ይላቸዋል። አባታቸው አጼ ይኩኖ አምላክ እናታቸው ንግስት ኮከቢያ ይባላሉ። የንጉስ ልጅ ሲሆን መናኔ መንግስት ወብእሲት
ናቸው። የተወለዱትም በ1238 ዓ.ም ነው። እንቁ ባህርይ የመል የቅዕል ስም አላቸው። ንጉሱ አባታቸው አግባና መንግስቴን ውረስ
ሲላቸው እምቢ ብለው ወደ እመቤታችን ስዕል ሄደው ተደፍተው አለቀሱ። እመቤታችንም ክፍልህ ምናኔ ነው ስትላቸው የአባታቸው
መንግስት እንደሚያል የእግዚአብሔር መንንግስት ብቻ ነው የማያልፈው ብለው ወደ ወሎ ሐይቅ ሄደው ተናደው ተወርውረው ከባህር
ገቡ። በዚያን ጊዜ መላእክት መጥተው አወጡአቸውና አፅናነትው በዚህ ገዳም እንዲቀመጡ ከአበምኔቱ ጋር አገኛቸው። በዚህ ገዳም መንኩሰው
ወደ አክሱም ገዳም ሄደው የታቦተ ሙሴ አጣኝ ሆኑ። ትልቁ ታሪካቸውም ጓደኛቸው ከእሳቸው ጋር አብረው የሚኖር መነኩሴ
የሚያገለግላቸውም ነበርና በንሰሐ አባትነት የያዟት አንዲት ሴት ነበረች። በዚህ ጊዜ ከአሽከሯ አረገዘች፤ በኋላም በሏ መኮነኑ ከዘመቻ
ሲመጣ ከምን አረገዝሽው ብሎ ቢጠይቃትና ቢገርፋት ሲጨንቃት ከንሰሐ አባቴ ነው ያረገዝኩት ብላ ንሰሐ አባቷን በሐሰት ወንጅላ ወስዳ
ሰጠችው። ከዚህ በኋላ ያነን መነኩሴ እገድላለሁ ብሎ ወደ ገዳሙ ሄደ። አቡነ አላኒቆስም ይህንን ነገር ሰሙ። ወደ እኔ ኑ ብለው ጠሩአቸው። ያም በሐሰት የተወነጀለው መነኩሴ ሄዶ ወደ
አቡነ አላኒቆስ ተጠግቶ አለቀሰ። ሰገደ ጻድቁም እሷን አስጠርተው ሲጠይቋት ስታፍር አዎን አለች፤ በሐሰት በዚህም ጊዜ ከሱ ከሆነ
ይወለድ ከሌላ ከሆነ ግን አይወለድ ብለው ገዘቷት፣ ረገሟት፤ በሆዷ ይዛ 22 ዓመት ጢም አውጥቶ ጥርስ አብቅሎ ተወለደ።
ህፃኑ ሲወለድም “ወእመሰ እምዘመደ እስራኤል ክብርት እንተ
ረስየተኒ ገብረ” በሎ መሰከረባት። ከዚህ በኋላ ህፃኑንም አባታችን አሳድገውት ስሙንም አባ ተወልደ መድህን ብለው አመንኩሰው በምናኔ
እንዲኖር አድርገውታል። ግድልም አለው፤ ታቦትም አለው። በዕብላ ወረዳ አሉጌን ከተባለው ተራራ ላይ ገዳም አለው። እንግዲህ
አባታችን ታሪካቸው እጅግ በጣም ብዙ ነው። ዛሬ ገዳማቸው የሚገኘው ትግራይ ማይበራዝዬ ነው። ይህን ሁሉ ተጋድሎ አድርገው
አባታችን በክብር በዛሬዋ ቀን ዐርፈዋል።