- "እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው"
- "14 ዓመት ደክሜ ከሰራሁት ቤቴ የትም አልወጣም"
- "ወደዳችሁም ጠላችሁም ከዚህ የትም አልሄድም"
- "አዎ አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ፣ ያንን ትቼ ይህንን ህዝብ ላገለግል መጣሁ"
- "ከዋሺንግተን ዲሲ እስከ ካሊፎርኒያ የኔ ግዛት ነው"
- "ከዚህ በኃላ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ መፃተኛ የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም"
የደብረ ምሕረት የትላንትናው ትዕይንት ይሄን ይመስል ነበር |
በትላንትናው እለት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ላይ የተገኙት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ላይ ልክ እንዳደረጉት ምንም የምታመጣው ነገር የለም የኔን የላከኝ ቀበሌ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስ ነው በማለት ለበዓል የታደመውን ምዕመን አስገርመውት ውለዋል። ትላንት በጠዋት የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በፓሊስ ውጪው በተቃዋሚ ታውኮ ውሏል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኃላ በመምህር ዘላለም ወንድሙ አማካኝነት የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲያስተላልፍ በተሰጠቅ ጥብቅ መመሪያ መሰረት መጥቶ በማያውቅበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ቆሞ ባለሙዋልነቱን
በሚገባ አረጋግጧል፣ እንደሚታወሰው መምህር ዘላለም ወንድሙ ከዚህ በፊት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ፈቃድ በአቡነ ፋኑኤል አደራጅነት እና አዋቃሪነት በተከፈተው "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት ጽ/ቤት" በሚባለው የሰሜን አሜሪካ የሰባኪያን እና ዘማሪያን ባለሙሉ ሥልጣን የበላይ ኃላፊ በሚል እንደተሾመ ይታወሳል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ በትላንትናው ድራማ ላይ አቡነ ፋኑኤል ለእኔ የሚናገርልኝ ሰው ከሌለ እኔው እራሴ ስለ እራሴ ማንነት እነግራችኃለው ብለው ህዝቡን ስለራሳቸው ግድል እና ድርሳን ሲናገሩ ከግማሽ ሰዓት በላይ አሳልፈዋል መዚህም መሠረት እኔ ልሰራ እንጂ ልከፋፍል አልመጣሁም ስለዚህ ከዚህ በኃላ ስደተኛ ወይም ገለልተኛ ሳንል በተጠራንበት በመሄድ እናገለግላለን በማለት አስጨብጭበዋል፣ እንደእውነቱ ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ከለየው ጋር ሄዶ መባረክም ሆነ እናቀራርባለን ብሎ ማለት ሥርዓት አልበኝነታቸውን የበለጠ ያጎላዋል እንጂ የሥራ ሰው መሆናቸውን አያስመሰክርም፡ ከዚህ በተጨማሪ "እኔ የሁሉም አባት ነኝ ማለታቸውም" ነገ የአባ ሰላማ ብሎግ ባለቤቶች (ፕሮቴስታንቶቹም) ቢጠሯቸው የሁሉም አባት ስለሆኑ ሄደው ሊባርኩ ነው ማለት ነው አንባቢ ያስተውል።

አቡነ ፋኑኤልና ካሕን መስሎ የቆመው body gourd |
በእለቱ ከታዩት በርካታ ካሜራዎች እና ተቃዋሚዎች ጥቂቱ |
በዋሽንግተን አካባቢ በተለያዩ አስተዳደር ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አሉ ከነዚህም ጥቂቶቹ
፩/ በእናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
፪/ በስተደኛው ሲኖዶስ አስተዳደር ያሉ
፫/ ያሉበገለልተኛ አስተዳደር ያሉ
፬/ ስደተኛውም ሲኖዶስ ወይም የሀገር ውስጥ ሲኖዶስ የማይመሩ ነገር ግን በራሳቸው የቦርድ አስተዳደር ያሉ
፭/ በእናት ቤተ ክርስቲያን ያሉ ነገር ግን ያፓትሪያሪኩን ስም በጸሎት የማይጠሩ
፮/ በገለልተኛ አስተዳደር ያሉ ነገር ግን የባለቤቶቻቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጥቂት አባላት ስር የሚተዳደሩ
እውነት ታዲያ አቡነ ፋኑኤልን መሪ አድርጎ ተቀብሎ የሚሰራ የትኛው ክፍል ነው እንደእርሳቸው አባባል የመጡት ለሁሉም ነው ብለዋል ታዲያ ይሳካላቸው ይሆን? ለጊዜው አሸንፈው የገቡት የራሴ ነው የግል ንብረቴ ነው ታክስ እከፍልበታለሁ ወይም መጦሪያ ቤቴ ነው በሚሉት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፣ ቀጥሎስ የትኛውን አሸንፈው ወይም ብልጣ ብልጥ አባባላቸውን ተጠቅመው ማስተዳደር ይችሉ ይሆን? ጥያቄውን ለአናባቢ በመተው የደፊቱን አብረን ለመመልከት የዛሬውን በዚህ እያጠቃለልን በመቀጠል የአቡነ ፋኑኤልን አካሄድ ለአንባቢ እየተከታተልን ለማቅረብ ቃል እንገባለን።
ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን አሜን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
god bless abune fanuel MAHBER SETANOCHE GUDACEW FELA
ReplyDeleteI have learn several just right stuff here. Definitely worth bookmarking
ReplyDeletefor revisiting. I wonder how a lot effort you place to create any such
great informative website.
Feel free to surf to my homepage Dr Dre Beats Headphones