በ1912 የተወለዱት አና በኢትዮጵያ እና በኤርትራ
በክህነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉት ብፁእነታቸው ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ይስሃቅ እንዲሁም ቅስናን ከኤርትራው ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመሆን
ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል እንዲሁም ከግብፅ ከፍሊስጤም እና ከሊባኖስ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በማቀለል ከፍተኛ አገልግሎትን
ፈፅመዋል ብፁእነታቸው የዕብራየስጢኛ እና የአረቢኛ ቋንቋም ተምረዋል ፡፡
ላለፉት 60 ዓመታት
በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር የሚጓዙትና ጥንታዊ
ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት በተወለዱ
በ 92 ዓመታቸው የካቲት 10 ለሊት ባደረባቸው ሕመም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል የአባታችንን ነፍስ አምላክ በገነት ያሳርፍልን::
No comments:
Post a Comment